
የነዋሪዎችቅሬታ “ሰላም ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለዘመናት ጥያቄ የነበረውን የመንገድ ሥራ ምላሽ እንዳገኘ ለማስመሰል ተሰባስበው ፎቶ ከተነሱበት ቀን ጀምሮ ምንም ስራ አልተሰራም የሚመለከተው አካል ሁኔታውን እንድከታተል እባካችሁ እንደተለመደው ለህብረተሰቡ ድምፅ ሁኑልን” ጥሪ የአከባቢው ነዋሪዎች አቅርበዋል።
በተለይም የገበያ ትስስርን በማሳለጥ ረገድ ለሀገር ዕድገትና ለዜጎች ተጠቃሚነት ጉልህ ሚና ያለው ተብሎ ለዘመናት የህብረተሰቡ ጥያቄ የነበረውን መንገድ በዎላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ከጋልዳ እስከ ቦሣ ቦርቶ ድረስ 32 ኪ/ሜ የሚሸፍን የጠጠር መንገድ ግንባታ ስራ “በሁለት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል” ተብሎ የአከባቢው ህዝብ በደስታ የጠበቁ ቢሆንም ከአመራሮቹ ፎቶ አለማለፉ ተገልጿል።

የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን በሶዶ ድስትሪክት የተጀመረው ሦስት መዋቅሮችን ያገኛል ተብሎ የ32 ኪ.ሜ መንገድ ለበርካታ ጊዜያት የመልካም አስተዳደር ችግር የነበረው መንገድ “በሁለት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ” ተብሎ ከተጀመረ ስድስት ወር ቢሆንም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊና የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ ክቡር አቶ ዘብዲዮስ ኤካ፤ የደቡብ ኢ/ክልል መንገዶች ባለስልጣን ሶዶ ድስትሪክት ኃላፊ አቶ ጳውሎስ አዋኖ እና የሌሎች አመራሮች ለዘመናት ጥያቄ የነበረውን የመንገድ ሥራ ምላሽ እንዳገኘ ለማስመሰል ተሰባስበው ፎቶ ከተነሱበት ቀን ጀምሮ ምንም ስራ አልተሰራም የሚመለከተው አካል ሁኔታውን እንድከታተል እባካችሁ እንደተለመደው ለህብረተሰቡ ድምፅ ሁኑልን”- ሲሉ ነዋሪዎች ተማፅነዋል።
የሚመለከተው አካል ለህብረተሰቡ ጥያቄ በፎቶ መሸወድ ትቶ በተግባር ተገቢ ትኩረት እንዲሰጥ እናሳስባለን። #WolaitaTimes
በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ