1000024179

“ክልሉ ከተመሰረተ ጀምሮ በማህበራዊ ሚድያዎች በአርሶ አደሩና በባለሀብቱ ልፋት የተገኙ ምርቶች ፎቶ እያስለጠፈ የተለጠፈዉም በኮማንድ ፖስት አማካይነት ላይክ፤ ኮሜንትና ሼር ኦዲት ማስደረግ መደበኛ ተግባር ካደረገ ሰነባብቷል”- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን

አንድ የደቡብ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን የክልሉን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት ከፍተኛ አመራሩ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በፅሁፍ በላኩትና አንገብጋቢ ባሉት በዚሁ መልዕክት “በክልሉ ህዝቦች ትልቅ ተስፋ የተጣለበት እና የለዉጡ ትሩፋት የሆነዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአፋኙና በአናቂዉ ሥርዓት የህዝቦች ጥያቄ በራሱ በህዝቡ መልካም ፈቃድና ተሳትፎ መመለስ የተሳነ፥ አለፍ ብሎም ወደ ፀረዴሞክራሲ ተሻጋግሮ እስራትና አፈና ካየለበት እና ለበርካታ ጊዜያት ስታፈን የነበረዉ በለዉጡ መንግስት ተገቢዉን ምላሽ ያገኘ ነዉ” ብለዋል።

በመልዕክታቸው “ይሄ አደረጃጀት ዕዉን እንድሆን የሀገርቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ትልቅ ዋጋ የከፈሉት እና ክልሉ ለሀገርቱ ብልፅግና የራሱን ተመጣጣኝ ድርሻ እንድወጣ በተለየ መልኩ በቅርበት ክልሉን እየደገፉ እንደነበሩ የዉስጥ አዋቅ መረጃ ይጠቁማል” ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

“ሆኖም ግን ክልሉ ከተደራጀ በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ የክልሉን ህዝብ ከቀድሞ ክልል በባሰ መልኩ ስቆቃ ዉስጥ እንድኖርና የለዉጡ ተስፋ እንድጨልም አድርጎታል፡፡ በዚህም ለብቻቸዉ የክልልነት ጥያቄ ያቀረቡ የዎላይታ፤ የደቡብ ኦሞ፤ የጎፋ እና የጌድዮ ዞኖች ጥያቄያቸዉ ትክክል እንደነበር አስታዉሶ አሁን ለብቻ የክልልነት ጥያቄ በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ አካል እንድሆን አድርጎታል” በማለት አመራሩ አክለዋል።

ለዚህ መሰረታዊ ምክንያት ሲገልፁ “የክልሉ የአመራር ብልሽት ስሆን በተላይም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ህዝቡን ከማገልገል ይልቅ ህዝቡን ለመግዛት ያለዉን ፍላጎት ለማሳካት በሚያግዝ መልኩ ከብልፅግና ዕሳቤዎች ባፈነገጠ መልኩ በብሄሮች ካባ የራስ አቋም የሌላቸዉና የህዝብ ዉግንና በሌላቸዉ ተላላክዎችን ወደ ፊት አመራር በማምጣታቸዉ ነዉ” ብለዋል።

“ለዚህ ደግሞ የፌደራል መንግስት የዚህን ትልቅ ህዝብ በሴራኛዉ፣ በቅመኛዉ፣ በአስመሳዩ እና ትንሽ ጭንቅላት ባለዉ ግለሰብ እጅ ላይ በዕምነት መጣሉ ነዉ፡፡ ይህ ግለሰብ ደግሞ የራሱ የሆነ ሃሳብ የለሌዉ ነዉ፡፡ በአርሶ አደሩ እና በባለሀብቱ ልፋት የተገኙ የሙዝ፤ የፓፓያ፤ የቡና፤ ቅመማቅመሞች እና የለሎች ምርቶች ፎቶ በማህበራዊ ሚድያ በየደቂቃዉ እያስለጠፈ የተለጠፈዉም በኮማንድ ፖስት አማካይነት ላይክ፤ ሼር ኦዲት ማስደረግ መደበኛ ተግባር ከሆነ ሰነባብቷል” በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል።

አኚህ ከፍተኛ ባለስልጣን በመጨረሻ መልዕክታቸው “ሃሳብ ያነሰዉ አዕምሮ ደግሞ ባትሪዉ እንዳለቀ ስልክ ነዉ፤ በቁሙ ይተኛል እንጅ አይነቃም፤ ያለ ይመስላል እንጅ የለም፤ ቢቀሰቅሱት አይሰማም፤ ሃይል ጨርሷል፡፡ በመሆኑም ክልሉ በገዥዉ ርዕሰ መስተዳድር እና የርዕሰ መስተዳድሩ ተላላኪ በሆኑት የፓርቲዉ አመራሮች በቁሙ ተኝቷል እንጅ አይነቃም፤ ያለ ይመስላል እንጅ የለም፤ ቢቀሰቅሱት አይሰማም፤ ሃይል ጨርሷል!!! ክልሉ በስም እንጅ በክልሉ ህዝቦች አዕምሮ ፈርሷል!!! የሚመለከተው አካል አፋጣኝ እርምጃ ይወሰድ፥ ሁኔታው በመድረክ ውይይት ከመፍታት ደረጃ አልፏል” ሲሉም አሳስበዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopiaregion