1723138818757

የAGRA ቦርድ ሰብሳቢ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፓውል ካጋሜ ጋር ተወያይተዋል።

እ.ኤ.አ. ከመስከረም 2 እስከ 6 ሊካሄድ በተያዘው አመታዊ የአፍሪካ የምግብ ስርዓት (ኤኤፍኤስ) ፎረም በተመለከተ የኢትዮጵያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአረንጓዴው አብዮት የአፍሪካ ህብረት (AGRA) የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና የአግአራ ፕሬዝዳንት ዶክተር አግነስ ካሊባታ ከሩዋንዳው ፕረዚዳንት ጋር ተወያይተዋል።

በኪጋሊ የሚካሄደው የዘንድሮው ፎረም “ፈጠራ፣ ማፋጠን እና ልኬት፣ የምግብ ስርዓት ለውጥን በዲጂታል እና የአየር ንብረት ዘመን ማድረስ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን በአፍሪካ ግብርና ላይ ያሉ ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ የአፍሪካን የምግብ ስርአቶች ወደ ፊት ለማራመድ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስዱ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። Wolaita Times