1000015037

“ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ስምምነቱን ደምስሶታል፥ ድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል” ሲሉ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከፍተኛ የሆነ መከፋፈል የፈጠረውን እና በምርጫ ቦርድም እውቅናን የተነፈገውን አወዛጋቢ ጉባኤው በሊቀመንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ቡድን እየተካሄደ ሲሆን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ባልተገኙበት በመቀሌ እየተካሄደ ይገኛል።

በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ጉባኤውን መጀመሩ ይፋ በተደረገበት በዚህ ሰዓት ላይ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አጭር ግን ጠንካራ መልእክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰራጭተዋል።

በዚህም “በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ አገር የሚመራው በህግና በስርዓት ነው” በማለት “ህግና ስርዓት ከማንኛውም ሰው፣ ተቋም፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ ቡድን፣ ስብስብ በላይ ነው። “ያሉት ለገሰ (ዶ/ር)” እነዚህ ሁሉ ከህግ እና ስርአት በታች ናቸው፤ ህግና ስርዓትን አክብሮ የማይንቀሳቀስ የትኛውም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግቡ ጥፋት ነው” ሲሉ ጠቁመዋል።

ለገሰ (ዶ/ር) ፥ “የህወሓት ያለፉት ዓመታት የግትርነት ባህሪም የዚሁ ምሳሌ ነው “ያሉ ሲሆን” ህወሓት ደጋግሞ እንደመሸሸጊያ የሚያነሳው የፕሪቶሪያ ስምምነት የፌደራል ተቋማትን አሰራሮች፣ ህጎችና አካሄዶች በጥብቅ ሊያከብር ግዴታ ጥሎበታል” ብለዋል።

“ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር ደምስሶታል፡፡” ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

“ድርጊቱ የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል፡፡” ያሉት ለገሰ (ዶ/ር)” አንዴ፡ ሁለቴ፡ መሳሳት ያለንና የነበረ ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ተመሳሳይ ስህተት ሶስቴ መፈጸም ግን የመጨረሻው የጥፋት መንገድ ነው” ሲሉም አክለዋል።

“ለዚህ ደግሞ ብቻኛ ተጠያቂ እራሱ (ህወሓት) ይሆናል” በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት፦ ህወሓት በአመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ መከፋፈል የፈጠረውን እና በምርጫ ቦርድም እውቅናን የተነፈገውን አወዛጋቢ ጉባኤ መክፈቻ እያካሄደ መሆኑ ተነግሯል።

ጉባኤው በሊቀመንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ቡድን እየተካሄደ ሲሆን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ” ጉባኤውን አንሳተፍም ” በማለታቸው አልተገኙም።

ሊቀ መንበሩን ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ፣ አዲስዓለም (ዶ/ር)ን ጨምሮ በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙትን አመራሮች መገኘቱ ተገልጿል። Wolaita Times