1000023923

ሰበርዜና

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሙስና ቅሌታቸውን አጋልጠዋል ያሏቸውን ሁለት አመራሮች ከኃላፊነት ማንሳቱ ተገልጿል።

ሃይ ባይ ያጣው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በዉሃና ማእድን ቢሮ በድንጋይ ከሰል ምርት ዙርያ የሚታየውን ሙስና አጋልጠዋል ያሏቸውን 2 አመራሮችን ከሀላፊነት አንስቷል፡፡

በባለፈዉ ዘገባችን የመንግስትና የህዝብ ሀላፊነት ወደ ጎን በመተዉ በማዕድን ምርት ምዝበራ ላይ የተሰማሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ተዋንያኖች ድርጊት የሚገልጽ የስልክ ንግግር እና ሠነዶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ማድረጋችን ይታወቃል፡፡

በሙስና ሰንሰሌቱ የተተበተቡ አካላት በዲላ ማዕከል የጨረባ ግምገማ በማድረግ የሙስና ቅሌታቸውን አጋልጠዋል ያሏቸውን ሁለት አመራሮችን ከኃላፊነት ማንሳታቸው ተረጋግጧል፡፡

አመራሮቹ 1ኛ. ኢንጅነር ፍፁም መኩርያ ምክትል ቢሮ ሃላፊና የዉሀ ዘርፍ ሃላፊ 2ተኛ. ወይዘሮ ወይንቱ ገዳላ ኮሙንኬሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ሲሆኑ ከሃላፊነት የተነሱበት ምክንያት መረጃ በማውጣት ሙስናችን አጋልጣቹዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

እነዝህ 2 አመራሮች የሚመሩ ዘርፍ ከማእድን ጋር የማይገናኝ ብሆንም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአቶ ጥላሁን ከበደ ፊርማ ከቀን 21-02-2017 ዓም ጀምሮ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን የዜና ምንጫችን አረጋግጧል፡፡

ከዚህ መረዳት የሚቻለዉ የሙስና ተግባር የፈጸሙና ተባባሪ የሆኑ አካላትን ከተጠያቂነት ለማስመለጥ የታሰበ እንደሆነ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

ሃላፊነት የሚሰማው አካል ቢኖር የሙስና ተግባር መኖር አለመኖሩን በማጣራት ትክክለኛ እርምጃ በመውሰድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ስገባቸው መረጃው ለምን ወጣ? ገጽታችን ተበላሽቷል በምል ተልካሻ ምክንያት ጊዜ አያጠፉም ነበር፡፡

ስለሆነም የሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጣልቃ በመግባት ሌብነታቸውን ለማድበስበስ የምያደርጉትን እንቅስቃሴ በመከታተል ሂደቱን በጥንቃቄ በመመርመር ዉጤቱን ለሕዝብ ይፋ እንድያደርግ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

  • እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች
    በ #WolaitaTimes ሚዲያ
    -በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
  • ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🙏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው