1000015073

በዎላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ለወራት መከፈል ባለመቻሉ ዋና አስተዳዳሪውን ጨምሮ ሌሎችም ስልጣን ለቀዋል።

“ደመውዝ ተከፍለው እንኳን ኑሮ ውድነትን መቋቋም ባልቻልንበት ወቅት ደመውዝ ተከልክለን ተረስተናል” ሲሉ በተለያዩ መዋቅር እየሰሩ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም ቅሬታ አቅርበዋል።

በዞኑ የሆቢቻ ወረዳ የሶስት ወር ደመውዝ ባለመከፈሉ ምክንያት የተቆጡ መንግስት ሰራተኞች በወረዳው አስተዳዳሪ ቢሮ ዘልቀው በመግባት ዘግተው ከቢሮ እንዳይቀሳቀስ እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ስያግቱ የተፈጠረውን ነገር ወረዳው መቆጣጠር ባለመቻሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፓሊስ ሄደው አከባቢውን ለጊዜው ስያረጋጉ የወረዳው አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ማዕረጉ አስራት በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈገ የወረዳው መንግስት ሰራተኛ ገልጸዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ዋና አስተዳዳሪው የኃላፊነት መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለዞኑ አስተዳደር እንዲሁም ለዞኑ ፓርቲ ፅህፈት ቤት ማስገባቱን ከምንጮቹ አረጋግጧል።

አንድ ለሁኔታው ቅርበት ያለው አመራር የአስተዳዳሪው ኃላፊነት መልቀቂያ “ሌላ የገቢ አማራጭ የሌላቸው መንግስት ስራተኞች የሰሩበትን ደመወዝ ለወራት አጥተው ሲቸገሩ፤ ቤተሰቦቻቸውን አደጋ ላይ ጥለው በሚኖሩበት ወቅት እንዲሁም እንደ አመራር የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ በጊዜ እንዲከፍል ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በተደጋጋሚ ያቀረብነው አቤቱታ ምላሽ ባለማግኘቱ መፍትሔ በሌለበት አልቀጥልም” በሚል ገልፀው ማሳወቁን አስረድተዋል።

በተመሳሳይ ዜና “ለመንግስት ሰራተኛ በግዜ ደመወዝ ባለመክፈሉ ምክንያት ስልጣን በገዛ ፍቃድ ስለለቀኩ ቀጣይ ለሎች እንድማሩበት በይፋ ለህዝብ እንዲገለፅ” በሚል የኦፋ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰልጣኝ አበራ የተባለ ግለሰብ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በላከው መልዕክት ገልጸዋል።

የደሞዝ ክፍያው መዘግየት በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየደረሰባቸው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የተናገሩት አንድ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ የሚሰራው አስተያየት ሰጪው በአብዘኛዉ መዋቅሮች ደመወዝ በጊዜ ባለመከፈሉ በዝህ የኑሮ ዉድነት የቤት ክራይ፣ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ እንዲሁም የቀለብ መግዣ በማጣት እየተቸገሩ እንደሆነ በመግለፅ የከፋ ጉዳት ከመድረሱ አስቀድመዉ ምላሽና ትኩረት እንዲሰጥበት” ሲሉም አክለው ጠይቀዋል።

“በአሰራር ጉድለት ምክንያት ደሞዝ እየተከፈለን አይደለም፤ ተቆራርጦ የሚገባ ደሞዝም በፈረቃ እየቀረበ ነው፤ ደመወዝ የሚሰጥበት ወር ገደብ ቢያልፍም እስከዛሬ ድረስ የመንግስት ሠራተኛ ደመውዝ ተከፍለው እንኳን ኑሮ ውድነትን መቋቋም ባልቻለበት ወቅት ደመውዝ ተከልክለን እኛ ተረስተናል” ሲሉ በተለያዩ መዋቅር እየሰሩ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ተመሳሳይ ቅሬታ አቅርበዋል።

የዞኑ መንግስት በዞኑ የተፈፀሙ ህገወጥ ቅጥሮችና የማዳበሪያ ዕዳ ይህንን ችግር ማስከተሉን በመግለፅ ሰራተኛ ሳይሆኑ ደሞዝ የሚከፈላቸው ጭምር መኖራቸው ተረጋግጦ ለማስተካከልና የደሞዝ ችግሮችንም ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው” በሚል አንድ የዞኑ መንግስት ከፍተኛ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ምላሽ የሰጠ ቢሆንም ዎላይታ ዞን በክልሉ ከፍተኛ ግብር የሚሰበሰብና የመሰብሰብ አቅም ያለው ቢሆንም በተቃራኒው ደግሞ ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች የሚመዘበር በመሆኑ ለአከባቢው ልማት ሆነ ለመንግሥት ሰራተኞችም ደመወዝ ሆነ ወደ መስክ የወጡበት ወጪ በግዜ መክፈል አለመቻሉ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ እየፈጠረ ስለመሆኑም ተገልጿል።
Wolaita Times በህብረተሰቡ ወስጥ 🙏 በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው