1000023967

እስኪ እንወያይበት🙏

በሌብነት የተጠረጠሩ አመራሮች ከታሰሩ በህጋዊ መንገድ እንቨስትመንት ለመስራት መሬት ተረክበው እንቅስቃሴ የጀመሩ ባለሀብቶች ስራ ለምን እንዲቆም ይደረጋል?

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ከመሬት ምዝበራ ጋር ተያይዞ ታስረዋል፣ እየታሰሩም ይገኛሉ።

በተቃራኒው ደግሞ በሌብነት የተጠረጠሩ አመራሮች ከታሰሩ በኃላ በህጋዊ መንገድ የተለያዩ ግዙፍ ፋብሪካ ጀምሮ እንቨስትመንት ለመስራት መሬት ተረክበው በአከባቢው ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ እንቅስቃሴ የጀመሩ ባለሀብቶች ስራ እንዲቆም መደረጉን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ለአንድ ከተማ ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና ያላቸውን የንግዱ ማህበረሰበንና ባለሀብቶችን የማሳደድና ተረጋግተው እንዳይሰሩ እየተወሰደ የሚገኘው እርምጃ በግልጽ የከተማዋን ዕድገት ወደኋላ የመመለስ ዕቅድ አካል እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ።

በቅርቡ በዞኑ የአለም ባንክ UIIDP ማዕቀፍ ተጠቃሚ የነበሩ ቦዲቲ እና አረካ ከተሞች በ2020 ዓ.ም አሁን ላይ አለም ባንክ ያወጣውን መስፈርት በተገቢው በማሟላትና የተሻለ አፈፃፀም በየጊዜው በማሳየት በክልሉ ከፕሮግራሙ ከፍተኛ ተጠቃሚ እየሆነ የሚገኘው ዎላይታ ሶዶ ከተማ የታለመውን አላማ ሲያሳካ ባላቸው አፈፃፀምና በየጊዜው በሚያሳዩት የተግባር መሻሻል መነሻ የሶዶ ከተማ ደረጃ ስለሚደርሱ ቦታውን የሚተኩ ናቸው” ተብለው ታቅደው የነበሩት ቢሆንም ከድጋፍ ተጠቃሚነት መሠረዛቸው የዚሁ ሴራ አካል አይደለም ወይ?

በክልሉ በየትኛውም አከባቢ ተግባራዊ ያልሆነ በተለየ መንገድ በዎላይታ ሶዶ ከተማ አመራሮች፣ የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ባለሀብቶችን የማሳደድና ተረጋግተው እንዳይሰሩ የሚወሰዱ እርምጃዎች ለአከባቢው ልማት በጎ ሚና ከመጫወት ይልቅ በከተማዋ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ለማድረስ ያመዘኑ አይደሉም ወይ?

ነገሩን ለዛሬው ውይይት ነጥብ ግልጽ ለማድረግ ለምሳሌ አንድ ባለሀብት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ወይንም በሌላ ቦታ በህጋዊ መንገድ እንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማድረግ የተፈቀደለትን መሬት በሚሰጥበት ወቅት ያ መሬት ያለበት መዋቅር አመራሮች ለባለሀብቱ ከሚሰጥበት ቦታ ለሚነሱ ተነሺዎች የሚሰጥ ካሳ ገንዘብ የውሸት ሰነድና ማንነት በማዘጋጀት ይወስዳሉ።

ከዚያ ባለሀብቱ በህጉ መሠረት የተፈቀደለትን ቦታ ለማልማት በሚጀመርበት ወቅት ከላይ የተጠቀሱ የአመራሮቹ ወንጀል ድርጊቶች ይገለጥና ይታሰራሉ። በዚያን ጊዜ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የለለው ባለሀብት እንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንዲቆም እየተደረገ ነው። ለመሆኑ ህገወጥ ተግባር የፈፀሙትን በግላቸው መጠየቅ ወይስ በአከባቢው ለበርካቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ግዙፍ ፋብሪካ ግንባታ ጭምር ማቆም ነው መፍትሔ የሚሆነው ? እስኪ እንወያይበት🙏

Ethiopia #Wolaita #southethiopia