
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ዮ ዮ ጊፓታ።
✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ሐጋሎ ሓጋሎ።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ምናልባት በሚዲያችን ተከታታዮች ጥያቄ መሰረት በተለይ በዎላይታ ሶዶ ጉዳይ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ይዘን መጥተናል።
✅ ማሪንዶስ ጦና፦ ጥሩ ነው። ሚዲያችሁ የተከታታዮቹንም ጥያቄ የሚያቀርብ ከሆነ ትልቅነቱን ያሳያልና ተቀብያለሁ መቀጠል እንችላለን።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ፦ ሌሎች የዎላይታ ከተሞች ሆነ ዎላይታ ሶዶ ከሚኒሊክና ከኃይለስላሴ ጊዜ ጀምሮ የፖለቲካ እስረኛ እንደሆኑ ሕዝቡ ያዉቃል ብለሐል። ማስረጃ ግን አላቀረብክም ተብሏል፥ በዚህ ላይ ምን ትላለህ?
✅ ማሪንዶስ ጦና፦ እሺ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው። ዎላይታ ሶዶ እየተገባት በተደጋጋሚ ማዕከልነት በኢትዮጵያ መንግስታት ብትከለከልም በጣሊያን የአምስት አመት አገዛዝ ወቅት ከሰባቱ ክልሎች የአንዱ መቀመጫ ተደርጋ ነበረ። ከዛ በሁዋላ የሆነዉን የጀግናዉ የትምህርት ፋና ወጊ ቦጋለ ዋለሉ ልጅ፣እርሱም የቀኃሥ ፓርላማ ላይ ነፍስ ከዘሩ ሰዎች አንዱ የሆነዉ 50 አለቃ ጻዉሎስ ቦጋለ ስለ ሁኔታዉ እንደሚከተለዉ ገልጿል። “ኢጣሊያን ዎላይታ ላይ ዘመናዊ ክሊኒክ እና የጥጥ መዳመጫ ሠርቶ ነበር።
እንግሊዞች ከአርበኞቻችን ጋር ኢጣሊያንን አሸንፈዉ ሲያስወጡ ቅሌታም እንግሊዞች የጥጥ መዳመጫዉንና ሌሎችን ነቅለዉና ሠርቀዉ መኪናዎችንም ጭምር ወደ ቅኝ ግዛታቸዉ የነበረችዉ ኪንያ ጭነዉ ወሰዱ። እርግጥ አቶ ቦጋለ ዋለሉ ይህ የሕዝቡ የጦር ካሣ ነዉ አትወስዱም ብለዉ ብቻቸዉን ከእንግሊዝ ታንክ ፊት ቆመዉ አግደዉ ነበር። በግዜዉ ነፃነቱ ብቻ እንጂ ከነበረዉ ነቃተ ሕሊና መዘረፉ ያልተሰማዉ ሕዝብ አረዳቸዉም።
ከዓመት በኃላ ራስ-አደፍርሰዉ ወላይታ ሄደዉ ክሊኒኩ የነበረዉን አልጋና መሣሪያ ቆርቆሮናመዝጊያ አፍርሰዉ አንዲት ጠብመንጃ በሕዝቡ እጅ እንዳይቀር ገፈዉ በሰባት ትሬንታ ካትሮ በተባለ የጭነት መኪና ጭነዉ ወሰዱ::” ይህ ራስ አደፍርሰዉ የተባለ ነፍጠኛ ድርጊት ብዙ ትርጉም አለዉ፤ በወቅቱ በከተማዋ የነበሩ ንብረቶችን ጣራ ገንጥሎ በር ነቅሎ ወስዷል፤ ብቅ ያለችዉን ከተማ መልሶ መግደሉ ነው። ጣሊያን ጥሎ ፈርጥጦ ከእግሊዝ ዝርፊያ የተረፈም ነገር ከነፍጠኞች አያመልጥም ማለት ነዉ።
ሌላዉ ሕዝቡን ትጥቅ አስፈትቶ ሄዷል፣ በኢትዮጵያ ብዙ ቦታ ባህል እየተባለ ትጥቅ አለ በዎላይታ አይፈቀድም። ቀደምት ማዕከል ዳልቦ ደግሞ በሚኒሊክ ወረራ ወድማለች እንጂ በወቅቱ በአፍሪካ ደረጃ የምትጠቀስ ከተማ ነበረች። እናም ዎላይታ ሶዶ የፖለቲካ ትግል ማዕከል ናት፤ ሕዝቡ ለማደግና ለመሰልጠን ካለዉ ፍላጎት አንጻር ብዙ ነገሮች ላይ ቀድሞ ቢሳተፍም የኢትዮጵያ መንግስታት የሕዝብ ብዛቱንም ወደ ጎን እያሉ የሚገባትን ማዕከልነት ሲከለክለዋት ኖረዋል፥ ሕዝቡን ወደተለያዩ ከተሞች ሲያንከራትቱት ኖረዋል።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ማዕከል ዉሳኔ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ወይዘሮ አለምጸሐይ ጻዉሎስ አርባምንጭ በቀድሞ አገዛዞች አርባ ምንጭ የሰሜን ኦሞ ክፍለ ሐገር ዞን እና የጋሞ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ ስለነበረች አሁንም ዋና ከተማ መሆን አለባት የሚል መከራከሪያ ማቅረቧ ከዉስጥ አዋቂ መረጃ ወጥቶ እንደነበረ ይታወሳል። ምናልባት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በዚህ እሳቤ እየተመራ ሊሆን ይችላልና የዎይዘሮ አለምጸሐይ ጻዉሎስ መከራከሪያ ላይ ምን አስተያዬት አሎት ?
✅ ማሪንዶስ ጦና፦ በመጀመሪያ የጋንታ ጋሯ (አርባ ምንጭ) ሕዝብ ወገናችን በመሆኑ በልማቱ ደስተኛ ነኝ። ለከተማዋም መልካሙን ሁሉ እመኛለዉ። የወይዘሮዋ መመከራከሪያ ግን አይሰራም። ለምን የተነገረዉ ከዎላይታ ሶዶ አንጻር ነዉና። ከሕገመንግስቱ መግቢያ መነሳቱ ጥሩ ነው። በብሔሮች መሐከል የነበረ የተዛባ ግንኙነት ይላል። የብሔር ጭቆና ካልሆነ በምን መመዘኛ ነው።
በታሪክ በጉልህ የሚታወቅ በሕዝብ ቁጥር እጅግ በጣም ከሚያንሱት ስር ጋሞ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት ስር የሚገባዉ? ከዳልቦ ቀጥሎ ረዥም ዘመናትን በአካባቢዉ ያስቆጠረችዉ ዎላይታ ሶዶ የተገፋችዉ የብሔር ጭቆና ስለነበረ ነው እንጂ በግልጽ መመዘኛ ነበረ እንዴ? የዛን ዘመኑ ዉሳኔዎች ከመጋረጃ ጀርባ በብሔር ጭቆና ዉሳኔ የሚሰጥባቸዉ ስለሆኑ ለዛሬ አይሰሩም።
ዛሬ ግልጽ መመዘኛ ወጥቶ የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄዎች ተመልሰዉ የትኛዉ ብሔር ቁጥሩ ስንት ነው ?ከተማዉ ምን ያህል መሥፋት ይችላል? በቀድሞ ሥርአቶች የተሰሩ ደባዎች ማንን ጎዱ የሚለዉና የመሳሰሉት መታየት አለባቸዉ። የዎላይታ ሕዝብ አዋሳን አልምቶ በተጨፈጨፈ ማግስት ይህ መከራከሪያ አይሰራም።
በዎጋጎዳ ጊዜ በአርባ ምንጭ ዎላይታዎች ላይ ጥቃት ደርሶ እንደነበረም ይታወሳል። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ከግምት መግባት አለባቸዉ። ተመሳሳይ ፍርደ ገምድል ዉሳኔ እንዲደገም የሚጠይቅ ኢ_ዴሞክራሲያዊ መከራከሪያ ነው። አሁንም ችግሩ አርባ ምንጭ ትልማ መባሉ ሳይሆን ከዎላይታ ሶዶ አንጻር መቅረቡ ላይ ነው። የዎላይታ ሕዝብ ደግሞ የጠየቀዉ የራሱን ክልል ነው።
ያ ካልሆነም ከላይ የጠቀስናቸዉ ነገሮች ከግምት መግባት አለበት። በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳሄዉ ምናልባት በአሁኑ ሰአት ትርጉም ያለዉ ሥልጣን ያለዉ የዎላይታ ተወላጅ ስለሌለዉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በመሰል ስንኩል መከራከሪያዎች እየተመራ ሊሆን ይችላ የኮሪደር ልማትም ዎላይታ ሶዶን የዘለላት ለዛ ይሆናል።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ዎላይታ ሶዶ የፖለቲካና የአስተዳደር ማዕከል የተባለችዉ ለማዘናጋት ነው። ግልጽ መመዘኛ ከመጣ ዎላይታ ሶዶ እጅግ በጣም የላቀ እድል ስላላት ለማጨናገፍ የተሰጠ ማዘናጊያ ነው ይላሉ። ቁልፍ ፕሮጀክቶች በሙሉ ግልጽ መሥፈርት በሌላቸዉ ዉሳኔዎች ከዎላይታ ሶዶ እንዲሸሹ እየተደረገ ነው ይላሉ። እርሱዎ ምን ይላሉ?
✅ ማሪንዶስ ጦና ፦ ሕጋዊ መሥፈርት አለመኖሩ እንዳለ ሆኖ ፖለቲካ የቆለፈዉ በሕግ የመከፈት እድሉ ጠባብ ነው ። ያዉ አንድ እርግጠኛ መሆን የምንችለዉ በመንግስት ዉስጥ በጸረዎላይታ አሰራር የሚወሰኑ ነገሮች መኖራቸዉን ነው። የስድስት ማዕከሉም ጉዳይ ብዙ የሚያስኬድ አይመስል፦ በፍጹም በሕዝብ ብዛት የማይገናኙ ሕዝቦችን ከተሞች እኩል ለማድረግ መሞከር ቦዲቲና አረካ ከተሞች ከአለም ባንክ ድጋፍ መሠረዛቸዉም መሰል ችግር ነው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በዎላይታ ለከተሞች ጥያቄ ተጨማሪ ድጋፍ እየተገባ የነበረዉም እየተቀነሰ ነው፦ ሕዝቡ ይህንን በጸረዎላይታ አካሄድነት እያየ ነው።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መፍትሔ የሚሉት ነገረ ካለ?
✅ ማሪንዶስ ጦና፦ መፍትሔዉ ሕገመንግሥታዊነት ነው። ከተቻለ የክልል የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ ነው። ካልሆነ ግን እያንዳንዷ ነገር በግልጽ መሥፈርት መወሰን አለባት፣ በኢትዮጵያ አይነት ብሔራዊ መግባባት በሌለበት በተለይ በዎላይታ አይነት ከባድ ጭቆና በደረሰበት ሕዝብ ላይ የሚሰራ ሸፍጥ በጣም ከባድ ዋጋ ያስከፍላል።
ምናልባት ከድሮ አገዛዞች በወረሱት አስተሳሰብ ዎላይታ ሶዶን ወደ ሁዋላ ለማስቀረትና ህልማቸዉን በደቡብ ቀጠና ለማስፈጸም ከፖለቲካ ዉሳኔዎች ጀርባ በስዉር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በእርግጠኝነት የምነግራቸዉ የዎላይታ ዴሞክራሲያዊ ብሔረተኝነት ከራሱ አንጻር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ጭቁን ሕዝቦች ጋር በማበር ሕልማቸዉን መና እንደሚያደርግ በእርግጠኝነት እናገራለሁ። የዎላይታ ሕዝብ ሰዉን ሳያጠቃ የማንንም መብት ሳይጋፋ በሰላማዊ ትግል ኢ_ፍታዊ አሰራሮችን እርቃናቸዉን ማስቀረቱ አይቀርም።
💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።
✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።
ማሳሰቢያ ለአንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዛሬው የፓለቲካ ወጌሻ እንግዳ ዝግጅት ከላይ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረበ የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።
WolaitaTimes , በህብረተሰብ ውስጥ🙏 እናመሰግናለን🙏
በድጋሚ Hashshu Mayzza Wolaytta Deriya Ooratta Laytta Laamiya Gipaataw Saro Gattees!
በዓሉ የእርቅ፣ የሰላምና የመተሳሰብ ይሁንልን🙏
ጊፓታ ዮዮ🙏
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ቃለመጠየቅ ተደርጎ የተዘጋጀ ዘገባ ነው