1000022608

በፕሬዝዳንቱ የተሰረቀዉ ስታዲየም

አቶ ጥላሁን ከበደ የክልሉ ፕሬዘዳንት/ቅንብር Wolaita Times ሚዲያ

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በዎላይታ ሶዶ ይገነባል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ ስታዲየም ተሰርቆ ወደ አርባምንጭ የሄደበትን አጋጣሚ እናስታዉስ እስቲ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አዉ እንግዲህ አጋጣሚዉ የተፈጠረዉ አቶ ተስፋዬ ይገዙን የክልሉ አመራሮች ከአርባ ምንጭ ያባሩበት ወቅት ነው። በዚች ዉዝግብ መሐል ነው። እንግዲህ አቶ ጥላሁን ከበደ ያለ ምንም መሥፈርትና ዉይይት ስታዲየሙን በአርባምንጭ ያስጀመረዉ። አሳቻ ሰአት ጠብቆ ነው የዎላይታ ተወካይ በሌለበት፣ እርምጃዉን የወሰደዉ። ኢትዮጵያ በ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ እየተንቀሳቀሰች ነው፣ እንግዲህ ለዚህ ይመስላል፣ አድሎዉ የተፈጸመዉ። ያ የኢኮኖሚ ጥቅም ይኖረዋል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በመሥፈርት ላይ የተመሠረተ ዉይይት ቢደረግ ኖሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ዎላይታ ሶዶ እስቴዲየም ይገባታል፣ ብለን ለማለት የሚያስችሉ መከራከሪያዎችን ቢያቀርቡልን?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በመጀመሪያ የዎላይታ ሶዶ ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማነት፣ ብዙ ሊጎበኙ የሚችሉ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶች በቅርብ ርቀት ትገኛለች። ከ67ሺ አመታት በፊት ሰዉ የኖረበት የአፍሪካን ጥንታዊ ስልጣኔ ያስመሰከረዉ ሞቼና በራጎ ዋሻ በጉያዋ ነዉ። ከተማዋ በትንሽ ኢንቨስትመንት ለአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነት የመብቃት እድሏ ሰፊ ነዉ።

በሕዝብ ብዛት የዎላይታ ሕዝብ ከክልሉ ሕዝቦች አንደኛ ነዉ ብዙ ሚሊዮን በልጦ፣ ለዛዉም በሌሎች አካባቢ የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ታፍኖ ባለበትም። በአካባቢዉ በቂ ደረጃቸዉን የጠበቁ ሆቴሎች አሉ። ለልምምድ ከተባለም በትንሽ ዝግጅት ለልምምድ ሜዳነት ዝግጁ መሆን የሚችሎ በዎላይታ ሶዶ የአሁኑ ስታዲየም እና በዩኒቨርስቲዉ ጫፍ የሚገኘዉን መዉሰድ ይቻላል።

በቦዲቲና በአረካ ያሉ ስታዲየሞች ዝግጁ ናቸዉ። አለምንን ተጨማሪ የመለማመጃ ሜዳ ግምባታ፣ ያለምንም ካሳ ክፍያ በአንድ ምድብ የሚገኙ አራት ቡድኖችን ማስተናገድ የሚችሉ አራት ደረጃቸዉን የጠበቁ ስታዲየሞች አሉ። የእግር ኳስ ተሳትፎና ዉጤትን ካየን በደርግ ጊዜ በተጀመሩት መላዉን ኢትዮጵያ በሚያሳትፉ የእግር ኳስ ዉድድሮች ዎላይታ ደማቅ ነበረች፣ ለብሄራዊ ቡድን አራትና አምስት ተጨዋቾች ታስመርጥ ነበረ።

ዎላይታ ቱሳ የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ያሸነፈ የመጀመሪያው የደቡባዊዉ ኢትዮጵያ ክፍል ክለብ ነበረ፥ በአፍሪካ ኮንፈደሬሽንም በመሳተፍ የመጀመሪያዉ ክለብ ነው። ከ31 አመት በሁዋላ ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ስትመለስ ወቅቱ የአቶ ኃይለማርያም ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ተከትሎ ለደቡብ ከወትሮዉ የተለዬ የእኩልነት ቦታ የሚሰጥበት ነበረና አቶ ሳህሉ ገብረወልድ የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ጀግናዉና ከወገንተኝነት የጸዳዉ አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ከመረጣቸዉ የአርባምንጭ እና የአዋሳ ልጆች ብዙዎቹ የዎላይታዎች ልጆች ነበሩ፥ አበባዉ ቡጣቆ፣ ሲሳይ ባንጫ፣ ባህሉ አሰፋ ቱሳ|ን መጥቀስ ይቻላል።

ዎላይታ ዲቻ ከመጣ በሁዋላ ደግሞ በሊጉ ተፎካኳሪ ሆኖ ከመዝለቁም ባሻገር ለብሔራዊ ቡድን እንቁ ልጆችን ከማፍራቱ በተጨማሪ በአፍሪካ ኮንፈደሬሽን ካፕ የግብጹን ኃያል ክለብ ዛማሌክ ጥሎ በማለፍ ለመላዉ ኢትዮጵያውያን ኩራት መሆኑ CGTN ን በመሰሉ አለም አቀፍ ሚዲያዎች የተዘገበ ነበረ። በወቅቱ በዎላይታ እቴዲየም ባለመኖሩ ቡድኑ በአዋሳ ጨዋታዎችን ያደርግ ነበረ። በአሁኑ ሰአት የዎላይታ ዲቻ አካዳሚ በታዳጊዮች ዉድድር ለተከታታይ አመታት ሻምፒዮን ከመሆኑም ባለፈ ፍሬዎቹ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንጀምረዉ የፕሪሚየር ሊግና የብሄራዊ ሊግ ክለቦችን ከቦዲቲ ከነማና ከአረካ ከነማ ፍሬዎች ጋር ተደምረዉ አጥለቅልቀዋል።

በደጋፊው ብዛትም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ተመርጦ የሕዳሴው ግድብ ዋንጫ ተጫዉቶ ማሸነፉም ይታወሳል። በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በአዋሳ በሚደረገዉ የሊጉ ጨዋታዎች ስታዲየሞችን የሚሞላዉ የዲቻ ደጋፊ ነው። በዎላይታ ሶዶማ ጨዋታ ሲደረግ በኢትዮጵያ ከየትኛውም ከተማ የበለጠ ደጋፊ እስቴዲየም የሚገባበት፣ በየሕንጻዉ ጫፍ ተንጠልጥሎ፣ ከገባዉ በላይ እስቴዲየሙ በመሙላቱ ስታዲየሙ ዙሪያ ላይ ቆሞ እንደሚጠባበቅ ያዬ ሁሉ የሚመሰክረዉ ነው።

እስከ አምና መጨረሻ በክልሉ ብቸኛ የፕሪምር ሊግ ተወካይ ዲቻ ሲሆን፣ ዎላይታ ሶዶ፣ ቦዲቲና አረካም በብሄራዊ ሊግ አሉ። ስለዚህ የቀድሞ ደቡብ ክልልን እንኳን ብንወስድ፣ በአፍሪካ መጀመሪያ የተሳተፈዉ ዎላይታ ቱሳ ሲሆን፣ ሁለተኛዉ አዋሳ ከነማ ነበረ፣ ቀጥሎም ዎላይታ ዲቻ ነው። መሥፈርት ቢኖር የምትመረጠዉ ዎላይታ ሶዶ እንደምትሆን ግልጽ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህንን አድሏዊ ዉሳኔ ግን አቶ ጥላሁን ብቻዉን ደፍሮ ይወስናል? ከጀርባ ሌሎች አካላት ያሉ አይመስልዎትም?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ያዉ ይህ መንግስት የዎላይታን ሕዝብ በበቀልና በተንኮል እንደሚያስተዳድር የአደባባይ ሚስጢር ነው ። ከጀርባ ሌሎች አካላት እንደሚኖሩ ግልጽ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህንን የዎላይታ ተወካዮች በካቢኔ ስብሰባዎች፣ በክልል ምክር ቤትም ሆነ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለምን አያነሱም ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አንደኛዉ ተጋፋጭ በነበረዉ የነዳጋቶ ኩምቤ አስተዳደር ወቅት ብልጽግና በዞኑ ላይ ያደረገዉ መፈንቅለ መንግስት ብዙ ዞኑን ጎድቷል። አብዛኛው አመራር መንግስት በዎላይታ ሕዝብ ላይ ጤናማ አመለካከት እንደሌለዉ አምኖ የተቀበለ ይመስላል። በጣም ያሳዝናል። ሌላዉ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ዎላይታ በፌደራልም፣ በክልልም የሚገባትን ሚዛናዊ ዉክልና ተነፍጋለች፣ ስለዚህ ለዘርፈ ብዙ ተንኮሎች ዞኑ ተጋልጧል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

በተያያዘ አርባምንጭ ከተማ እያስገነባ ላለው ስታዲየም ግንባታ ሁሉም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ በአንድ አባወራ 1000 ብር እንዲያዋጣ ሊደረግ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ቃል በቃል ለጠቅላላ አማራሩ በዎላይታ ሶዶ ስልጠና ማዕከል መዝጊያ ንግግር ባደረጉበት ወቅት መናገራቸውን ከስብሰባው ተሳታፊዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የአርባምንጭ ስታድየም ተገንብቶ እስከሚያልቅም አንድም ሜጋ ፕሮጀክት የትኛውም ዞን ሆነ ልዩ ወረዳ ህዝብ አስተባብሮ ለማሰራት ቢያቅድ አመራሩ ተጠያቂ እንደሚሆንና ክልሉም ለሚሰራው ስራ እውቅና እንደማይሰጥ ተነግሯል።

ለአፈጻጸሙ ከጋሞ ዞን አመራሮች ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት ወደ ተግባር እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፏል።

በቅርብ ጊዜ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ ለትውልድ አካባቢያቸው በክልሉ ካብኔ የጋራ ውሳኔ ባልተሰጠበት ለአርባምንጭ ከተማ ስታዲየም ግንባታ በሚል ከመንግሥት በጀት 500 ሚሊዮን ብር መስጠታቸው ጫፍ የወጡ አድሏዊ አሰራሮች አንዱ ማሳያ በሚል በርካቶች ቅሬታ ማሰማታቸው ይታወሳል።

WolaitaTimes , በህብረተሰብ ውስጥ🙏 ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏 #Ethiopia #Wolaita #Etv #Ebc

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ቃለመጠየቅ ተደርጎ የተዘጋጀ መሰናዶ ነው