
ወላጅ አባትን አጥቶ እንደመኖር ያለ ከባድ ነገር የለም።
ወጣት ማብራቶም አባቱን በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ዓይኑን እንኳ ሳያይ ተለይቶ 31 ዓመታትን ያክል አሳልፏል።
አባቱ አቶ ባሳ ባልጣ ከእናቱ ጋር ብዙም ሳይቆይ ጦርነት በአከባቢው በመነሳቱ ምክንያት ወታደር ስለነበር ተለያይቶ ከጦርነቱ በኋላም ሳይገናኙ ወደ ትውልድ ሥፍራ #ዎላይታ አከባቢ ስለማቅናቱ ከወላጅ እናቱ እንደሰማ የሚናገረው ወጣት መብራቶም በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ሆላንድ ሀገር ሆኖ ስለ ወላጅ አባቱ ባሰበ ቁጥር ሠላም እንደማይሰማው ለWT ገልጸዋል።
በዚህም የሥነልቦና ጉዳት እየደረሰበት እንደሆነም ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ወላጅ እናቱ ኤርትራ ስለመኖሯን የተናገረው ፈላጊ ልጅ መብራቶም፣ አባቱ አቶ ባሳ ባልጣ በህወይት ይኑር አይኑር እንደማያውቅ ገልጾ በአባት ፍቅርና በፈጣሪ ስም አባቴ ያለበት ቦታና አድራሻ እንዲሁም ቤተሰቦቹ ያሉበትን ለጠቁመልኝ ወሮታውን ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ይላል።
በመሆኑም ከታች በፎቶ የሚትመለከቱት አቶ ባሳ ባልጣ ያገኘ ወይም ቤተሰቡን የሚያውቅ ሰው ለWT Inbox በማድረግ አልያም በ 0953750517 በመደወል መሪጃ ቢያደርሱ ወሮታውን እንከፍላለን ይላሉ በድጋሚ ልጅ መብራቶም ባሳ እና ቤተሰቦቹ።
የተነፋፈቁ ቤተሰቦች እንዲገናኙ መረጃውን በማጋራት የሰብኣዊነት ግዴታችንን እንውጣ!