
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዎላይታ ብሔር የሚጠቀምበት የራሱ የዘመን አቆጣጠር (Calendar) ያለው ሲሆን የጊዜ አቆጣጠርም በጨረቃና በፀሐይ የሚሰላ እንደሆነ ጥናቶች ቢጠቁሙም ከጥንት ጀምሮ በጨረቃ እንደሚቆጠር ብዙ ታሪካዊ ሰነዶች ያረጋግጣሉ።
ጊፓታ ደግሞ የዎላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል ነው። ጊፓታ ማለት የመጀመሪያ አዲስ አመት ወር ነው። ጊፓታ በዎላይታ ብሄር አቆጣጠር መሠረት የሚከበረው ከመስከረም 14_20 በሚውለው ዕሁድ ይሆናል።
ስለ ዎላይታ ጊፓታ አከባበር ሂደት በተመለከተ በርካታ ገላጭ ሰነዶች/ኦዲዮ-ቪዲዮዎች መኖራቸዉ አይካድም፡፡ ይሁን እንጂ ስለ አገርበቀል በዓሉ ማህበራዊ፣ባሕላዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች በተመለከተ ተገቢና በቂ ሳይንሳዊጥናቶች አልተደረጉም፡፡ በመሆኑም ፈርጀ ብዙ ፋይዳዎቹ በተመለከተ የግንዛቤ ክፍተት እና የትኩረት ማነስ ይስተዋላል፡፡ አልፎም ተርፎ ከግንዛቤ ዉስንነት ወይንም ከተዛባ አመለካከት የተነሳ አንዳንድ ወገኖቻችን በዓሉን ሲያወግዙት ይታያሉ፡፡
በመሆኑም በዚች አጭር መጣጥፍየበዓለ ጊፓታ ማህበራዊ፣ ባሕላዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች በተመለከተ ጥቅል ማብራሪያ በዘርፉ የተመራመሩ ረዳት ፕሮፌሰር ያብራራሉ።
ስለ ዎላይታ ጊፓታ ፈርጀ ብዙ ማህበረሰባዊ ፋይዳዎች ከማዉሳታችን በፊት በአንዳንድ አፍሪካ ማህበረሰቦች የሚከበሩ አገርበቀል በዓላት/ፌስቲቫሎች ያላቸዉን ማህበረሰባዊ ፋይዳዎች በተመለከተ ጥቂት የታተሙ አካዳሚክ አርቲክሎችን መዳስስ ጠቃሚ ሆኖ አግኝቻለሁ፡፡
የሰዉ ልጆች ባጠቃላይ በኤትኖግራፊክ ጥናቶች የሚታወቁ ማህበረሰቦች በሙሉ የሆኑ ነገሮችን ወይንም ክስተቶችን ያከብራሉ፡፡ የምዕራባዊያን ታሪክ ስነዳ ከመጀመሩ በጣም ቀደም ካሉ ዘመናት ጀምሮ እስከ ዛሬ የዓለማችን ኢንዲጂኔስ ማህበረሰቦች በርካታ የተለያዩ በዓላትን/ፌስቲቫሎችን ያከብሩ ነበር ( Blessing Adjeketa et al፣ 2024) ከአፍሪካ ማህበረሰቦች መካከል ህያዋንን ወይንም ቅድመ አያቶቻቸዉን ወይም የዘመን መለወጫን ወይም ሸጋ የመከር ጊዜያትን/ወቅቶች ወይም አማልዕክቶችን የሚያወሳ በዓላት የማያከብር የለም፡፡
ከዚህ የተነሳ ምሁራንና ተመራማሪዎች ( kadar and Yoa, 2004, Adekule, 2009,cited by Blessing Adjeketa et al፣ 2024 ) አፍሪካን a festival continent” [a continent of indigenous celebration] (ብለዉ ይገልጹታል፡፡ ነገር ግን አፍሪካዊ-አገርበቀል በዓላት socio-cultural constructs ( ከእያንደኣንዱ አፍሪካዊ ማህበረሰብ ማህበራዊ-ባህላዊና ታሪካዊ ብዝሃነት ጋር የተቆራኙ መሆናቸዉን መዘንጋት የለብንም፡፡
አፍሪካዊ አገርበቀል በዓላት (ምዕራባዊያን ልህቃን ፌስቲቫል ብለዉ የሚገልጹት ፈርጀብዙ ሶሳይታል ፋይዳ ያላቸዉ መሆኑን የጥናት ዉጤቶች አረጋግጠዋል፡፡
እነኚህ አገር በቀል በዓላት አንዱ ማህበረሰብ ከሌሎቹ የሚለይበት ባሕላዊ መገለጫዎች ናቸዉ። በሌላ አነጋገር ባለቤት የሆኑ ማህበረሰቦች/ሕዝቦች የብሔራዊ ማንነት መገለጫዎች እና ብሔራዊ ማንነት መገንቢያና ማጠናከሪያ ባሕላዊ እሴቶች ናቸዉ።
በሌላ በኩል እነኚህ አገርበቀል በዓላት ባለቤት በሆነዉ ሕዝብ/ማህበረሰብ መካከል ማህበራዊ አንድነትና መተሳሰብ በመፍጠር/በማስተሳሰርና በማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።
በተጨማሪም እነኚህ አገርበቀል በዓላት interpersonal, intrafamily interfamily, interclan ሰላምና ዕርቅ የመገንባት ሚና ይጫወታሉ። አገርበቀል የአፍሪካ በዓላት የባሕል ተሃዲሶ መሣሪያ በመሆን ያገለግላሉ።
አልፎም ተርፎ አገርበቀል/ቱባ በዓላት በተለይም ከ1980ዎቹ ጀምሮ የዓለማቀፍ ኤትኖቱሪዝም መዳረሻ በመሆን ለሕዝባቸዉ የቱሪዝም ገቢ ምንጭ በመሆን ያገለግላሉ።

የበዓለ ጊፓታ ፈርጀ ብዙ ፋይዳዎች
1/ፖለቲካዊ ፋይዳዎች
መላዉ የዎላይታ ሕዝብ ከጥንት-ጥንት ዘመናት ጀምሮ ጊፓታንlavishly ሲያከብር እንደነበር በርካታ የተለያዩ መጣጥፎች፣ oral traditions including folklores አረጋግጠዋል። ጊፓታ ለመላዉ የዎላይታ ሕዝብ (ለድሃው ለሀብታሙ) ብሎም ለቤትና ዱር እንስሳት ጭምር የደስታና ፌሽታ ባሕላዊ ኩነት ከመሆኑም በላይ የዎላይታ/ የዎላይቱማ ልዩ ባሕላዊ እሴት ነዉ። የዎላይታ ብሔራዊ/ባሕላዊ ማንነት መገለጫ ምልክቶች/ማጠናከሪያ እሴቶች አንዱ ነዉ። መጠሪያ ስሙም የዎላይታ ጊፋታ ነዉ። የዎላይታን ብሔራዊ/ባህላዊ ማንነት ከጊፓታ በዓል ነጥሎ መመልከት አዳጋች ነዉ።
2ኛ/ ማህበራዊ ፋይዳዎች
የጊፓታ በአል ማክበር በግለሰቦች/በቤተሰብ አባላት/በጎሳዎች/ጎረቤቶች መካከል ማህበራዊ አንድነትን ትስስርን መተሳሰብን በመፍጠርና በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
በዓለ ጊፓታ ለማክበር በተለያዩ አከባቢዎች ተበታትነዉ በተለያዩ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ወጣቶች፣ ትዳር መስርተዉ የሚኖሩ ዎላይታዎች ከነቤተሰቦቻቸው (ከአቅም በላይ የሆነ ችግር እስካልገጠማቸዉ ድረስ ወደ ትዉልድ መንደራቸዉ ይመጣሉ።
አብዛኛዎቹ ለቤተሰቦቻቸዉና ለወዳጆቻቸዉ ለበዓሉ ፍጆታ የሚዉሉ ቁሳቁሶችን/ እና አልባሳትን ገዝተዉ ይዘዉ ይመጣሉ። ከትዉልድ መንደራቸዉ ርቀዉ የሚኖሩ ወገኖች በበዓሉ መሳተፋቸዉ በእነርሱና በቤተሰቦቻቸዉ/ጓደኞቻቸዉና ጎረቤታቸዉ መካከል የነበረዉን ዝምድና፣ ወዳጅነት ማህበራዊ ትስስርና መተሳሰብ ያጠናክራል።
ከዎላይታ ራቅ ባሉ አከባቢዎች/ማህበረሰቦች መካከል የተወለዱ ልጆችና ሕጻናት ትዳርና ከወላጆቻቸዉ ጋር መጥተዉ በበዓሉ መታደማቸዉ ልዩ ደስታና ትዝታ ይፈጥርባቸዋል። ከዚህም በላይ ዎላይታንና ዎላይቱማን የማወቅ ብሎም የዎላይታ ብሔራዊ ማንነት ስሜት ይፈጥራል።
የበዓለ ጊፓታ Amuuwa, Ciishsha oittuwa oitiyoga, guuliya, wosolluwa; gaziyaa kaassa ወዘተረፈ በተሳታፊዎች መካከል ጠንካራ ወዳጅነት፣ ጓደኝነት፣ ማህበራዊ ትስስር ይፈጥራል። ያጠናክራል። በዓለ ጊፋታ public ትዕይንቶች በተለይም Gazziyaa kaassa ወጣቶች የሚተጫጩበት ጊዜ/ኩነት በመሆኑ ቋሚ ወይንም ጠንካራ interpersonal, interfamily, interclan ግንኙነት (affinal) ይፈጥራል።
በሌላ በኩል ጊፓታ በግለሰቦች፣ በቤተሰቦች፣ በጎረቤታሞች መካከል የተከሰተ ግጭት፣ ጥል፣ አለመተማመን በዉይይት የሚፈታበትና ዕርቅ የሚፈጸምበት ብርቅዬ ባሕላዊ ኩነት/ቅርስ ነዉ። በሰዎች መካከል የተፈጠረ ግጭት/ጥል በዉይይት ሳይፈታ እርቅ ሳይፈጸም የጊፓታ በዓል አይከበርም። በተለያዩ ምክንያቶች ከባሎቻቸዉ ጋር ተጣልተዉ ቤታቸዉን ትተዉ ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር የሚኖሩ ሴቶች እርቅ ፈጽመዉ በዓሉን አብረዉ ያከብራሉ።

3/ ጊፓታና የባሕል ተሐድሶ
ጊፓታ አገርበቀል እሴቶች እንግዳ ተቀባይነት፣ መከባበርና መተሳሰብ በተግባር የሚገለጥበትና የሚጠናከርበት ፌስቲቫል ነዉ። ሆሌ ለሚዘፍኑ የሚደረግ ግብዣ፣ ዘፈንና ጭፈራ ዘመን ተሻጋሪ ትዝታና ወዳጅነት ይፈጥራል።
አርቲስቲክ ቫሊዩስ-በጋዜ ጨዋታ የማህበረሰቡ ፎክሎር እሴቶች/ዘፈን/ዜማ/ጭፈራ/የሙዚቃ መሣሪያዎች cutural revival and the means to ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የሚሸጋገርበት ከዚህም በላይ በጉጉት በሚጠበቀዉ ጉሊያ ጡጌታ፣ ዎሶሎ ኬታ እና የጋዜ ጫዎታ በየጾታቸዉና ዕድሜያቸዉ ተለይተዉ የሚጫወቱ አዳዲስ ዜማዎች ዘፈኖች ፎክሎርስ ይፈበረካሉ። ፐብሊክ ትዉዉቅ፣ ትስስር እና አድናቆት የሚያገኙበት ነዉ።
✍️ ዘፈን ጭፈራ ዜማ እሴቶች ጋር ሕጻናቱ የሚተዋወቁበት /የሚለማመዱበት ትዕይንት ሲሆን ልጃገረዶች የዎላይታን ምግብ ዝግጅት የሚለማመዱበት ልዩና ድንቅ ባሕላዊ እሴት/ኩነት ነዉ።
የጊፓታ ጋዚያ ጨዋታ ብዙዉን ጊዜ አዳዲስ artistic folklores mainly new songs እና የዘፈን ግጥሞች የሚፈበረኩበትና ሥራ ላይ የሚዉሉበት ድንቅ ኩነት ነዉ። በዘፈንና ጭፈራ (performance) የላቀ ተሳትፎ ያሳዩ ግለሰቦች/ቡድኖች ከፍተኛ ሕዝባዊ አድናቆትና ዝና የሚያገኙበት ባሕላዊ ኩነት ነዉ።
4/ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ
ከዘመነ ደርግ ጀምሮ የአሟ አባላት እስከ ቀጣይ ጊፓታ ድረስ ዕቁብ መሥርተዉ ገንዘብ ይቆጥባሉ። የዕቁቡ አባላት ችግር ሲገጥማቸዉ በአነስተኛ ወለድ ገንዘብ ይበደራሉ። ይህ ለቁጠባና ብድር ተቋማት ግንባታ እንደ እርሾ ሊያገለግል ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ የዎላይታን ጊፋታ ህዝባዊነቱን እና ቱባነቱን (indignity and originality ጠብቀን በተቀናጀ መልኩ ማክበርና ማስተዋዎቅ ከቻልን ከዓለማቀፍ ኤትኖ-ቱሪዝም ገበያ ዳጎስ ያለ ገቢ ማግኘት ይቻላል። በረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ወዳጆ

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዎላይታ ብሔር የሚጠቀምበት የራሱ የዘመን አቆጣጠር (Calendar) አለው።
የዎላይታ ጊዜ አቆጣጠር በጨረቃና በፀሐይ (Lunosolar) የሚሰላ እንደሆነ ጥናቶች ብጠቁሙም ከጥንት ጀምሮ በጨረቃ እንደሚቆጠር ብዙ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ጊፓታ ደግሞ የዎላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል ነው። ጊፓታ ማለት የመጀመሪያ አዲስ አመት ወር ነው። ጊፓታ በዎላይታ ብሄር አቆጣጠር መሠረት የሚከበረው ከመስከረም 14_20 በሚውለው ዕሁድ ይሆናል።
የአንድ ቀን (24 ሰዓት) ክፍፍል
Bakkaaliyaa 12:00 AM
Maallado 12:00-1:00 AM
Guuraa 1:00-4:00 AM
Poo7o 4:00-6:00 AM
Gallaassaa 6:00-9:00 AM
Omarissaa 10:00-12:00 AM
Lenkkilenkkaa12:00-1:00 PM
Qammaa 2:00-6:00 PM
bilahiyaa 6:00-7:00 PM
henqelleelaa 6:00-8:00 PM
Hekka blahiyaa 9:00-10:00 PM
Wonttimaattaa 11:00-12:00 AM
የአንድ ወር ( 30 ቀን/በአራት ገበያ) ክፍፍል
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Koyro giya-Xuma ceggenaa ወሩ በገባ የመጀመሪያው ሳምንት
Naa”antto giya-Xeero ceggennaa ወሩ በገባ በሁለተኛው ሳምንት
Heezzantto gita-Poo7o ceggennaa ወሩ በገባ በሶስተኛው ሳምንት
Oydantto giya-Goobana የወሩ የመጨረሻው ሳምንት
የአንድ ዓመት (በአራት ወቅቶች/12 ወራት) ከፍፍል
አራት አንኳር ወቅቶች
➖➖➖➖➖
Ofinttaa (መሄር)
Boniyaa (በጋ)
Badhdheesa (በልግ)
Balgguwaa (ክረምት)
12 ወራት + ጳጉሜ
➖➖
- Gifaata➢መስከረም
- Gooluwaa➢ጥቅምት
- Baraataa➢ህዳር
- Duubbalaa➢ታህሳስ
- Shachchaa➢ጥር
- Longgiyaa➢የካቲት
- Bullaalaa➢መጋቢት
- Gabbaa➢ሚያዚያ
- Laabooshaa➢ግንቦት
- Guuliyaa➢ሰኔ
- Caljjuwaa➢ሐምሌ
- Kuushshaa➢ነሐሴ
- Nuucaa➢ጳጉሜ
Yoo yoo Gipaataa 🙏
ለዘንድሮው ለዎላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ “ጊፓታ” በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ🙏 Wolaita Times