1000024928

ሰሞኑን ይፋ የተደረገውን ሙስና ቅሌት ለመሸፈን ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምረው እየተሯሯጡ እንደሚገኙ ተጠቆመ!

የህግ አካላትን አሰማርተው ተፈጽሟል የተባለውን የሙስና ተግባር ማጣራትን ትተው በነገው ዕለት በዲላ ማዕከል ያለዉ አመራርና አባላት አስቸኳይ ሰብሰባ መጠራታቸውም ተገልጿል።

ጠያቂ የሌለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ከፋፋይ አጀንዳ በመቅረጽ እመራለዉ የምለውን ህዝብ በየግዜው እያዋከበ ቅጥ ያጣ ብልሽትና በሙስና ቅሌት ስለመዘፈቁ ባለፉት ሳምንታት ሙስናን በምጠየፉ ሠራተኞችና አመራሮች አማካይነት መረጃው ለሕዝብ በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በኩል ይፋ ሆኗል፡፡

ከፍተኛ የሙስና ተግባር ከሚፈጸምባቸው ቢሮዎች አንደኛው የዉሃ ማዕድንና ኢኔርጂ ቢሮ የማዕድን ሀብት ዘርፍ ሲሆን ይሄ ዝርፍያና ብዝበዛ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ ብዙዎች የተሳተፉበት እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በመሆኑም “ይሄን ነዉር ዉጫዊ ለማድረግና የሌላ አካል ብልሽት ለማስመሰል ርዕሰ መስተዳድሩ ያልገባበት ቦታ የለም። ለማሳሳት ያልሞከረዉ አካልም ጥቂት ነዉ። የሆነ ሆኖ በእሳቸው ትዕዛዝና እውቅና የተመራዉን ብልሽት ወደ ሌላ ለማላከክ ከትዉልድ ቀያቸዉ እስከ አገር አቀፍ ቢሯሯጡም የማይመለስ ደረጃ ደርሷል። እሳቸዉንና ተባባሪዎችን ግልጥልጥ አድርጓል” ሲሉ ምንጮቻችን አረጋግጧል።

”ዉሸትና ዉፍረት ለባለቤቱ አይታወቅም” እና እንደ መንግስት እጃቸው ንጹህ ከሆነ የህግ አካላትን አሰማርተው ተፈጽሟል የተባለውን የሙስና ተግባር በማጣራት ፈንታ ሰኞ በዲላ ማዕከል ያለዉ አመራርና አባላት አስቸኳይ ሰብሰባ ተጠርተዋል” በማለትም ስለሁኔታው አስረድቷል።

ሌላኛው ለእሳቸው ቅርብ የሆነ አንድ ከፍተኛ አመራር መረጃ እንዳጋሩት የስብሰባዉ አጀንዳ “የሌብነት ድርግት መረጃ ያወጡ አመራሮች ላይ እርምጃ ወስደናል። እኛ ከደሙ ነፃ ነን። ፈጣሪ ከሰማይ እንደምያየኝ ምንም ሙስና የለም። እኛ ክልሉን የሰላም የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ነው። አንዳንድ ሚዲያዎች በፈጠራ ወሬና በሴራ ይዘምታሉ። እነዝያን ሚዲያዎች አትስሙ” የሚል እና ሌሎች ማደናገርያ ሀሳብ ለማሰማት እንደሆነ ታውቋል።

ይሄ የማደነጋገርያ እንቅስቃሴ ለሳቸዉ አይታወቅ ይሆናል እንጅ ለሰፍዉ ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ የአደባባይ ምስጥር ነዉ።
ወይም እንደ ስብዕናቸው ራሳቸውን ነጻ በማውጣት ሥርአት አልበኛ የሆነውን ቢሮ ተጠያቂ ሊያድርጉ ይችላሉ? የምለው ዘውትር ጥያቄያችን ይሆናል። ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩን እስከመጨረሻው ተከታትሎ መረጃ ማድረሱን ይቀጥላል። #Ethiopia #southethiopia