በዎላይታ ዞን ካሉ ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ካምፎውርድ ትምህርት ቤት ያውቃሉ ?

በመላው ደቡብ ክልል ትምህርትን ያቀጣጠሉት የአቶ ቦጋሌ ዋሌሎ ዎላይታ ዞን የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ነዋሪዎች ለበርካታ ዘመናት ለተቸገሩበት ጥራት ያለውና አቅምን ያገናዘበ ጥራትን የጠበቀ የግል ትምህርት ቤት እጦት በግለሰብ ጥረት መፈታት የጀመረው የዛሬ 18 ዓመት በካምፎውርድ “ስኩል ኦፍ ኤክሴለንስ” በሚል መሆኑን ከአከባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትምህርት ቤቱ በተለያዩ በጎ ተግባር በሚታወቀው በአከባቢው ተወላጅና የሼፕ ኢትዮጵያ አለምአቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና መሪ በሆነው እንጂነር ደሳለኝ ዳካ የተመሰረተው ትምህርት ቤቱ በ1998 ዓ.ም በ5 መምህራን 155 ተማሪዎችን በመቀበል ሀ ብሎ የጀመረውን የመማር ማስተማር ስራ ዛሬ ላይ ከ50 በላይ ታዋቂ መምህራን በየዓመቱ ከ852 በላይ ተማሪዎችን በቅድመ መደበኛ እና በመደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጭምር ለማስተማር የጀመረ በአከባቢው ተመራጭ መሆኑንም ከህብረተሰቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ካምፎውርድ ት/ቤት ዘንድሮ በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ ሁሉንም ተማሪዎች ያሳለፈ ሲሆን ከፍተኛ = 99.98 ዝቅተኛ = 94.46 በማስመዝገብ 42ቱም ተፈታኞች ወደ ዘጠነኛ ክፍል ማዛወሩን የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ማቴዎስ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጠዋል።
በዚህም ትምህርት ቤቱ ያስፈተናቸውን ሁሉንም ተማሪዎችን በከፍተኛ ቁጥር ውጤትን በማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ክፍል ማሳለፍ የቻለ ሆኗል።

ትምህርት ቤቱ ከአምናው ውጤት አንፃር ሲታይ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት ሲሆን ለምሳሌ የአምናው ዝቅተኛው 88.06 ሲሆን የዘንድሮው ዝቅተኛ 94.46 ነው። የአምናው ከፍተኛ 99.63 ሲሆን የዘንድሮው ከፍተኛ 99.98 ነው። የአምናው ተፈታኞች ቁጥር 23 ሲሆን የዘንድሮው ከአምናው በእጥፍ እንደሚበልጥም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ከአምናው ልዩነቱ እጂግ የጎላ መሆኑ ትምህርት ቤቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተማሪዎች ውጤት መሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ በመሰራቱንና አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ልዩ ክትትል በማድረጉ የመጣ ስለመሆኑም አስረድተዋል።
ለዚህ ውጤታማነት ዋነኛ ምክንያት የሆኑትን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት እንዲሁም አጠቃላይ የወረዳውን መንግስት በተማሪዎች፣ በወላጅ/አሳዳጊዎች እና መምህራን ስም በማመስገን ትምህርት ቤቱ ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ በመስጠት በዞኑ አልፎ በክልል ደረጃም ተወዳዳሪ ለመሆን ከምንጊዜውም በላይ እየተጋ እንደሆነ በመግለፅ የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ከሊቃ አንጻር ትምህርት ቤቱ በዞኑ ቅርብ ተፎካካሪ ነው፣ ሊቃ ከአጠቃላይ ዞኑ መርጦ ወስዶ ነው የሚያስተምራቸው፤ ነገር ግን ኮምፎውርድ ከታች ኮትኩተው አብቅቷቸው ነው ይህንን ያህል ነጥብ ያስመዘገበው፥ ሌላው የሚገርመው ሊቃ ያስፈተነው 39 ብቻ ሲሆን የኮምፎውርድ 42 ናቸው። ይህ ጉዳይ ሊቃ የሕዝብ ሆኖ ተደራሽነቱ ላይ እጂግ ውስን መሆኑና ስለተደራሽኑቱ የሚመለከታቸው አካላት መስራት እንዳላባቸው ይጠቁማል።
የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ያስፈተናቸዉን 39 ተማሪዎችንም ወደ 9ኛ ክፍል አዛዉሯል፤ ከፍተኛዉ አማካይ ዉጤት 96.55 ሲሆን ዝቅተኛዉ 81.43 ሆኖ መመዝገቡን ከትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አጠቃላይ በዎላይታ አምና 14.3% የነበረው ዞናዊ አማካይ መጠነ ማሳለፍ ምጣኔ ዘንድሮ ወደ 54.79% ከፍ ያለ ሲሆን ዘንድሮ በዞኑ በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተፈተኑት ወንድ፡ 16,731፣ ሴት፡ 18,317፣ ድምር፡ 35,048 ተማሪዎች መካከል ከ50% እና በላይ የማለፊያ ውጤት ያመጡት ወንድ: 9,666 (57.77%)፣ ሴት፡ 9,537 (52.07%)፣ ድምር፡ 19,203 (54.79%) እንደሆነ ከትምህርት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በደቡብ ኢትዮጵያዊ ክልል 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ 129,384 ተማሪዎች መካከል 50% የማለፊያ ውጤት ያመጡት ብዛት 42.57% ሲሆን ከ1,787 ት/ቤቶች ውስጥ 165ቱ ምንም ተማሪ አላሳለፉም። #WolaitaTimes #Ethiopia
በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው