የሲዳማ አባቶች ለቀድሞ ኢፊድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስጦታ አበረከቱ።
በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል የተመረቀው ይርጋለም የተቀናጀ አግሮ እንዱስትሪ ፓርክ በወቅቱ በአቶ ኃይለማርያም መሠረት ድንጋይ ተቀምጦ የተጀመረ ሲሆን ዛሬ ክብር የኢፊድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች በተገኙበት በይፋ ተመርቀዋል።
የሲዳማ አባቶች ለአቶ ኃይለማርያም ካበረከቱት ስጦታ በተጨማሪ ለዶክተር ዐቢይም ስጦታ መስጠታቸው ተገልጿል።