የአለም አይኖች ሁሉ 🇺🇸U.S Presidential Election 2024🗳 ካማላ እና ትራምፕ አንገት ለአንገት በተፎካከሩበት አሸናፊው ማን ይሁን ?

ሰሞኑን የነበረው የወራት የአሜሪካ የእጩዎች ቅስቀሳ ፍፃሜውን የሚያገኝበት ዕለት ላይ እንገኛለን። በተለያዩ ሚዲያዎች መረጃዎችን እየተከታተላችሁ መምጣችሁን ስለምጠብቅ ከእውነታ አንፃር እንዴት እንደሚቃኝ እና ስለ ምርጫው ሒደት እና ውጤት የሚታወቅባቸውን መንገዶች እንደሚለተለው እንመልከት።
ምርጫ ዲሞክራሲን ከአምባገነን ስርዓት የሚለየው ህዝብ መሪዎቹን እንዲቆጣጠር እና አብዮት ሳያስፈልግ ከስልጣን እንዲያባርር መብት የሚሰጥ ነው። ይህ ቀን በዲሞክራሲ እሳቤ ለተሰጡን መብቶች ያለንን አድናቆት የምናሳይበት ታላቅ መንገድ ነው።
አሜሪካዊያን ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም. ወደ ምርጫ ጣቢያዎች አምርተው ለፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ድምፃቸውን ይሰጣሉ።
እርግጥ ነው በዩናይትድ ስቴትስ ሰዓት አቆጣጠር መሠረት ምርጫው በአብዛኛዎቹ ግዛቶች ማክሰኞ ከሰዓት አካባቢ ነው የሚጀምረው።
የድምፅ መስጫው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላም አሸናፊው ወይም አሸናፊዋ ለሰዓታት ላይታወቁ ይችላሉ። ሰዓታት ብቻ አይደለም፤ ቀናት አሊያም ሳምንታት ሊወስድ ይችላል።
እነሆ ስለምርጫው ውጤት ሊያውቋቸው የሚገቡ ጉዳዮች።
🗳የምርጫው ውጤት መች ነው የሚታወቀው?
የወቅቱ ምክትል ፕሬዝደንት ዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ እና የቀድሞው ፕሬዝደንት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ለሳምንታት አንገት ለአንገት ተናንቀው ቆይተዋል።
የምርጫው ቀን ቢቃረብም በብሔራዊው እና ወሳኝ በሚባሉ ግዛቶች ያለው የነጥብ ልዩነት አሁንም ጠባብ ነው። በሁለቱ ዕጩዎች መካከል ያለው የውጤት ልዩነት እጅግ ጠባብ ከሆነ ድምፅ ድጋሚ ሊቆጠር ይችላል።
የምርጫውን ውጤት ለመውሰን ወሳኝ ናቸው የሚባሉት ሰባት ግዛቶች እንዴት ነው ድምፅ የሚቆጥሩት? የሚለውም ወሳኝ ነው።
በሌላ በኩል እንደ ሚሺጋን ያሉት ግዛቶች የድምፅ ቆጠራቸውን እያፋጠኑት ነው። በርካታ ግዛቶች በኮቪድ ጊዜ በፖስታ ነበር ድምፅ የሰበሰቡት። ነገር ግን ይህ አሁን እየቀነሰ ይገኛል።
የምርጫ አሸናፊ በድምፅ መስጫው ምሽት፣ አሊያም በነጋታው ካልሆነ ደግሞ ከቀናት ወይም ከሳምንታት በኋላ ሊታወጅ ይችላል ማለት ነው።
🗳የምርጫ 2020 ውጤት
ያለፈው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ በአውሮፓውያኑ 2020 ማክሰኞ ኅዳር 3 ነው የተደረገው። ነገር ግን ጆ ባይደን አሸናፊ መሆናቸው የተሰማው ቅዳሜ ኅዳር 7 ቀን ነበር።
በድምፅ መስጫው ቀን የትራምፕ ደጋፊዎች ዕጩው ፕሬዝደንት እንዳሸነፉ እርግጠኛ ነበሩ። ሁለቱም ዕጩዎች ፕሬዝደንት መሆን የሚያስችላቸውን ድምፅ ለማግኘት ከጫፍ ደርሰው ነበር።
አብዛኞቹ ግዛቶች ድምፅ በተሰጠ በ24 ሰዓታት ውስጥ ውጤት ቢያሳውቁም ፔንሲልቬኒያ እና ኔቫዳን ጨምሮ በተወሰኑ ግዛቶች ቆጠራው ቀናት ወስዷል።
19 ኢሌክቶራል ኮሌጅ ያላት ፔንሲልቬኒያ ወደ ዲሞክራቶች ማድላት ጀመረች። ቅዳሜ ጥዋት ነው የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ጆ ባይደን አሸናፊ መሆናቸውን ያወጁት።
ሲኤንሲኤን ባይደን ማሸነፋቸውን ያወጀ የመጀመሪያው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ 15 ደቂቃዎች ሌሎች ጣቢያዎችም ይህን ዜና ሰበሩ።
🗳ቁልፍ ግዛቶች
የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚወሰነው በጥቂት ግዛቶች በሚገኝ ድምፅ ነው።
ለዚህ ምክንያቱ ኢሌክቶራል ኮሌጅ የተባለው ሥርዓት ነው። ይህ ማለት አሜሪካ ፕሬዝደንቷን የምትመርጠው ዕጩዎች በሚያሸንፉት ግዛት መሠረት ነው። አብዛኛዎቹ ግዛቶች ዲሞክራት አሊያም ሪፐብሊካን ናቸው።
ዘንድሮ በጣም ወሳኝ የሚባሉት ግዛቶች ሰባት ናቸው። እነሱም አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ዊስኮንሲን፣ ፔንስሊቪኒያ እና ሚሸጋን ናቸው። ባለፈው ምርጫ ባይደን በአሪዞና እና ጆርጂያ ግዛቶችም ማሸነፋቸው ይታወሳል።
ኔቫዳ ግዛትም እንዲሁ ለሁለቱም ያላደላች ብትሆንም የሕዝብ ብዛቷ አነስተኛ መሆኑ አስፈላጊነቷን ዝቅ ያደርገዋል።
ፍሎሪዳ እና ኖርዝ ካሮላይና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ሪፐብሊካን ፓርቲ አድልተዋል። ቨርጂኒያ እና ኮሎራዶ ደግሞ ወደ ዲሞክራቲክ ፓርቲ አዘንብለዋል።
🗳ድምፅ የሚቆጠረው እንዴት ነው?
ብዙውን ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው በምርጫው ቀን ለሚሰጡ ድምፆች ነው። ቀጥሎ ደግሞ ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት የመረጡ እና በፖስት ድምፃቸውን ያስገቡ ሰዎች ቆጠራ ይካሄዳል።
ከውጭ ሀገራት እና ከወታደራዎ ካምፖች የሚላኩ እንዲሁም ድጋሚ እንዲቆጠሩ የተደረጉ ድምፆች ይከተላሉ።
የአካባቢ የምርጫ ባለሥልጣናት አንዳንዶቹ የተሾሙ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ተመርጠው የመጡ ናቸው።
እነዚህ የምርጫ አስተባባሪዎች ናቸው
አስተባባሪዎች የተሰጠውን ድምፅ እና የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ያመዛዝናሉ፤ መረጃዎችን ያጣራሉ፤ ጉዳት የደረሰባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን ይፈትሻሉ፤ አለመመሳሰል ካለበት ደግሞ ምርመራ ያደርጋሉ።
ወረቀቶቹ ወደ ኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ገብተው ውጤታቸው እንዲቆጠር ይደረጋል። አንዳንዶቹ ድምፆች ደግሞ በእጅ ሊቆጠሩ ይችላሉ።
ድምፁ ትክክለኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ መጀመሪያ በክፍለ-ግዛት ቀጥሎ ወደ ግዛት ይሸጋገራል።
አዲስ የሚመረጡት ፕሬዝደንት በአውሮፓውያኑ ጥር 20/2025 ቃለ-መሐላ ይፈፅማሉ።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ እውነታዎች፦
🗳የድምጽ መስጫ ማሽን ለመጠቀም የመጀመሪያው ምርጫ በ1892 ነበር።
🗳ጆርጅ ዋሽንግተን የፖለቲካ ፓርቲን የማይወክል ብቸኛው ፕሬዝዳንት ነበር።
🗳አብርሃም ሊንከን 6 ጫማ፣ 4 ኢንች (1.9 ሜትር) ነበር፣ ይህም የዩናይትድ ስቴትስ ረጅሙ ፕሬዝዳንት አድርጎታል።
🗳የመጀመሪያው ግራኝ ፕሬዝዳንት 20ኛው ፕሬዝደንት ጄምስ ጋርፊልድ ነበሩ።
🗳13ኛው ፕሬዝደንት ሚላርድ ፊልሞር የእንጀራ እናት የነበራቸው የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ነበሩ።
🗳የህክምና ዶክተር ለመሆን የተማረው ብቸኛው ፕሬዝዳንት ዘጠነኛው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሄንሪ ሃሪሰን ናቸው።
🗳ከ 1845 በፊት ስቴቶች በ 34 ቀናት ውስጥ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎችን በ 34 ቀናት ውስጥ በኖቬምበር የመጀመሪያ ረቡዕ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ ስርዓት ችግር ያለበት እና አንዳንድ ጉድለቶች ነበሩበት። ግንኙነቶች እና መጓጓዣዎች ተሻሽለው ነበር፣ ይህም በተለያዩ የሰዓት ዞኖች ውስጥ ባሉ ድምጾች ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።
🗳46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዴሞክራቲክ ፕሪሚየር ምርጫ ካሸነፉ በኋላ በሀገሪቱ ታሪክ ከ2024 ፕሬዚዳንታዊ ውድድር ያገለሉ ብቸኛው ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
ከዓለም ትልቅ ሁነቶች መካከል አንዱ የሆነው የአሜሪካውያን ምርጫ ዛሬ በተለመደው የምርጫ ሒደት ይካሔዳል። ጥቂት የማይባሉ አሜሪካውያንም የመረጥነው ሰው ባያሸንፍስ ከሚል እሳቤ እና ግጭት ሊነሳ ይችላል ከሚል ፍርሀት እየተጨነቁ እንዳሉ ትላንት የወጡ ዘገባዎች አመላካችነታቸው አይዘነጋም።
Source:- bbc , cnn , world election , the whitehouse