የዘር ግብዓት አቅርቦት ባለመቅረቡ የተጠበቀውን ምርት ማግኘት እንዳልቻሉ የዎላይታ ዞን አርሶአደሮች ቅሬታ አቀረቡ።

ዞኑ በዘንድሮው በልግ እርሻ ከ129 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ለማልማት አቅዶ ከ138 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በአመታዊ የሰብል አይነቶች መሸፈን መቻሉን ከግብርና መምሪያ ያገኘነው መረጃ ቢያመለክትም የዘር ግብዓት አቅርቦት ባለመኖሩ የተጠበቀውን ምርት ማግኘት እየተቻለ አለመሆኑን አርሶአደሮች ቅሬታ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ለአብነትም በዘንድሮው የበልግ አዝመራ ወቅት ምርጥ ዘር አቅርቦት በጊዜ ባለመድረሱ የተጠበቀውን ምርት ማግኘት አለመቻላቸውን በዳሞት ፑላሳ ወረዳ ውስጥ በተለያዩ ቀበሌያት የሚገኙ ሞዴል አርሶአደሮች ቅሬታ አቅርበዋል።

በዞኑ ውስጥ ከተፈጥሮአዊ ሁኔታ አንፃር የበልግ እርሻ ቀደሞ የሚጀመርበት በዚሁ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ውሰጥ በግብርና ሥራ ውጤታማ ከሆኑ ሞዴል አርሶአደሮች መካከል አቶ ቦሎሼ ጆርጌ እና አቶ አሳሌ ጎዳና በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ለግብርና ሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን አስቀድሞ ማቅረብ እንደሚጠብቅባቸው አሳስበው ከዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች የተጠናከረ ድጋፍ እንዲደረግላቸው አፅንኦት ሰጥተው ተማፅነዋል።

በዘንድሮ በልግ እርሻ ወቅት የሰብል አይነቶች መካከል በቆሎ፣ ቦሎቄ፣ ማሽላ፣ ድቡልቡል፣ ስኳር ድንች፣ ጎደሬ፣ አተር እና ሌሎችንም ምርቶችን ከ129 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ለማልማት አቅዶ ከ138 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ በማልማት ከዕቅድ በላይ ሸፍነው እያለማ ስለመሆኑ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከግብርና መምሪያ ያገኘው መረጃ ቢያመለክትም በተቃራኒው የዘር ግብዓት አቅርቦት ባለመኖሩና እንዲሁም በጊዜ ባለመቅረቡ የተጠበቀው ምርት ማግኘት እየተቻለ አለመሆኑን በተለያዩ መዋቅሮች የሚገኙ አርሶአደሮች ቅሬታ አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *