
የክልሉ የፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በፃፈው ደብዳቤ በዎላይታ ዞን መለስተኛ የእንዱስትሪ ፓርክ ልማት ግንባታ ለማካሄድ ዞኑ የቦታ ዝግጅት እንዲያደርግ መጠየቁን ከተፃፈው ደብዳቤ ለመረዳት ችለናል።
ከትናንት ማታ ጀምሮ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ ግለሰቦች በደብዳቤው ህጋዊነት ዙሪያ ስከራከሩበት እንደነበር WT ለመታዘብ የሞከረ ሲሆን ለዞኑ ፓርኩ እንዲገነባ የሚያስችል ቦታ እንዲዘጋጅ ተጠይቆ የተፃፈው ደብዳቤ ትክክለኛ መሆኑንም ከምንጮቹ ለማረጋገጥ ችሏል።
በተለይም በዎላይታ ዞን የዚሁ ፓርክ ግንባታ በቅርቡ እውን የሚሆን ከሆነ ዞኑ በርካታ የስራ አጥ ወጣቶች የሚገኙበት በመሆኑ በተወሰነ ደረጃም ችግሩን ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።