“አዎ እኔም ሊስሮ ነኝ!! በ23 ዓመት ዕድሜዬ በራስ ጥረት እስከ እውቁ አሜሪካው ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በመቀላቀል ከአለም ሀብታም ሀገራት ከተሰበሰቡ ተማሪዎች ጋር በመማር አሸንፌ በከፍተኛ ውጤት በዋንጫ ሽልማት እንዳልመረቅ ሊስትሮነቴ ያላገደኝ ከታታሪው ሰራተኛ ህዝብ ማህፀን የወጣሁት!! አዎ ያ እኔው ራሴ ነኝ ፦ የመላው ህዝባችን ከጥንቱም እስካሁን የትጋትና ሰራተኝነት ነፀብራቅ ታሪክ የወረስኩት‼️

ታታሪው ከዎላይታ ሊስትሮነት ስራ ተነስቶ በራሱ ጥረት በልጅነቱ ህልሙን አሳክቶ በቅርቡ ከአሜሪካው አውቅ ሀርቫርድ ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ወጤት የተመረቀው የቀድሞ የዎላይታ ሊቃ ተማሪ ወርቅነህ ፎላ ከትናንት በስትያ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ካፕ ውድድር የግብጹን ኃያሉን ቡድን ዛማሌክን አንበርክኮ ከዎላይታ አልፎ መላውን ኢትዮጵያ ስም ያስጠሩት የጦና ንቦቹ በሚያስደንቅ ሁኔታ በበርካታ ደጋፊዎች ድምቀት ታጅቦ በአይበገርነት ተጫውተው በግልጽ ዳኝነት አድሎ ምክንያት ዕድሉን ባጡበት ሜዳ ላይ የነበሩ የቡና እግር ኳስ ደጋፊዎች በአደባባይ “ሊስትሮ ሊስትሮ” እያሉ የዲቻ ደጋፊዎችና ተጫዋቾችን ለማሸማቀቅ ጥረት ሲያደርጉ መደመጣቸውን ተከትሎ ከሚሊዮኖች የአንዱን ብቻ ለመማሪያነት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያቀረበው 🙏

ለመሆኑ ዎላይታ ማነው ❓በእውኑ ዎላይታ ሊስትሮ ብቻ ነውን ❓

ዎላይታማ የሊስትሮም ሰራተኛ፣

ዎላይታ ሎቶሪ አዘዋሪ፣

ዎላይታ የጀበና ቡና ሻጭ፣

ዎላይታ ጆብሎ አዘዋዋሪ፣
ዎላይታ የመኪና ሾፌር፣

ዎላይታ ጠቅላይ ሚንስቴር፣

ዎላይታ መከላከያ ሠራዊት፣
ዎላይታ የፖለትካ ቅመም፣

ዎላይታ ዶክተር፣
ዎላይታ ፕሮፈሰር፣
ዎላይታ ሙዚቃ አቀናባሪ፣

ዎላይታ የወንገል ሰባኪ፣
ዎላይታ ሞዴልና ዲዛይነር፣

ዎላይታ የመረብና የእግር ኳስ ተጨዋች
ዎላይታ ቦክሰኛ

ዎላይታ ሙዚቀኛ ፣
ዎላይታ ተማሪ፣

ዎላይታ መምህር ፣
ዎላይታ ተመራማሪ ፣

ዎላይታ ጋዜጠኛ ፣
ዎላይታ ባንክ ገዢ፣ ሠራተኛ፣

ዎላይታ የጥበብ ባለሙያ፣ አርትስት፣

ዎላይታ የፅዳት ሠራተኛ፣
ዎላይታ ታታሪ ነጋዴ፣

ዎላይታ ናሳን ጨምሮ በአለም ከፍተኛ ምርምርና ተክኖሎጂ ተቋም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለው፣

ዎላይታ በአፍርካ በአለም ከማንም ጋር ተቻችሎ የመኖር እሴቱን ተጠቅሞ የትም የሚገኝ፤

ዎላይታ ማንነቱን የማይረሳ ፣
ዎላይታ በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር ፣

ዎላይታ ፈጣሪን የሚፈራ፤
ዎላይታ ሌሎችን ከራሱ በላይ የሚወድ፤

ዎላይታ ለኢትዮጵያዊነት ስል በአዱዋ፣ ካራማራ ሀገሬ ብሎ በችግር ጊዜ ከፊት ተሰላፊ፤

ዎላይታ የመቻቻል የፍቅርና የአብሮነት ተምሳለት፣

ዎላይታ ሃኪም፤

ዎላይታ አምባሳደር፤

ዎላይታ ሚንሰቴር፤

ዎላይታ ሞዴል አርሶአደር፣

ዎላይታ ፖይሌት፣

ዎላይታ እንጂነር፣

ዎላይታ ኮምፑተር ባለሙያ

ዎላይታ ፖሊስ፣

ዎላይታ የህግ ባለሙያ፥

ዎላይታ የተኛውንም ሥራ የማይንቅ፣

ዎላይታ መሪን የሚወድ፣ የሚያከብር፣

ዎላይታ ውለታ የማይረሳ፣

ዎላይታ ህግን የሚያከብር፣ የሚያስከብር፤

ዎላይታ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብር ታታሪ ሰራተኛ፣

ዎላይታ የራሱ ጠንካራና የተደራጀ ሀገር የነበረው፣

ዎላይታ ስልጣንን በታሪካዊና በሰላማዊ መንገድ ያስረከበ፣

ዎላይታ በቅርቡ እንኳን ለውጥን ለመደገፍ ደምን የገበረ፣

ዎላይታ የሀገር ባለውለታ ቢሆንም በምላሹ በኢትዮጵያ የሚገባውን ጥቅምና ክብር የተከለከለ፣

በአጠቃላይ ህዝቡ ሁሉንም መሆንና የትም ከማንም ጋር ተግባብተው መሥራትና በታማኝነት መኖር የሚችል ኢትዮጵያዊ ቅመም ነውና እባካችሁ ይህ ህዝብ የትም ተከብሮና ሰርቶ ይኑር አትንኩት ለማሸማቀቅ አትሞክሩ ታታሪዎቹን🙏

ሰላም ለሃገራችን🙏 Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *