በዎላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ለረጅም ጊዜ የህብረተሰቡ መልካም አስተዳደር ጥያቄ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

የዎላይታ ዞን የዳ/ፑላሳ ወረዳ መንግስት በ2013 ዓ.ም ለመሰራት ያቀዳቸውን የተለያዩ  የመሠረተ ልማት ሥራዎችን አጠናክሮ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በወረዳው ውስጥ በተለያዩ ቀበሌዎች ለዘመናት የህዝብ መልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ በተለያዩ ምክንያት ሳይሰራ የቆየ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች አሁን ላይ በወረዳው መንግስት ጥረትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተመለሱ እና እየተሰሩ ይገኛሉ ተብሏል።

የወረዳው መንግስት በዘንድሮው በጀት ዓመት ትኩረት ሰቶ ለህብረተሰቡ እየሠራ ከሚገኘው ሥራዎች መካከል የሻንቶ ከተማ የመንታ መንገድ ዲች ሥራ በትኩረት እየተሰራ ሲሆን ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበሩና ከተለያዩ ከአጎራባች ቀበሌዎች ጋር የምያገናኝ ድልድይ ሥራዎችም በመሰራት ላይ ይገኛሉ።

በተጨማሪም በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የመንገድ ጠረጋና ጥገና ሥራ በሕብረተሰብ ተሳትፎና  በወረዳ መንግስት ጋር በመተባበር ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተሰራ ይገኛል።

በወረዳው ከንፁህ መጠጥ ወሃ ዝርጋታ በቁጥር 20 የሚደርሱ ንፁ የመጠጥ ወሃ ጉድጓድ በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሁሉም ቀበሌዎች ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጤናው ዘርፍ በቁጥር 10 የሚያህሉ ቀበሌያት በጤና ሥራ ሞዴል ለማድረግ ታቅዶ 7 ቀበሌዎችን ሞዴል ማድረግ የተቻለ ሲሆን የቀሩትን ሞዴል የማድረግ ስራና የአዴ ሻንቶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ የእናቶችና የህፃናት ህክምና ማዕከል ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል።

ዳሞት ፑላሳ ወረዳ በዎላይታ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል ለግብርና ስራ ምቹ በመሆን የተለያዩ ምርቶችን በአመት ሶስት ጊዜ ከሚያመርቱ አከባቢዎች በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

Wolaita Times ,07/07/13 ዓ.ም Sodo,Ethiopia 🇪🇹