
“የሻለቃ ኃይሌ እና የዶክተር አሸብር ሽኩቻ ከአትሌቲክስ ባሻገር ነው” በሚል ተጨባጭ መረጃዎች እና ሰነዶች አረጋግጠዋል።
ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በራሽያ የህክምና ትምህርቱን ከመከታተሉ ባሻገር እዛው ሩሲያ ሀገር ጭምር የህክምና ተቋም ያለው እንደሆነ ይወራል።

ግለሰቡ ሀገር ቤት ዶን ዴንታል የጥርስ ህክምና እንዳለው የሚታወቅ ሲሆን ባለፉት በርካታ ዓመታት ሙያውን የተወ በሚመስል መልኩ በሀገሪቱ ፖለቲካ እና ስፖርት ዘርፍ ዘልቆ በመግባት “የበርካቶችን ቅስም የሰበረ ሀይ ባይ ያጣ ግለሰብ” እንደሆነ በቅርበት የሚያውቁ ይመሰክራሉ።
ዶክተር አሸብር በትውልድ ስፍራው ካፋ አካባቢ ያለውን ተፈጥሯዊ ሀብትን በቤተሰብ ሰንሰለት በኢንቨስትመንት ስም ለመዝረፍ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ባለበት ወቅት ነው ሻለቃ ኃይሌ እዛ አካባቢ መካናይዝድ እርሻ ወደ መሥራት እንደገባ መረጃው ደርሶናል።
ዶክተር የኃይሌን እንቅስቃሴ ባለመውደዱ የቡናና የሌሎችም እንቨስትመንት ሥራው በተደጋጋሚ እንቅፋት እንዲያጋጥመው በባለስልጣናት በኩል እየሠራ እንደቆየ ለማወቅ ኃይሌ በግልጽ ባይሆንም በተደጋጋሚ ለሚዲያዎች የገለፀባቸው አጋጣሚዎችን ማስታወስ እንደሆነ እኚህ የመረጃ ምንጩ ገልጸዋል።

በተለይም ሩሲያ ለትምህርት በቆየሁባቸው ጊዜያት “የኬጂቢ የስለላ ድርጅት አባል ሆኜ እንዳገለግል ተመርጫለሁ” በማለት በትውልድ አካባቢው ከተራው ግለሰብ እስከ ትላልቅ ባለሥልጣናት እሱ የሚለውን ብቻ እንዲከውኑ አስቀድሞ የህዝቡን አስተሳሰብና አቅጣጫ ቀይሮ ነው የተቀመጠው ሲሉ ለረጅም ጊዜ የሚያውቅ አንድ የትውልዱ አከባቢ ግለሰብ አስረድተዋል።
ከላይ የተጠቀሱትን አካባቢዎች ለመበዝበዝ በሚያደርገው ጥረት በቀድሞው የደቡብ ክልል የነበሩ “ተሟጋች የዎላይታ ልጆች ጣልቃ ስለሚገቡ በክልል እንሁን ጥያቄ የእነዚህ አካባቢ ተወካዮች ሳይፈልጉ ከአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ አደረጃጀት መደራጀት እንደማይፈልጉ ለመንግሥት ጥያቄ እንዲያቀርቡ” በሚል ለተወካዮች ከአንድ መቶ ሺህ ጀምሮ እስከ ሚሊየን ብር በቼክ ጽፎ እንደሰጠ በወቅቱ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ይፋ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።
“ተስፋዬ” የሚባልና በራሱ በዶክተር አሸብር የህክምና ፍቃድ ክሊኒክ ከፍቶ በሚሠራ ባለሀብት ወንድም በኩል ደንና የደን ምርቶችን እና የዱር እንስሳትን ከአካባቢው በከፍተኛ ሁኔታ በህገወጥ መንገድ ሲያሸሽ እንደነበር እንዲሁም ወንድዬ ኮንታ የሚባል ዘፋኝ ዶክተር አሸብር ለገንዘብ ካለው አደገኛ ፍቅር የተነሳ የካፋ፣ የዳውሮና የኮንታን የተፈጥሮ ሀብት ለመበዝበዝ እንዲመቸው ከሠራቸው ሥራዎች አንድ ሚዲያ ላይ ቀርቦ ይህችን በመናገሩ ወደ ትውልድ አካባቢው እንዳይገባ ያስደረገውም ዶክተር አሸብር እንደሆነ ምንጮች አረጋግጧል።
ሻለቃ ኃይሌ እጅግ ዘመናዊ የቡና እንቨስትመንት ከጀመረ በኋላ ለማዕከላዊ መንግሥት አንዳንድ መረጃዎች መድረስ መጀመሩ ያላስደሰተው ዶክተር አሸብር በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ላይሻር የነገሰውን ብርቅዬ አትሌት የገባበት ገብቶ ማሳደድ የጀመረውም ከዚህ ጋር በተያያዘ እንደሆነም የመረጃ ምንጩ አክለው ጠቁመዋል።
ሁለቱም ወገኖች ይፋ አላደረጉም እንጂ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከአካባቢው ባገኘው ተጨባጭ መረጃ እና ኃይሌ በተለያዩ ጊዜያት ስለ እንቨስትመንቱ ሲያነሳ ከሚጠቀማቸው አገላለጾች ግጭታቸው የስፖርት ወይም አትሌትክስ ብቻ ሳይሆን እነዚህንና ሌሎችንም የጥቅም ግጭቶችን የያዘ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል።
ማሳሰቢያ፦ ስለግለሰቡ ካገኘነው በርካታ መረጃዎች በጥቂቱ ለዛሬው ያቀረብነው ሀገራዊ ፋይዳ ባለው ጉዳዮች ላይ እንደፈለገ ጠልቃ እየገባ በሚያደርገው አካሄድ ከግለሰቦች ጀምሮ የሀገር ጥቅም እስከመንጠቅ የደረሰ ጉዳት እንዲከሰት ምክንያት በመሆኑ ሁሉም እንዲያውቅ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው🙏