በዎላይታ ህብረተሰቡ ከመንግሥት የሚጠይቃቸው ልማት ጥያቄዎች ተከልክለው በግለሰቦች ጥረት የተገነቡ ፋብሪካዎችን የማስመረቅ አካሄድ መቀጠሉ ተገልጿል።

በዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በወጣት ባለሀብት አቶ አብርሃም ፋንታ እና ባለቤቱ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተገነባ የሳሙና እና የቅባት ፋብሪካ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብረመስቀል ጫላ እንዲሁም የክልል፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።


በተቃራኒው በዞኑ ህብረተሰቡ ከመንግሥት የሚጠይቀው የተለያዩ ልማት ጥያቄዎች ተነፍጎ አመራሮች በግለሰቦች ጥረት የተገነቡ ፋብሪካዎችን የማስመረቅ አካሄድ አጠናክረው መቀጠላቸው አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን በርካቶች ይገልፃሉ። #Wolaita #Ethiopia
የህብረተሰቡ የልማት ጥያቄዎች በአመራሮቹ ተነፍጎ በግለሰቦች ጥረት የተገነቡት ጉብኝት ዘመቻ መቼ ይቆማል ?