
በብልፅግና ጭምብል የምንቀሳቀሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች ሙስና ቅሌት
በባለፈዉ ፅሁፍ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በምርመራ ዘገባው ለመጠቆም እንደተሞከረዉ የክልሉ ፖለቲካ ብልሽት በኢኮኖሚዉ ጠንካራ ሀብት ያካበተ ስሆን በዋናነት በዛሬዉ ስማቸዉ የማይጠቀሱ ከፍተኛ የፈደራል የመንግስትና የፓርት አመራሮችን ያካተተ ጠንካራ የጥቅም ሰንሰለት የክልሉ ሀብት እየተዘረፈ ይገኛል፡፡
በክልሉ ማዕድንና የመሬት ዉስጥ ሀብቶች ዝርፍያ የሚመራዉ በደቡብ ኢት/ያ ክልል ፊት አመራሮች ከርዕሰ መሰተዳደር ጀምሮ በተቀናጀ ሰንሰለት መሆኑ እዉነት ሲሆን በኢት/ያ የመሬት ዉስጥ ሀብትና ማዕድናት በአገርቱ ህግ መሠረት መመረት እየተገባዉ በታኝና ከፋፋይ ትርጉም በመስጠት ለዛ ሀሳብ የሚሆኑ ትፖዞዎችን በመሰብሰብ ልክ የህወሓትን ፈለግ በመከተል “ሳሮ” የሚባል ማህበር በርዕሰ መስተዳደሩ ሀሳብ አመንጭነት በማቋቋም ከአንድ ብሔር ብቻ እነዚህን የማህበሩ አባል የሆኑ ግለሰቦችን በመሰብሰብ ከማዕድናት ፊቃድ አሰጣጥ መመሪያ ዉጭ በርዕሰ መስተዳደሩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ፊቃድ እንዲሰጥ በመደረጉ ህገ ወጥ ተግባር ጫፍ መዉጣቱ የሰለቻቸዉ አካላት በክልሉ ለሥራ የተሰጠዉ የመንግስት ተሽከርካሪ ጭምር በመጠቀም የኮንትሮባንድ ነጋደ ለሆኑት ለክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠታቸዉ የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያለ ወትሮ ጥቆማዉም ስለበዛባቸዉ የእገዳ ደብዳቤ ፅፈዋል፤ እገዳዉም ከርዕሰ መስተዳደሩ ጋር የተናበበ ነዉ፤ ይሁንና ግን እገዳ ነዉ።
እገዳዉ እንዳልኩት የተናበቡት ስለሆነ በቅጽበት የማህበሩ ስም በመቀየር ‘ምንጭ’ የሚባል ሌላ ከመጀመሪያዉ ስም ሀሳብ ጋር የሚገናኝ ስም በመስጠት ፈቃድ ይሰጣሉ፤ አሁንም በቢሮ ዉስጥ ያሉ ይህ ጫፍ የረገጠ ህገ-ወጥነት እጅግ ያንገሸገሻቸዉ ዜጎች ድጋምም መረር ያለ ጥቆማ ለኮሚሽኑ ያቀርባሉ፡፡
ኮሚሽኑ አሁንም ጉዳዩ እየከፋ መሄዱንና ከርዕሰ መስተዳደር ከሚሰጠዉ ትዕዛዝ ዉጭ እነሱንም ወደ ተጠያቅነት ሊወስድ እንደምችል በመገንዘብ ለአለቃቸዉ ድጋምም እገዳ እንደምፃፍ በማግባባት ድጋሚ ላደራጁት ህገ-ወጥ ማህበር እገዳ ፃፉበት ይሁን እንጅ እነዚህ ማህበራት ፊቃዳቸዉን ከሌላ አከባቢ በደላላ ለሚመጣዉ ባለሀብት በብዙ ሚሊዮን ይሸጡና ገንዘቡን ተከፋፍሎ ሌላ ማህበር ያደራጃሉ፤ ምክንያቱም ሰጪዎችም ነሽዎችም እነሱ ስለሆነ ጉዳዩ አልጋ በአልጋ ነዉና።
በቢሮዉ ሁኔታዉን የሚያመቻቹ አካላት ከአምስት መቶ ሺህ ብር በታች ጉቦ እንደማይወስዱ እና ለዛ ማሳያ ይሆን ዘንድ የምርመራ ሥራ በማያደናቅፍ መልኩ የተዘጋጀ በድምፅ የላክነዉ መረጃ ለእዉነታ ፍለጋዉ መነሻ ይሆናል።
ሌላዉ ይሄ ተቋም የሚያንቀሳቅሰዉ በጣም በብዙ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ፕሮጀክት ያለ ሲሆን እያንዳንዱ ፕሮጀክት በዚህ ሙስና ተግባር ምክንያት ሳይጠናቀቁ ተስተጓጉሎ ይቀራሉ፤ ግን ክፍያ ባልሰሩበት ይከፈልና ዉል እንዲቋረጥ ይደረጋል።
ለምሳሌ የባስኬቶ ዞን ላስካ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት እና የዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት እዉነተኛ ማሳያዎች ናቸዉ።
ሌላዉ አንገብጋቢዉና አሳሳቢዉ ትልቁ ችግር ህገ-ወጥነትን ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት እንዲጠብቅና እንዲከላከል ሀላፊነትና ስልጣን የተሰጠዉ የክልላችን ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮች ራሳቸዉ ኮንተርቫንድስቶች ከመሆናቸዉ ባሻገር የሙስና እና ሙሰኞች ቅንጅት በመፍራት የሙስና ጥቆማና አቤቱታም ጭምር ያለዉን ይዞ ከመከላከል ይልቅ ሙሰኞችን በእናንተ ላይ ጥቆማ እየመጣ ስለሆነ በጥንቃቄ ሥራችሁን ሥሩ ብሎ መንገድ ለሙሰኞች በመስጠት መደላደልን መፍጠር በክላላችን የሙስኛ ተግባርና አድራጊዎች በቀላሉ ጠቋሚዎችን በመጉዳት ተፈርቶ እንዲኖሩ የሚያደርግ አደገኛ ሁኔታ መኖሩን ለማሳያነት እየጠቆምን በክልሉ የኮንትሮባንድ፣ የድንጋይ ከሰል እና በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በሚመለከታቸዉ አካላት የተጀመረዉ የምርመራ ሥራ ተጠናክሮ እንድቀጥል እና ለዛ አጋዥ መረጃዎች የማጋለጥ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እየገለጽን ዝርዝር መረጃ ለህዝብ ይፋ ካደረግን በምርመራ ሥራ ጫና እንዳይፈጥር ታስቦ ለማሳያ የተላከ መረጃ ነዉ፡፡
በተያያዘ ከዚህ መረጃ ጋር በተያያዘ የክልሉ ውሃ ማዕድንና ማዕድን ኢኒርጂ ቢሮ ለመንግስታዊ አገልግሎት በሚሊዮን ብር ከግለሰቦች ጋር የተደራደሩበት የስልክ ንግግር ድምፅ ከሰዓታት በኃላ እናቀርባለን። #Ethiopia #southernethiopiaregion