
በዎላይታ እየደረሰ ባለው የመሬት መሸንሸራተት አደጋ ከክልል ሆነ ፌዴራል እየተሰጠ ያለው ምላሽ አሳሳቢ መሆኑ ቅሬታ መፍጠሩ ተገልጿል።
የአከባቢው ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ነዋሪዎች ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ በሚገኘው አደጋ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት እየሰጡ ያሉት ምላሽ ዝቅተኛ እና ለዜጎች ጉዳት ትኩረት አለመስጠት ነው በሚል ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ።
በመሬት ናዳው አፈር ከተከደነባቸውን ለማውጣት አስቸጋሪ መሆኑ፣ በየቦታ እየተበጣጠሰ በሚደረመሱ አደገኛ ቦታዎች ለሚኖሩ ወገኖቻችን ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ አንጻር እየተስተዋለ ያለው መቀዛቀዝ እና መዘናጋት ዋጋ አስከፋይ ስለሆነ የአደጋ ስጋት እና ዝግጁነት ኮሚሽኑ በዚህ ዙሪያ የሰራው ሥራ ካለ በዝርዝር እንዲያሳውቅ በተመሳሳይም የክልሉ መንግስት በባለቤትነት በጉዳዩ ዙሪያ ወቅታዊ መረጃ መስጠት እንዳለበትና ተጨማሪ አደጋ ቢደርስበት በክልሉ ቸልተኝነት መሆኑ መሆኑን እየገለፁ ነው።
በሌላ በኩል “ኢትዮጵያ እና አብዛው ኢትዮጵያዊ ባሁኑ ሰዓት በዎላይታ የተከሰተውን አደጋተከትሎ ምንም ሀዘን እየገለፁ አይደለም። የፌዴራል መንግስትም የነፍስ አድንና ፍለጋው ሥራ እየሰራ አይደለም።ወደ ስፍራው ያቀኑ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አደጋውን ለዓለም የማሳወቅ እና ዓለማቀፍ ትኩረት እንዲገኝ እና በቂ ድጋፍ እንዲገኝ ከማድረግ ይልቅ ራሳቸውን እንደ ደጋፊ እና ረጂ በመሆን ተከታይ በመሰብሰብ ሥራ ተጠምደዋል” ሲሉ እየተቹ ይገኛሉ።

በተጨማሪም “ለተፈናቃዮችና ተጎጂዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት በመጠለያዎች ወረርሽኝ እንዳይከሰት ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እንዲሁም በፌዴራል ፓርላማ ዎላይታን የወከሉ ተወካዮች ወደስፍራው በማቅናት የወከሉትን ሕዝብ ሊጎበኙና ድምፅ ሊሆኑላቸው ይገባል” በሚልም እየጠየቁ ነው።
በዎላይታ ዞን እስካሁን በመሬት ናዳ የ13 ሰው ሕይወት ማለፉንና በርካቶች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም መፈናቀላቸውን ጋዜጠኛ ግርማ ጌቾ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ተነስቶ እስከ ጤፓና ማናአራ ቀበሊያት ባደረገው ቅኝት በርካታ ቀበሌዎች ያለው ሕዝብ በሥጋት ቀጠና ወስጥ እንደሚገኝና ዘላቂ መፍትሔ እንደሚፈልግ በማስረዳት አደጋው የተከሰተባቸው ካዎ ኮይሻ ወረዳ እና ኪንዶ ኮይሻ እንዲሁም ዲዳዬ ወረዳዎች የመልካም ምድራዊ አቀማመጥ እጅግ ተራራማና ቁልቁለት የበዛበት የበዛበት መሆኑንም አትቷል።


በጉዞው ወቅት ከተራራው ሥር የሚፈልቁ በረካታ ምንጮችና አከባቢው ተራራማ ከመሆኑም በላይ እጅግ ለም በመሆኑ በክረምት ወቅት ለመሬት መንሸራተትና ለናዳ በጣም የተጋለጠ አከባቢ መሆኑን መታዘቡን ከጋዜጠኛ ግርማ ጌቾ ዘገባ ጠቅሶ ከፍተኛ የሚዲያ ባለሙያና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አስራት አሳለ ልምዱ በመነሳት የሚከተሉትን የመፍትሔ አስቀምጧል።
አሁን አደጋው የተከሰተባቸው አካባቢዎች ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖችን የመርዳትና የማገዝ ሥራ ቅድሚያ ሰጥቶ ሕይወታቸው ካለፈ 13 ወገኖቻችን በተጨማሪ ዜጎቻችን እንዳያሳጣን የፍለጋው ሂደት በዞኑ እና በክልሉ በተዋቀረ ግብረሃይል እንዲመራ በማድረግ ተጋላጭ አካባቢ ያሉ ዜጎች ከዚህ በፊት በዲዳዬ ወረዳ የተደረገው አይነት ቦታ ተፈልጎ (ወል መሬት ) እንዲሰፍሩ በማድረግ አዲስ በሚመሠረተው ሰፈር መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ ማድረግ እና ሰው አሳምኖ ወደተዘጋጀው ቦታ ለመውሰድ ክልሉ ይሄንን ችግር ለመፍታት ሀገራቀፍ ንቅናቄ እንዲፈጠር እና አስፈላጊ በጀት እንዲመደብ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ ማቅረብ ያስፈልጋል ብለዋል። Wolaita Times
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ