1000023489

የመብት ጥያቄ ይዘው ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ያመሩ የጎፋና ባስኬቶ ሀገረ ስብከት ምዕመናን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞና ዎላይታ ዞኖች ድንበር መታገታቸው ተገልጿል።

ጠያቂ የሌለዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መንግስታዊ ብልሽት አልበቃ ብሎ ወደ ሃይማኖታዊ ጣልቃ-ገብነት መሸጋገሩ ተጠቆመ!

እገታው የተፈጸመው በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል ፖሊስ ኮሚሽን ሲሆን በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በአቶ ጥላሁን ከበደ ቀጥታ ትዕዛዝ መሆኑም ተረጋግጧል።

የታገቱ የጎፋና ባስኬቶ ሀገረ ስብኬት ምዕመናን ዝርዝሩን እንደሚከተለው ያብራራሉ፡፡

ታግቶ ከሚገኙ ምዕመናን መካከል ስለ እገታው ተጠይቆ ምላሽ የሰጡ ታጋቾች እንደሚገልጹት በቁጫ ወረዳ ሞርካ አከባቢ እና በተለምዶ ጋሱባ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በ 2 አውቶቢስ ከፊትና ኋላ ሆነው እየተጓዙ ሳሉ በፖሊስ አባላት መታገታቸውን ተናግረዋል፡፡

ልክ እንደታገቱ ወደ ጎፋ ዞን አስተዳደር ስልክ በመደወል በዎላይታ ዞን እና በጋሞ ዞን ፖሊስ ታግተናል ብለን ሲንጮህ የጎፋ ዞን አስተዳደር ተወካይ የሆነ ግለሰብ እኛ የሚናውቀው ነገር የለም ወደ ክልል ደውሉና አሳውቁ እንደተባሉ ይናገራሉ፡፡

ቀጥለን ለክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የውሀ ቢሮ ሃላፊ ለሆኑት ለኢንጅነር አክሊሉ አዳኝ ደውለን ሲንጠይቅ መረጃ እንደለሌውና የምያውቀው ነገር እንደለሌ ገልጾ ለክልል ፖሊስ ወይም ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ደውላችሁ አሳውቁ ብሎናል ይላሉ ታጋቾች በጋራ ባሰሙት ድምጽ፡፡

በምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ጥቆማ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ስልክ በማግኘት ደውለን በጋሞና በዎላይታ ዞን ፖሊስ አባላት መታገታቸውን ሲናገሩ በስልክ ያናገሯቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሃ ጋረደው ስለ እገታው እንደሚያውቁና በሳቸው ትዕዛዝ ጭምር መታገታቸውን ገልጸው ጥያቄያችሁን ይዛችሁ የትም መሄድ አትችሉም የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጭምር ስለተሰጠ አርፋችሁ ብትቀመጡ ይሻላቹዋል በማለት ከአንድ ሕዝባዊ ፖሊስ አመራር የማይጠበቅ ንግግር መናገራቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሐይማኖት ጉዳይ ምን ያህል እጁን ከቶ እያበጣበጠ እንደሚገኝ ማሳያ ነው በማለት ታጋቾቹ ምእመናን በምረት ያስረዳሉ፡፡

እነዚህ የታገቱ ምእመናን ስለሚሄዱበት ጉዳይ ስያስረዱ በጎፋና ባስኬቶ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ለአራት ተከታታይ አመት የጠየቁት ሀገረ ስብከት መዋቅር ጥያቄ ተገቢ መሆኑ በቅዱስ ስኖዶሱ ታምኖ ምላሽ ቢሰጥም የቀድሞ ጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩ ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ደርቦ ለመምራት በመፈለጋቸው ምክንያት እሳቸው ለ20 አመታት የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆኖ በሰሩበት አመታት በሙሉ ጎፋና ባስኬቶ ምእመናን ያልጎበኙ ያልባረኩና መንፈሳዊ አባት ሊሆኑ ያልቻሉ አባት ስለሆኑ ደርበው እንዳይመሩ ጥያቄ ለማቅረብ በአድስ አበባ እየተካሄደ ባለው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አቤት ለማለት ለ43ኛ ጊዜ እንደሚሄዱ አስረድተዋል፡፡

እኝህ አባት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከ250 በላይ ዜጎች በናዳ በሞቱ ጊዜ እንኳን ሕዝቡን ያላጽናኑ ቅመኛ አባት መሆናቸውን ለአብነት ያነሳሉ፡፡

ጉዳዩ በኃይማኖታዊ ስርዓት ለመጨረስ እየተመካከርን ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጉዞ በሚናደርግበት ወቅት በአምባገነኑ በክልሉ ርዕሰመስተዳድር በአቶ ጥላሁን ከበደ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የቀድሞ ጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ኤልያስን በዘመናዊ መሳሪያ እና በልዩ ኃይል በማሳጀብ ምዕመናኑ ያለአግባብ አርባምንጭ ላለው ሀገረ ስብከት እንዲገብር ለማድረግ ምዕመኑን በበረሃ አሳግዶ ምሽት በብርድ ቀን በፀሐይ እንዲንቀጣ እያደረጉ ናቸው በማለት በከፍተኛ ቁጣ እየተናገሩ ይገኛሉ።

ከዚህ ቀደም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች የሙስና ቅሌት በፅሑፍና በድምጽ ቅጅ ጭምር ያጋራን ሲሆን የሙስና ቅሌታቸው ሳያንስ በኢትዮጵያ ሕገ መንገግስት አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 1-3 መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፤ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ተብሎ የተደነገገውን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ ጭምር በመተላለፍ የማህበረሰቡን ስቃይ እያበዙ መቀጠላቸውን መረጃዎቹ ያመላክታሉ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመብት ጥያቄ ለሚያነሳ ማንኛውንም አካል ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በማሰር፣ በማንገላታት እና በማሰቃየት አጸፋ የሚመልስ ስሆን ዛሬም በሰጡት ቀጥታ ትዕዛዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጎፋና ባስኬቶ ሀገረ ስብከት ምዕመናን ላይ የበቀል ዱላ አሳርፎባቸዋል፡፡

በመሆኑም ይህንን ህዝብን እያሳቃየ የሚኖረዉን የደቡብ ኢት/ያ ክልል መንግስት የሚጠይቅ አካል ይኖር ይሆን? ጥያቄያችን ይሆናል።

#WolaitaTimes ሚዲያ, ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን, ስለዘውትር አብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏