ዎላይታ ዲቻ በኢትዮጵያ ዋንጫ ቡናን አሸንፎ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን የመሳተፍ ጉዞ በዳኝነት አድሎ ምክንያት ተገታ።

በዳኝነቱ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ በማሰማት የጦና ንቦቹ የተዘጋጀላቸውን የብር ሜዳሊያ እንዲወስዱ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ኢፍትሃዊነትን ተቃውሟል።

የጦና ንቦቹ ደጋፊዎች በአዲስአበባ በተካሄደው በዚሁ ጨዋታ በስታዲየሙ በሚያስደንቅ ሁኔታ በመሙላት “ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦኒያጋ (ከእኛ ጋር ያለው የሁሉ አሸናፊ ነው)” እያሉ በሚያስደምም ሁኔታ ቡድናቸውን እስከመጨረሻው በማዜም በማራኪ ጨዋታ ታጅበው ቢደግፉም ከዋንጫው ባለቤትነት በተጨማሪ በአፍሪካ መድረክ የሚወዳደሩበትን ዕድል አላሳኩም።

የጦና ንቦቹ በዛሬው ዕለት በአዲስአበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ በአጨቃጫቂ ሁኔታ 2 ፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች ተቆጥሮባቸው መሸነፋቸውን ተከትሎ ቡናዎች የዋንጫ ተሸላሚ ከመሆኑ ባሻገር ሀገራቸውን በአፍሪካ ኮንፌደረሽን ካፍ ውድድር ወክለው ይጫወታሉ።

ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታ መቻልን በማሸነፍ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ካፕ ውድድር የግብጹን ኃያሉን ቡድን ዛማሌክን አንበርክኮ ከዎላይታ አልፎ መላውን ኢትዮጵያ ስም ያስጠሩት የጦና ንቦቹ በሚያስደንቅ ሁኔታ በበርካታ ደጋፊዎች ድምቀት ታጅቦ በአይበገርነት ቢጫወትም በግልጽ ዳኝነት አድሎ ምክንያት አልተሳካላቸውም።

ዎላይታ ድቻ 1-0 ኢትዮጵያ ቡና
53′ አበባየሁ ሀጂሶ 67′ ዋሳዋ ጂኦፊሪ
116′ ጎል ዋሳዋ ጂኦፊሪ
Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *