“በ50ዎቹ ነገሥታት ምድር-ዎላይታ ሶዶ! የ32 ምንጮችና የ12ቱ ጅረቶች መነሻ፤ የዎላይታ ነገስታት ጥንታዊ ስፍራ፤ የ”ሞቼና ቦራጎ” ዋሻ መገኛ ከሆነው ዳሞታ ተራራ ጉያ የምትገኘው ዎላይታ_ሶዶ ስፋት ብቻ ሳይሆን ጥራትንም በሚመጥን ፍጥነት እያበበች ነው” በሚል ጋዜጠኛው በከተማዋ የመጀመሪያ ቀን ምልከታውን አብራርቷል።

ጋዘጤኛው የመስክ ምልከታ ቆይታ አጠናቅቆ በዛሬው ዕለት፦ “የዎላይታ ሶዶ (የስሜ ከተማ) ሌላኛው መልኮች” በሚል ምልከታውን በጥልቀት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

“አንድ ከተማን ተመራጭ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ”ሳቢነትና ማረፊያ…” የሚሉት ይገኙበታል። እነዚህ ሌላውን ነገር ያመጡታል።

እኔም በዎላይታ ሶዶ ቆይታዬ በከተማዋ ያሉ ”አይን ከፋች” ቦታዎችን ተዟዙሮ ከመቃኘት ባሻገር ለሥራ ዝግጁ የሆኑ ውብ የመንገድ ዳርቻዎችን ጨምሮ እንደ ”አቦል ጋርደን ካፌ” እና ”ሊዲያ የባሕል ምግብ” ባሉት ቀጠናዎች ተገኝቼ መልካም ነገር ታዝቤያለሁ። ለዎላይታ ሶዶ ተጨማሪ መዳረሻ ናቸው። ጋላታይስ🙏

መፍጠን ካልሆነብኝ ”ዎላይታ ሶዶ እንደ ሳንባ ንፁህ አየር ስቦ ለማስወጣት በሚያስችሉ አረንጓዴያማ ውብ ስፍራዎችም እያጌጠች ነው” ለማለትም ያስችላል። ከሁሉ በላይ በእንጨት ውጤቶችና ቀለል ባሉ ቁሳቁስ የተዋቡበትን መንገድ ስመለከት አንዳንዴ ያልተለመደ ነገርን መድፈር ጥሩ ነው እንድል አድርጎኛል። ወድጄዋለሁ!

በነዚህ ቦታዎች ብዙዎች ደረጃውን በሚመጥን ”ዘመናዊ ንግድ” ተሰማርተዋል። እነሱም ከተማዋም ተጠቀመች ማለት ነው! ”የኮሪደር ልማት” በሚል በቅርቡ በአዲስ አበባችን ደረጃ የተጀመረው ተነሳሽነት አካል ይመስላል። በሕዝብ በተለይ በወጣቶች ተደግፎ በሌሎችም ከተሞች መቀጠል አለበት። ሶዶ ለማ ነኝ ከዎላይታ ሶዶ” በሚል ጋዜጠኛው ምልከታውን በገፁ አስፍሯል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *