
2 መቶ ሺህ በላይ ተከታይ ለማፍራት ዘመቻ ተከፍቶ የነበረው ለምን ተዘጋ ?
የዎላይታ ብልጽግና ፓርቲ አምና ሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ፌስቡክ ገጽ ተከታይ ቁጥር ወደ 200ሽህ ተከታይ ለማድረስ በአቅጣጫና በቀጭን ትዕዛዝ በዞን ደረጃ ሼርና ላይክ እንዲያደርጉ ለአመራሩ አስገዳጅ አቅጣጫ ተቀምጠው ዘመቻ ተከፍቶ ከ47 ሽህ ተከታይ ማለፍ ያልቻለው ፌስቡክ ገፃቸው ከወራት በፊት የፌስቡክ ህግና ደንብ በመጣሱ ሊዘጋ መቻሉን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል።

አንድ የቀድሞ የፓርቲ ከፍተኛ አመራር ስለሁኔታው ሲገልፅ፦ “በዞኑ ሁሉም የፓርቲውን ፌስቡክ ገፅ ላይክም ሆነ ሼር በዞኑ ፓርቲ ኮማንድፖስት ስለሚቆጣጠር የዞንና የወረዳ አመራሮች ከሁለት ጊዜ በላይ ሼር እንዲያደርጉ ይገደዳሉ። ይህን የማያደርግ አመራር በአመራርነቱ እንደማይቀጥል ቀጭን ትዕዛዝ ይሰጣል” ይላል።
“ይህን ፔጅ ሼርና ላይክ የማያደርግ እንዲሁም በጎ ሀሳብ የማይሰጥ አመራር በኮማንድፖስት በኩል ለሚመለከተው ቀርቦ ከሥልጣን እንዲባረር የሚደረግበት ዋነኛው መስፈርት ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም እኚሁ የቀድሞ አመራር “የዞን ፓርቲ ፌስቡክ ገጽ ላይክና ሼር ለማድረግ እንዲሁም በዞኑ ውስጥ የመልካም አስተዳደር እጦት ስከሰት በመቃወም የሚጽፉትን ማህበራዊ ሚደያዎችን ለማጠልሸት ፌክ/የውሸት አካውንቶች ከዞን እስከ ወረዳ ተከፍቶ እየተሠራ ይገኛል” ሲሉ አስረድተዋል።
አመራሩ ለአብነት ሲጠቅሱ “በማንኛውም በዞኑ ተሿሚ በፌስቡክ በግል አካውንታቸው ብንመለከት የፓርቲውን ዜና ጥሩ ሆነ መጥፎ መጋራትና ላይክ ማድረግ የሹመቱ አንዱ መሥፈርት ነው። ውጤቱ ይሰጣል ተግባራዊ የማያደርጉት ከሥልጣን ይነሳሉ። በእያንዳንዱ ዜና ላይክና ሼር የሚያደርጉ አመራር በኮማንድፖስት አማካይነት ይቆጠራል” በሚል አብራርተዋል።
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ፌስቡክ ገጽ የተከታይ ቁጥር ወደ 200ሽህ ተከታይ ለማድረስ በአቅጣጫና በጥብቅ ትዕዛዝ ለወራት በዞን ደረጃ ብሠራም ከ47ሽህ ተከታይ በላይ ማለፍ ያልቻለው ፌስቡክ ገፃቸው በዞን ደረጃ በአዋጅ ሼርና ላይክ እንዲያደርጉ ለአመራሩ አስገዳጅ አቅጣጫ ተቀምጠው ስሰራበት የፌስቡክ ህግና ደንብ በመጣሱ ተዘግቶ አዲሱ 12 ሺህ የደረሰውን በተመሳሳይ መንገድ በማሳደግ ዘመቻ ላይ እንደሚገኙ ተመልክተናል (ዜናቸውን ብንመለከት ከላይክ በላይ ሼር ይበልጣል)።

አጠቃላይ የዞኑ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በፓርቲው ኮማንድፖስት ሀሳብን በነፃናት የመግልፅ መብት በሚጥስ መንገድ እንደሚጠረነፍ የተገለፀ ሲሆን የዚህ ጉዳይ ዋነኛው ማሳያ ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ያለውን አመነታ ከማጠልሸት በላይ የመረጃ ነፃነት፣ ታአማንነትና ተደራሽነት እውነታውን ሸፍነው በላይክና በሼር ሥራ የተሠራ የሚመስለው የዞን ፓርቲ ቀጣዩ ዕጣ ፈንታው ምን እንደሚመስ መገመት ይቻላል ያስብላል።
በተያያዘ ዜና ይሄው በመረጃ ነፃነት ላይ የተከፈተው አፈና ዘመቻ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አምና ሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ፌስቡክ ገጽ የተከታይ ቁጥር ወደ 450 ሽህ ለማድረስ በአቅጣጫና በቀጭን ትዕዛዝ ለወራት በክልል ደረጃ ብሠራም በአሁኑ ወቅት ከ13 ሽህ በላይ ተከታይ ማግኘት እንዳልቻለ ተመልክተናል።

በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው