ፓርቲው የዎላይታ፣ የምእራብ ኦሞ፣ የዲራሼና የኮንታ እጩዎችን በከፊል ይፋ አደረገ
በዚሁ መሠረት ፓርቲው የህዝብ ይሁንታ ያላቸውን፣ የዳበረ የስራ ልምድና የዳበረ የአመራር ጥበብ ያላቸውን እጩዎች ይዞ ቀርቧል፡፡
ፓርቲው ያቀረባቸው እጩዎች የበለጸገችውን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የሚደረገውን ሁሉ አቀፍ ጥረትና ርብርብ ጠንቅቀው የሚረዱና በተግባርም የተፈተኑ በመሆናቸው መራጩ ህዝብ ቀድሞ እንዲተዋወቁ ይፋ አድርጓል፡፡
ፓርቲያችን በወላይታ ዞን 11 እጩዎችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ ዶክተር አሰለፈች ኩቼ እና ሌሎች ሰባት እጩዎችን ለተወካዮች ምክር ቤት በጥንቃቄ መርጦ አቅርቧል ተብሏል፡፡
ብልጽግና በዎላይታ ዞን ለክልል ምክር ቤት 39 እጩዎችን አቅርቧል፡፡ ከቀረቡት መካከል ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ፣ አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ አቶ አብርሀም ደምሴና አቶ አክሊሉ ለማ ይገኙበታል፡፡
በምእራብ ኦሞ ዞንም ፓርቲያችን አራት እጩዎችን ለህዝብ ተወካዮች ያቀረበ ሲሆን ሰባት እጩዎችን ደግሞ ለክልል ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ወይዘሮ አረጋሽ ክፍሌ፣ አቶ ፍቃዱ በድሉ፣ አቶ እሸቱ ገ/ማሪያም፣ ወይዘሮ ትደነቅ ጉልዱ ለተወካዮች ምክር ቤት፤ አቶ ባርዱላ ኦለኪቦ፣ አቶ ፋጅዮ ሳፒ፣ ወይዘሮ አልማዝ ገበየሁ እና ሌሎች አራት እጩዎች ለክልል ምክር ቤት እንደቀረቡም ተገልጿል፡፡
ፓርቲው በዲራሼ ልዩ ወረዳም አቶ ፍሬው ተስፋዬና ወይዘሮ ይፍቱ ጉድሳን ለህዝብ ተወካዮች በእጩነት ያቀረበ ሲሆን ወይዘሮ አማረች አየለ፣ አቶ ዘነበ ሳጎያ፣ አቶ ታማሳ ታምራትና ሌሎች ሁለት ሰዎችን ደግሞ ለክልል ምክር ቤት በእጩነት አቅርቧል ተብሏል፡፡
በኮንታ ልዩ ወረዳም ፓርቲችን አቶ ኢያሱ ሳላን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት ሲያቀርብ ለክልል ምክር ቤትም አቶ ፋንታሁን ብላቴ፣ ወይዘሮ እንግዳወርቅ ዶኖቾ እና ወይዘሮ የኋላሸት በላይነህ በእጩነት ቀርበዋል ሲል ፓርቲው በፌስቡክ ፔጅ ይፋ አድርጓል፡፡