
“ለህወሓት ቡድናዊ ጥቅም ሲባል በህዝብ ላይ ዳግም ቁማር መጫወት ቆመው ሁሉንም የፓለቲካ ሃይሎች ያቀፈ መንግስት በአስቸኳይ መመስረት ያስፈጋል” – ሦስት የፓለቲካ ፓርቲዎች
ከፍተኛ የሆነ መከፋፈል የፈጠረውን እና በምርጫ ቦርድም እውቅናን የተነፈገውን አወዛጋቢ ጉባኤው በሊቀመንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ቡድን ሲሆን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ባልተገኙበት በመቀሌ እየተካሄደ በሚገኘው ዙሪያ ሦስት የፓለቲካ ፓርቲዎች መግለጫ ሰጥቷል።

በትግራይ የሚንቀሳቀሱት ባይቶና፣ ሳወት፣ ናፅነት የፓለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ “ሳምንቱን በስርዓቱ ባለቤቶች መካከል በመካሄድ ያለው ህገ-ወጥ እንቃስቃሴና ፍጥጫ ተው መባል ይገባዋል” ብለዋል።
በህወሓት አመራሮች የተፈጠረው ፍጥጫ ተከትሎ በህዝቡ የሚታየው መረበሽ ያወገዙት ሦስቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች “ህግ እየጣሱ በህዝብ ካባ ስም ለመደበቅ የሚደረገው መሯሯጥ እናወግዛለን” ሲሉ ገልጸዋል።
“ለቡድናዊ ጥቅም ሲባል በህዝብ ቁማር መጫወት መቆም አለበት” ያሉት ፓርቲዎቹ “ደርጅታዊ ይሁን ቡድናዊ ጉዳይ ከህዝብ ህልውና ማጣበቅ እንፀየፈዋለን እንዲቆምም እናሳስባለን” ብለዋል።
“የህዝብ ሰላም፣ ህልውናና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ህገ-ወጥ ፓለቲካዊ ተግባር ሲታይ የሚመለከተው የፀጥታ አካልና ህዝብ ያለማዳላት በአስቸኳይ የማስቆም ሃላፍነቱን መወጣት አለበት” ሲሉም ገልጸዋል።
“የተፈጠረው ፓለቲካዊ አለመረጋጋት ዋነኛ መፍትሄው ሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት መንግስት በአስቸኳይ መመስረት ነው” የሚል የመፍትሄ ሀሳብ አቅርበዋል።
ፓርቲዎቹ፤ ሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት መንግስት በአስቸኳይ የመመስረት ጥሪ በተደጋጋሚ ማቅረባቸውና ግን ሰሚ አለማግኘታቸው አመልክተዋል ሲል ቲክቫሃ ዘግቧል።
“ህወሓት በተጨባጭ ስምምነቱን ደምስሶታል፥ ድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል” በማለት በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ጉባኤውን መጀመሩ ይፋ በተደረገበት ቀን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አጭር ግን ጠንካራ መልእክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰራጭተው ነበር።
ህወሓት በአመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ መከፋፈል የፈጠረውን እና በምርጫ ቦርድም እውቅናን የተነፈገውን አወዛጋቢ ጉባኤውን “ድርጊቱ የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል፡፡” ያሉት ለገሰ (ዶ/ር)” አንዴ፡ ሁለቴ፡ መሳሳት ያለንና የነበረ ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ተመሳሳይ ስህተት ሶስቴ መፈጸም ግን የመጨረሻው የጥፋት መንገድ ነው” ሲሉም አክለዋል። #Tigray #TPLF #Ethiopia