
በመላው ዎላይታ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ለወራት መከፈል ባለመቻሉ የተቋውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያካሂዱ እንደሆነ ተገልጿል።
“ደመውዝ ተከፍለው እንኳን ኑሮ ውድነትን መቋቋም ባልቻልንበት ወቅት ደመውዝ ተከልክለን መኖራችን በአደባባይ መታወቅ ስላለበት የተቋውሞ ሰልፍ አስፈልጓል” ሲሉ ኮሚቴው አሳውቋል።
የደሞዝ ክፍያው መዘግየት በመንግስት ሰራተኞች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየደረሰባቸው እንደሆነ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የተናገሩት የሰልፉ አስተባባሪዎቹ በአብዘኛዉ መዋቅሮች ደመወዝ በጊዜ ባለመከፈሉ በዝህ የኑሮ ዉድነት የቤት ክራይ፣ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ እንዲሁም የቀለብ መግዣ በማጣት እየተቸገሩ እንደሆነ በመግለፅ የከፋ ጉዳት ከመድረሱ አስቀድመዉ ምላሽና ትኩረት እንዲሰጥበት” ያለመ ሰልፍ እንደሆነም ኮሚቴው ጠቁመዋል።
“በአሰራር ጉድለት ምክንያት ደሞዝ እየተከፈለን አይደለም፤ ተቆራርጦ የሚገባ ደሞዝም በፈረቃ እየቀረበ ነው፤ ደመወዝ የሚሰጥበት ወር ገደብ ቢያልፍም እስከዛሬ ድረስ የመንግስት ሠራተኛ ደመውዝ ተከፍለው እንኳን ኑሮ ውድነትን መቋቋም ባልቻለበት ወቅት ደመውዝ ተከልክለን መኖራችን በአደባባይ መታወቅ ስላለበት የተቋውሞ ሰልፍ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል” ሲሉም ኮሚቴው አብራርቷል።
በመሆኑም በዞኑ በሁሉም መዋቅር የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የተቋውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም አስተባባሪዎቹ ገልፀው የተቋውሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ኮሚቴው ቀኑንና ተያያዥ ጉዳዮችን አመቻችቶ በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚያሳውቁ በላኩልን መረጃ ጠቁመዋል።
የዞኑ መንግስት በዞኑ ችግር መኖሩን አምኖ ለማስተካከልና የደሞዝ ችግሮችንም ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው” በሚል አንድ የዞኑ መንግስት ከፍተኛ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ምላሽ የሰጠ ቢሆንም ዎላይታ ዞን በክልሉ ከፍተኛ ግብር የሚሰበሰብና የመሰብሰብ አቅም ያለው ቢሆንም በተቃራኒው ደግሞ ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች የሚመዘበር በመሆኑ ለአከባቢው ልማት ሆነ ለመንግሥት ሰራተኞችም ደመወዝ ሆነ ወደ መስክ የወጡበት ወጪ በግዜ መክፈል አለመቻሉ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ እየፈጠረ ስለመሆኑም ተገልጿል። #WolaitaTimes #Ethiopia
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው