1000015444

የክልሉ የፖለቲካ እና የአመራር ብልሽት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የፀጥታ ራስ ምታት እንዲሁም ህዝባዊ የመልካም አስተዳደር ቁጣ የሚያስነሳ ከፍተኛ አዝማሚያዎች እንዳሉ ምሁራን አሳስበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በርካታ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ያሉበት የብዝሐ ብሔር፣ ባህል፣ ቋንቋ ታሪክ ያለው ክልል ቢሆንም “የፌዴራል መንግስት በቂ ትኩረት ባለማግኘቱ የተወሳሰበ ችግር እየተከሰተ ስለሆነ በአፋጣኝ ካልታረመ ለወደፊቱም ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ሊገባ ይችላል” በሚል የአከባቢውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በንቃት የሚከታተሉ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችና የገዥው ፓርቲ አባላት ሆኑ የመንግስት ሠራተኞችም ይገልፃሉ፡፡

ይህ ክልል የቀድሞ ደቡብ ብ/ብ/ሕ/ ክልላዊ መንግሥት በአራት ቦታ ሲከፈል ከተመሠረቱ ክልሎች አንዱና ወደ 15 ሚሊዬን የሚጠጋ ሕዝብ ያለበትም ክልል ሲሆን እንደ ምሁራኖች ገለፃ ይህ ክልል ከመመስረቱ በፊት በአከባቢው በርካታ ፖለቲካዊ እና የአደረጃጀት ጥያቄዎች በከፍተኛ ሁኔታ ሲነሱበት የነበረ ከልል መሆኑ በአሁኑ ወቅት የአመራሮች ሽኩቻ ታክሎበት በአካባቢዎቹ ተጨማሪ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እያስነሳ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ከአደረጃጀት ጥያቄዎቹ መካከል የዎላይታ ሕዝብ ሲጠይቅ የነበረው በክልል የመደራጀት ጥያቄ ግንባር ቀደም ሲሆን ሌሎች በርካታ የብሔር ማንነት ጥያቄ፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎች የነበሩበት ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከነበሩት ነባር ችግሮችና ጥያቄዎች በተጨማሪ በአደረጃጀት ሂደቱ ላይ የነበሩ ጉልህ ስህተቶችና ክልሉ ከተደራጀም በኋላ እየተፈፀሙ ያሉ የመልካም አስተደዳር ጉድለቶች፣ የሥልጣን ላይ ብልግና፣ የሕግ የበላይነት መጥፋት፣ የክልሉ አስተዳደር ወሳኔዎች መርህ የለሽ መሆን፣ በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፋው ሙስና እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ክልሉን ለመፍረስ አደጋ ከመጋረጣቸው በላይ አሁን ላይ ሀገሪቱን በአንዳንድ ከልሎች እየገጠማት ከሚገኘው አይነት የፀጥታና የፖለቲካ ችግር ተጨማሪ ራስ ምታት ወደ መሆን እየደረሰ ይገኛል፡፡

በክልሉ ያሉ ችግሮች ዋናዎቹ፦ የክልሉ ማዕከል ከተሞችን በመወሰን ሂደት የተፈጠሩ ከፍተኛ ሽኩቻዎችና እነዚያ ሽኩቻዎች የፈጠሯቸው ተቃርኖዎች ሳይወገዱ በችኮላ ወደ ክልል ምስረታ መገባቱ እንዲሁም የክልሉ ማዕከል ከተሞች መብዛትና የክልሉ ቢሮዎች ተበታትነው በመገኘታቸው በሕዝቡ፣ በክልሉ ሠራተኞች ያስከተለው እንግልትና ከፍተኛ የሆነ የበጀት ብክነት ይጠቀሳሉ።

በተጨማሪም የክልሉ መንግስት መቀመጫ ከተማ በውል ለይቶ ያለ ማስቀመጥና በክልሉ ህገ-መንገስትም ጭምር የሚታየው ብዥታ “የክልሉ መንግሥት መቀመጫ በሆቴል ነው ወይስ ዎላይታ ሶዶ?” (የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት በአርባምንጭ ፓራዳይ ሎጅ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል”
በሚል በህጋዊነት ላይ ጥያቄ ያነሳሉ።

በክልሉ ምላሹ ባላገኙ የአስተዳደር እና የማንነት ጥያቄዎች ምክንያት እየተፈፀሙ የሚገኙ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ( በቁጫ፣ በሻራ አከባቢ፣ በዛይሴ፣ በቦሮዳ ወዘተ እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎች፣ የዘፈቀደ እስራት እና መፈናቀል) እንዲሁም በክልሉ ሀብት የሚያስተዳድሩ ቢሮዎችን በመደልደል ሂደት የተፈጠሩ አድሏዊና ግልፅነት የጎደላቸው አሠራረሮች ጎልተው መታየታቸው የክልሉን ዕጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ማነቆ እየፈጠሩ የሚገኙ ውስብስብ ችግሮች እንደሆነም
አብራርተዋል።

በክልሉ በጉልህ እየታየ የሚገኘው የፖለቲካ ሥልጣን ክፍፍልና የአኮኖሚ ተጠቃሚነት ኢፍትሐዊነት፤ የክልሉ አስተባባሪ አካላት ለሁለት በመሰንጠቅ ጎራ ተለይቶ መካረር መጀመሩ እና ይህም እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ መዝለቁ እንዲሁም ሰሞኑን የክልሉ ከፍተኛ አመራር በዎላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ ባለው አንድ ሆቴል ላይ ከህዝብና ከመንግሥት የተጣለበት ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ያሳየው አይነት ስነምግባር የጎደለው አዝማሚያዎች ለሌላኛው እንቅፋት እንደሆነም አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ከፍተኛ የሆነ ሙስና እና የሕዝብ ሀብት ዝርፊያ፦ እስከ ፌዴራል ባለሥልጣናት ተዋናይ እንደሆኖቡት የሚጠረጠረው ከጥቂት ዘራፊ ባለ ሀብቶች ጋር በመመሳጠር በፕሮጀክቶች፣ ከድንጋይ ከሰልና ከሌሎች ማዕዳናት፣ የእርሻ መሬትና የከተማ መሬት ምዝበራ፣ የሆቴል መስተንግዶዎች ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ አሻጥሮች የክልሉ ዋናዎቹ የልማት ፀረ ራስ ምታት እንደሆኑም አክለዋል።

የተጠቀሱ ችግሮችን በተመለከተ ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተጨባጭ መረጃዎች ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች የደረሱትን ጨምረው ይሄንን ሁሉ ችግር ተሸክመው በየቦታው የአመራር ግምገማ እያደረገ በሚገኘው በእያንዳንዳቸው አንኳር ጉዳዮች ላይ ትንታኔ የሚያቀርብ ሲሆን የዝግጅቱ ዓላማውም ችግሮቹ ተባብሰው በአከባቢው ውስብስብ ቀውስ ከመፍጠራቸው በፊት የሚመለከተው አካል፥ በተለይም የፌዴራሉ መንግሥት የእርማት እርምጃ እንዲወስድና ሕዝቡም ችግሮቹ የሚከሰትባቸውን ሁኔታ ተገንዝቦ በአከባቢው የተረጋጋ ሁኔታ እንዲፈጠር አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ለማሳውቅ ብቻ መሆኑን በድጋሚ ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ #WolaitaTimes #Ethiopia

በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው