ኦሞቲክ የተሰኘ ማህበር በ114 ሚሊየን ብር በኮይሻ ሎጅ ሊገነባ ነው ተባለ
ኦሞቲክ ጠቅላላ ንግድ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ114 ሚሊየን ብር ደረጃውን የጠበቀ ሎጅ በኮንታ ልዩ ወረዳ በኮይሻ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የማህበሩ የሎጆችና ሆቴሎች መምሪያ ሃላፊ አቶ አብዲ ፤ ማህበሩ በገበታ ለሀገር በታቀፈው የኮይሻ ፕሮጀክት ለሚገነባው ሎጅ አምስት ሄክታር መሬት ተረክቧል ብለዋል።
በሶስት ምዕራፍ ለሚካሄደው ግንባታ 114 ሚሊየን ብር በጀት መመደቡንና በአሁኑ ወቅት ግንባታውን ለማስጀመር በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
የእንግዳ ማረፊያ ናሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የያዘው የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በተያዘው ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።