1000023090

“የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግሥት ሰራተኞች ስቃይና የአመራሮቹ ቀልድ እንደቀጠለ ነው” – ሰራተኞች

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ የመንግስት ሰራተኛውን ደሞዝ “በአግባቡ የማያስገቡ ዞኖች እና ወረዳዎች በመኖራቸው ከነሐሴ ወር ጀምሮ ቀጥታ የሰራተኞች ደሞዝ በባንክ አካውንቱ እንዲገባለት ማድረጉንና ይህ አሰራር በቀጣዩም ወር እንደሚቀጥል” በሚል ከዎላይታ ሶዶ ፋና 99.9 FM ሬዲዮ ጣቢያ ጋር በዚህ ሳምንት ባደረጉት ቃለመጠይቅ አስታውቀዋል።

ኃላፊው በገለፃቸው ፦ “የመንግስት ሰራተኛውን ደሞዝ ሳይሸራረፍ ክልሉ ከዚህ ቀደምም ይልክ እንደነበረና ነገር ግን አንዳንድ ወረዳዎች ለሌላ አገልግሎቶች በመቁረጥ ሰራተኛውን ሲበድሉ ቆይተዋል ያሉት የቢሮው ሃላፊ በእነዚህ አካላት የተዝረከረከ አሰራር ክልሉ ደሞዝ መክፈል እንደማይችል ሲቆጠር ቆይቷል በማለት በጥቅምት ወርም የሰራተኛውን ደሞዝ እራሳችን በሙሉ ሃላፊነት ማስገባት የግድ ይለናልም” ብለው ተናግረዋል።

በተቃራኒው በዎላይታ ዞን የመምህራን ደሞዝ አሁንም አልተከፈለም፤ በአብዛኛው መዋቅር ትምህርትም አልተጀመረም፤ ደመወዝ የተከለከሉ መንግሥት ሠራተኞች ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ሲሉ ከድለላ ጀምሮ እስከ ጉልበት ሥራ ያገኙትን ሁሉ እንደሚሰሩ ጠቅሰው “በልተን ማደር አለብን በሚል ወደ ቢሮ አይገቡም፤ በአንዳንድ መ/ቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሠራተኞች አይታዩም፥ ቁጭ ብለን ከምንሞት ብለው ቢሮ ዘግተው ወደ ገጠርና ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል“ ተብሏል።

በዎላይታ ዞን ከመምህራን የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የ2016 የመማር ማስተማር ሥራ እንደተጎላላ ነው ዓመቱ ያለቀው፡፡ የመምህራኑ ጥያቄ አሁንም መፍትሄ ባለማግኘቱ ችግሩ ወደ 2017 ዓም ተሻግሯል መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዞኑ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከግል ትምህርት ቤቶች በስተቀር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከአሁን ትምህርት አልተጀመረም።

የቀጠለው የመምህራን ደሞዝ ጥያቄ በዎላይታ ዞን ከመምህራን የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የ2016 ዓም የመማር ማስተማር ሥራ እንደታጎለ ነው ዓመቱ ያለቀው። የመምህራኑ ጥያቄ አሁንም መፍትሄ ባለማግኘቱ ችግሩ ወደ 2017 ዓም መሻገሩ ነው የሚነገረው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አሁን ላይ በዞኑ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከግል ትምህርት ቤቶች በስተቀር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከአሁን ትምህርት አልተጀመረም፡፡

በዎላይታ ዞን ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የመምህራንም ሆነ የሌሎች መንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ በወቅቱ አይከፈለም፡፡ ዘግይቶ ቢከፈልም የደሞዛቸው ከ20 እስከ 50 በመቶ ብቻ እየተሰላ እንደሚያገኙ ነው የሚነገረው፡፡ የዞኑ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር መምህርት ባዩሽ ዘውዴ የመምህራን የደሞዝ ጥያቄ አለመፈታት የትምህርት ሥረዓቱን እየረበሸ ይገኛል ይላሉ፡፡

በመንግሥት ተቋማት ላይ ያሳደረው ተፅእኖ በዎላይታ ዞን በሚገኙ 17 ወረዳዎች የሠራተኞች ደሞዝ ክፍያ አለመፈጸም የጤና ተቋማትን ጨምሮ በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ መሥሪያቤቶች ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ አሁን ላይ አብዛኛው ሠራተኛ ተስፋ በመቁረጥ በሥራ ገበታው ላይ እንደማይገኝ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በዚህም የተነሳ አንዳንድ መሥሪያቤቶች በከፊል ሌሎቹ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል፡፡

“ሠራተኛው ቤተሰቡን ለማስተዳደር ሲል ከድለላ ጀምሮ እስከ ጉልበት ሥራ ያገኘውን ሁሉ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ“ በልተን ማደር አለብን በሚል ወደ ቢሮ አይገቡም፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንድ መሥሪያቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሠራተኞች አይስተዋልባቸውም፡፡ ምክንያቱም ቁጭ ብለን ከምንሞት ብለው ቢሮ ዘግተው ወደ ገጠርና ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል“ ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ዞኑ ክልሉ በጀት ቶሎ አይለቀቅም ሲል ክልሉ ደግሞ ችግሩ እኔን አይመለከትም እያለ ነውና በመሀል የመንግስት ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ህይወት ኑሮ ውድነት ተጨምሮ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ቀጥሏል።

ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን, ስለዘውትር አብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏

#Ethiopia #Wolaita #southethiopia #wolaitatimes