የትግራይ ፖለቲከኞች ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሳሰበዋል።

ዶክተር ቴድሮስ በትግርኛ ትናንት በግል ማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት የቪዲዬ መልዕክት የትግራይ ፖለቲከኞች ችግራቸውን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት በትግራይ መልሶ ማቋቋም ላይ እንዲያተኩሩ ጠይቀዋል።
የአዲሱን ዓመት በማስመልከት ዶክተር ቴድሮስ ባስተላለፉት መልዕክት “ትግራይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ትገኛለች” ብለዋል።
እንደሚታወቀው ህወሃት ከፌደራል መንግሥት ሆነ ከምርጫ ቦርድ ይሁንታና ፈቃድ ያላገኘ የተባለውን 14ኛውን ጉባኤ ማድረጉን ተከትሎ በፓርቲው እና በጉባኤው ባልተሳተፉት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች መካከል ውዝግብ ተነስቶ ቆይቷል።
ውዝግቡ እየተካተረ መጥቶም በቅርቡ የፓርቲው አመራሮች በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ቦታ እንዲሰጣቸው ዶክተር ደብረፅዮን ጠይቀዋል።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ “በክልሉ ያለ አስተዳደሩ እውቅና ምንም አይነት ስብሰባ መካሄድ የለበትም” ሲል በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ባወጡት መግለጫ “ህወሓት የውስጥ ሽኩቻውን ወደ ሕዝብ ለማስገባት እየሠራ እየሠራ ነው” ሲሉ መውቀሳቸው ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት ከዚህ በፊት የተከሰተ አይነት ጦርነት ዳግም እንዳይከሰት በህወሓት አመራሮች መካከል ባለው ሽኩቻ ህዝብ ይሁን በትግራይ ያሉ ታጣቂ ኃይሎች ከውግንና ራሳቸውን እንዲያረቁ እየወተወቱ እንደሆነ ከክልሉ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የተለያዩ ሪፓርት እንደሚያመለክተው ባለፉት 2 ዓመት ገደማ ከትግራይ ኃይሎችና የፈደራል መንግስት በተፈጠረው የፓለቲካ አለመግባባት ምክንያት ባደረጉት ጦርነት ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወት አጥቷል፣ በርካቶች ለአካል ጉዳትና ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋልጧል እንዲሁም በቢሊዮን ገንዘብ የሚቆጠር የሀገር ንብረት መውደሙ ይታወቃል። #Ethiopia #Tigray #TPLF