1000023773

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ዞን ለጥቂት ጊዜ ቀዝቅዞ የነበረው በማህበራዊ ሚዲያ ሀሳባቸውን የሚገልጹ ወጣቶችና የመብት ተሟጋቾችን ማሰርና መደብደብ ማገርሸቱ ተገልጿል።

ሰሞኑን በዞኑ በቦድቲ ከተማ የታሰሩት በዞኑ እና በአከባቢያቸው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ችግሮችን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋለጥ የሚታወቁ ወጣቶች እንደሆነ ተነግሯል።

ከጥቅምት 15/02/2017 ዓ.ም ጀምሮ በግፍ በዎላይታ በቦድቲ ከተማ ደረቅ ፖሊስ ጣብያ ታስረው የሚገኙት፦ 1ኛ ወጣት ባንተወሰን በርገነ፣ 2ኛ ወጣት እምነት ኢያሱ፣ 4ኛ ወጣት ሄኖክ_ሞጎስ፣ 4ኛ መስፍን ቡሹሎ ሲሆን የመንግስት ሰራተኞችም ናቸው።

ወጣቶቹ በዞኑ እና በአከባቢያቸው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ችግሮችን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋለጥ የሚታወቁ መሆኑ ተገልጿል።

እነኚህ ያለምንም ፍ/ቤት ትዕዛዝ እና በፖሊስ መጥርያ ከቤታቸው በፖሊስ ታፍሰው ከተወሰዱበት ቀን ጀምሮ ነገ ማለትም በጥቅምት 22/02/2017 ዓ.ም በቦድቲ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት ይቀርባሉ እንደሚቀርቡ ቤተሰቦቻቸው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ማምሻውን ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

ቤተሰቦቻቸው እንደገለፁት፦ እነዚህ የታሰሩ ወጣቶች “እስከአሁን ድረስ የተከሰሱበት የወንጀል መረጃ ማስረጃ እና ከሳሽ በለሌበት በፖለቲካ አመራር ትዕዛዝ ብቻ ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ተነፍገው ህገመንግስት ያጎናጸፈው መብት በሚፃረር መልኩ ፖሊስ፣ ፍ/ቤት እና አቃቤ ህግ ከፖለቲካ ነፃ ባለመሆናቸው ያለምንም የወንጀል ህግ በፖሊስ ጣብያ ብቻ በርሀብ በጥም እንቅስቃሴዎችን በመገደብ እንዲሁም የዋስትና መብታቸው ተከልክለው አንድ ሳምንት መሉ በፖሊስ ጣብያ ቆይተው ነገ ችሎት ይቀርባሉ” የሚል መረጃ እንደሰሙ አስረድተዋል።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዎላይታ ዞን በየመዋቅሩ በማህበራዊ ሚዲያ በአከባቢው የሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ሀሳባቸውን የሚገልጹ ወጣቶችንና የመብት ተሟጋቾችን ለእስርና ድብደባ ማድረግ ለጥቂት ጊዜ ጋብ ያለ ቢመስልም አሁን ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መልሶ አገርሽቷል።

እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች- በ #WolaitaTimes ሚዲያ
ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🙏

Ethiopia #southethiopia

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተዘጋጀ ዘገባ ነው