የዎላይታ ዲቻ ደጋፊዎች ምኞታቸው ሰምሮ አዞዎቹ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊግ መግባታቸው በመረጋገጡ ደስታ እየገለፁ ነው

አምና የጦና ንቦች ደጋፊዎች አዞዎቹ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መውረዱን ተከትሎ እንዲህ ብለው ሀሳብ ሰጥተው ነበር👇

👉አርባምንጭ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከዎላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ጋር ተመጣጣኝ ቁመና ላይ የነበረ፣ ሁለቱ ክለቦች በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የዱንጉዛ ደርቢ በመባል በሚታወቅ ጠንካራ የፉክክር ስሜት ድቻ ጠንክሮ እንዲወጣ ስያደርግ የኖረ ጠንካራ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አድማቂ ክለብ ነው።

👉ያኔ አርባምንጭ ከተማ እኳቡ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ገብቶ ከአአ እየተመለሰ ዎላይታ ሶዶ ላይ የወቅቱ የዎላይታ ልማት ማህበር ሥራአስኪያጅ አቶ አልታዬ አየለ ለቡድኑ ደማቅ አቀባበል አድርገው፣ ምሳ ጋብዟቸው ስጦታ ሰጥቷቸው ሸኝቷቸው ነበር፣ ይህ ወንድማማችነትን ያሳያል፣ ዛሬ ቡድኑ ከሊጉ በመውረዱ እናዝናለን። ቶሎ እንድመለስም እንመኛለን።

👉በእግር ኳስ ዓለም ነገሮች አንዳንዴ በእንደዚህ አይነት መልኩ ይጠናቀቃሉ እና ክለቡ ዛሬ ከፕሪሚየር ሊግ መውረዱ እንደ መጥፎ አጋጣሚ ሊታይ የሚገባው አይደለም። እንደ ምታወቀው ከጨርቃ ጨርቅ የእግር ኳስ ክለብ ጀምሮ በኢትዮጵያ ደረጃ አርባ ምንጭ እና አከባቢው በእግር ኳስ ስፖርት ትልቅ ታሪክ የነበረው በመሆኑ ከዚህ ረጅም ልምድ ተነስቶ ክፍተቶችን በመሸፈን ክለቡ በሚቀጥለው አመት በእርግጠኝነት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንደሚመስል አልጠራጠርም ።

👉የዱንጉዛ ደርቢ አባል የነበሩት አዞዎቹ ወደ ታች ከፍተኛ ሊግ መውረዳቸው ያሳዝናል። ክትፎዎቹ አዞዎቹን በለጡ። አስጌ ሎላሼ ዘፈንህ አልጠቀመንም።

👉በጥንካሬያችሁ ጥርጣሬ የለንም። ነገ ሌላ ቀን ነው።አይዟችሁ!!!

👉ሎላሼ ❤❤❤አይዞን ብለናል !! ኳስ ድቡልቡል ናት ግን የወንድም ጋሞ ህዝብ ተወካይ የሆነው አርባምንጭ ከነማ በመውደቁ አዝነናል። ጥበብን ፣ ኳስንና ፖለቲካን ለይተን የምንደግፍና የምንቃወም ያድርገን 🙏 ኑን እስኖ 👐

👉የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረድ ያሳዝናል! አይዞን አዞዎቹ! ደጋግማችሁ እንደመጣችሁ ጠንክሮ በመስራት መመለስ የጠንካሮች ምልክት ነውና ይበልጥ መስፈንጠር ይቻላል። ላልተወሰነ ጊዜም ቢሆን የዱንጉዛ_ደርቢን ማየት አለመቻላችን እንደ አጠቃላይ የአካባቢውን የእግርኳስ ዕድገት የሚያቀጭጭ ከመሆኑ ባሻገር ፋይዳው ምንም አይታየኝም!

👉Arabaminch City Sport club is unlucky today. በእውነቱ ዛሬ አሸንፈው በመውጣት በሊጉ መቆየት  ነበረባቸው። ኳስ እንደዚህ ናት  በክሮሺያም እንዳየነው።⚽️

👉አሰጌን ከጋንታ ጋሮ ከተማ ህዝብ እንዲሁም ከክለቡ ደጋፊ ለይቶ ማየት ተገቢ ነዉ ጎበዝ።  ይህ ከፋፋይ ሰዉ በስራዉ በግሉ ይጠየቅ እንጂ የጋንታ ጋሮ ክለብ ነገ በስራ ወደ ሊጉ መመለሱ የማይቀር ነዉ። ይኸዉ ነዉ! ከዝህ ባሻገር ሌላኛዉ ወልቂጤ ከነማ በፕሪሚየር ሊጉ በመቆየቱ የተሰማኝ ደስታ እያጣጣምኩ ነዉ።

👉የአርባምንጭ ከተማ ደጋፊወች ፈፅሞ በክለባቸው መውረድ ማዘን የለባቸውም ምክንያቱም ዎላይታ ዲቻም የነሱ ተወካይ ነውና!! ዱንጉዛ!!

👉የአርባምንጭ እግር ኳስ ክለብ ዛሬ የደረሰበት ከደረጃ መውረድ የሚገባው አይደለም። ለመላው የአከባቢውና ለአገራችን የእግር ኳስ አፍቃሪዎችና አድናቂዎች “አይዟችሁ!” በምቀጥለው የጨዋታ ዘመን መንጭቃችሁ በመውጣት እንደምገባችሁ ተዳኝታችሁ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ይዛችሁ እየጨፈራችሁ በአፍሪካ መድረኮች እንድናይ ፈጣሪ ያብቃን እላለሁ። በዚህ ጊዜ ሁላችንም ከአዞዎቹ ጋር ነን!

👉አይዞን😭አዞዎቹ ልክ እንደ ጦና ንቦች የሊጉ ድምቀት ነበሩ። ብዙም ሳይቆዩ እንደሚመለሱ ተስፋ እናደርጋለን! ደግሞ ይመለሳሉ በእርግጠኝነት!

👉ጋንታ ጋሮ 🐊 እና የጦና ንቦች 🐝 ለአከባቢው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ከሚጫወቱት ሚና በተጨማሪ ለኢኮኖሚ የሚሰጡት አበርክቶ እጅግ ላቀ ያለ ነው። ለአብነት ባለፈው ቅርብ ጊዜ ለወጣት Yibeltal Elias የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የወዳጅነት ጨዋታ በማድረግ ትልቅ አበርክቶ አድርገዋል። ስለሆነም እንደ ግለሰብ መታርም ያለበት ሰው ካለ ግለሰብን ከሕዝብ እና ቡድን በመለየት ትክክለኛ የሙዚቃ መንገድን ማሳየት ተገቢ ነው።

👉 አርባ ምንጭ ከነማ በመዉረዱ በጣም አዝኛለሁ። ነገር ግን ጠንካራ አመራር እና ክለቡን ከልባቸው የሚደግፍ ማህበረሰብ ስላለው በቅርቡ ተመልሶ እንደምመጣ እምነቴ ሙሉ ነው።

👉በማንም ውድቀት ደስ አይለኝም። የውስጤን ሃዘን መደበቅ አቅቶኛል። የዎላይታ ድቻ ደጋፍ ብሆንም በአርባምንጭ ስኬት ደስ ይለኝ ነበር። በእውነት ዛሬ ግን ከፍቶኛል። በድጋሚ በክብር ወደ ፕርሚየር ሊግ እንደምትመለሱ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።

👉የውድድር አመት በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብቸኛው ተወካይ ዎላይታ ዲቻ ቢሆንም አርባምንጮች አይዞን ጠንክራችሁ ከሰራችሁ ዳግም ትመለሳላችሁ!!” በሚል አምና የዎላይታ ዲቻ ደጋፊዎች አርባምንጭ ከነማ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መውረዱን ተከትሎ ከገለፁት ሀሳብ የተወሰደ ነበር።

ደጋፊዎቹ ከአመት በፊት የገለፁት ምኞታቸው ሰምሮ ቡድኑ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊግ መግባቱን በማረጋገጡና በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ አዞዎቹ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አንድ ለምንም በማሸነፍ የ2016 የከፍተኛ ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ የተለያየ የደስታ እና የአጋርነት ሀሳብ እየገለፁ ናቸው።

እንኳን ደስ አላችሁ አዞዎች🐊❤ #wolaiatatimes

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *