

የደረሰውን ከባድ አደጋ አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት፣ የጅቡቲውን ፕረዚዳንት ጨምሮ የተለያዩ ኢምባሲዎች መግለጫ ያወጡ ቢሆንም የፈደራል መንግስት እስካሁን አለማውጣቱ ብዙዎችን እያነጋገረ መሆኑ ተገለፀ።
በትናንትናው ዕለት በጎፋ ዞን መሬት ናዳ አደጋ የሞቱ ዜጎቻችን ቁጥር #ከ250 እንደበለጠ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ይጠቁማሉ።
እስካሁን የጅቡቲው ፕሬዝደንት ኦማር ጌሌ፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት እና በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ ኤምባሲዎች የሀዘን መግለጫ እንዳወጡ ተረጋግጧል።
ነገር ግን በዚህ ድንገተኛና ዘግናኝ አደጋ ለተጎዳው ህዝብ በተለይም የፈደራል መንግስት ፕሬዝደንት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምረው ሌሎችም ለምን ዝምታን መረጡ? የሚል ቅሬታ ከበርካታ ዘጎች እየተነሳ ይገኛል።
በወገኖቻችን ላይ ደንገተኛ አደጋ ከደረሰ አነሆ 24 ሰዓት ያለፈ ቢሆንም እስካሁን ማሽን በስፍራው ባለመድረሱ ህብረተሰቡ ከጥቂት ባለሙያዎቸ ጋር በመተባበር አስክሬን ማፈላለጉን በእጅ መሳሪያ እያከናወኑ ሲሆን ከፌደራል መንግስት ተገቢ የሀዘን መግለጫ እንኳን እስካሁን አለመሰጠቱ ባሻገር በተጨማሪም ከጥቂት እውነተኛ የሚዲያና የየሚዲያ ባለሙያዎች በስተቀር “የጉዳቱን ያህል የሚዲያ ሽፋን እየሰጡ አይደለም” የሚሉ ድምፆችም ከፍ ብለው እየተደመጡ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ሀምሌ 15 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ አደጋ ከደረሰ በኋላ የሰው ህይወት ለመታደግ ወደ በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ጠቁመዋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ለእርዳታ የመጡ ነዋሪዎች በቀበሌው በርካቶች በመሆናቸው የነዋሪዎች ቁጥር በውል እንደማይታወቅ ነው የተነገረው፤ በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልፆል፡፡
በአደጋው ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች 198 ወንዶች እና 81 ሴቶች ናቸው።
በተከናወነዉ የነፍስ አድን ስራ ከናዳ ውስጥ አምስት ሰዎች በህይወት የተገኙ ሲሆን ከዚህ በኋላ በህይወት የሚገኙ ሰዎች ላይኖሩ ይችላል የሚል ግምት ተሰጥቷል።
ከአደጋዉ በህይወት የተረፉ ሰዎች ቤት ንብረታቸዉ በመዉደሙ የተነሳ አስቸኳይ የረድኤት ድጋፍ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ ጥሪ በመቅረብ ላይ ይገኛል።
በቻልነው መጠን ለወገኖቻችን አጋርነታችንን እናሳይ👇
ለተፈናቀሉና ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጊያ የባንክ አካውንት በዞኑ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት ይፋ ተድርጓል::
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት :-
1000511561276
GOFA/Z/YEADEGA/G/Z/M/MAKUAAKUAMIA
Wolaita Times
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው