
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ500 ሄክታር በላይ መሬት ከክልሉ ሆነ ከእንቨስትመንት አሰራር ውጪ በጥቅም ትስስር በአንድ ድጋፍ ደብዳቤ ለግለሰቦች እየተላለፈ እንደሆነ ሰነዱ አረጋገጠ።
ይሄንን ህግወጥ ትዕዛዝ በበላይነት የመሩት የቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ እንዲሁም የወቅቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዱ የተባለ ግለሰብ እንደሆነ ከሰነዱ ለማወቅ ተችሏል።
ይሄንን ከ500 ሄክታር በላይ የማዕድን ልማት መሬት ከክልሉ ሆነ ከእንቨስትመንት አሰራር ውጪ በጥቅም ትስስር ለግለሰቦች በአንድ ደብዳቤ ትዕዛዝ ሲሰጥ “በዞናችን በተለያዩ አካባቢዎች የድንጋይ ከሰል ማዕድን ከምችት መኖሩ በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን በተለይ በቦረዳ ወረዳ ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ለማምረት ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ የሚገኘው ማራ ማይንግ ኃላፊነት የተ/የግል ማህበር ለጥናት ይዞ ከነበረው 600 ሄክታር ላይ ለድርጅቱ 10 ሄክታር ብቻ በማስቀረት ሌላው ለጋሞ ልማት ማህበር እንዲሁም በዞኑ በግልም በማህበርም የድጋፍ ደብዳቤ ለወሰዱ ተሸንሽኖ እንድሰጣቸው የዞኑ አስተዳደር ምክር ቤት ባደረገው ሰብሰባ መወሰኑ ይተወሳል ሲል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ይሄንን ተከትሎ በክልሉ በቦሮዳ ወረዳ ማራ ማይኒንግ ኃላፊነት የተወሰነ ማህበር በህጋዊ መንገድ የተረከበውን ቀጥታ በህግ ወጥ መንገድ ለሌሎች በመሸንሸን ለመስጠት በመሞከሩ ማህበሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዘው በመሄድ በክርክር ሂደት እያለ ተጨማሪ ሽንሸና እና ዝርፊያ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉዳዩ ዙሪያ አንድ የዘርፉ ባለሙያ ከህግ አንፃር ጠይቀን ሲያስረዳ፦ “በማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንት ሕጉ መሠረት በቅድሚያ አንድ ባለሀብት የማዕድን ቅኝት (Exploration) ሕጋዊ ፈቃድ ከእነ ኮኦርድኔት ነጥቦች ጋር ከተሰጠ በኋላ፣ የፀደቀ የአዋጭነት ጥናት ሰነድ፣ የአከባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ሰነድ፣ የማልማት አቅም፣ የንግድ ምዝገባ ሰነዶች ከቀረቡ በኋላ አስቀድሞ የተፈቀደው የተፈቀደው ይዞታ መጠን ሊቀነስ አይችልም።
ነገር ግን ባለሀብቱ የማምረት አቅሙ ደካማ ከሆነ፣ በራሱ ፍላጎት ይዞታው ይቀነስልኝ የሚል ጥያቄ ካቀረበ፣ በአከባቢው ማህበረሰብና ሥነምህዳር ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱ በጥናት ከተረጋገጠ፣ ከይዞታው ሊቀነስ ይችላል። ከዚህ ውጭ ከልማታዊ ባለሀብት ቀንሰው፣ በጥቅም ትስስር ለሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት ማስተላለፍን ሕጉ አይፈቅድም” በሚል አብራርተዋል።
ሰሞኑን በክልሉ በማዕድን ዘርፍ እየተደረገ የሚገኘውን ህገወጥ ዝርፊያና አሰራር በተመለከተ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተከታታይ እያጋለጠ ሲሆን መረጃ አውጥቷል ያሏቸውን አመራሮች ጭምር ከኃላፊነት እያነሱ እንደሆነ መዘገቡም ይታወሳል።
ክልሉ የፍርድ ቤት ክርክር ሂደት እያለ ህግን በመጣስና የፍርድቤት ትዕዛዝ በመናቅ ከህጋዊ ማህበር በህገወጥ መንገድ ለሌሎች በገንዘብና በጥቅም እያስተላለፉ የሚገኘውን የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙስና ቅሌት በተመለከተ የሚመለከተው የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ የህግ የበላይነት እንዲያስከብር እናሳስባለን።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በርዕሰ መስተዳደሩ ደረጃ በየጊዜው በሚፈጠሩ ህገወጥ አሰራር ስንመለከት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሌሎች በመግፋት በአከባቢዊነት ግልጽ የመንግሥት አሰራር በመጣስ የዝርፊያ፣ የህገወጥ አሰራር መለማመጃ እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይቀር የማይከበርበት ጋጠወጥና ህግ የሌለበት ደረጃ ደርሷል።
ውድ ተከታዮች በዚሁ ጉዳይ ላይ እልባት እስኪገኝ ድረስ ዝርዝርና ተከታታይ መረጃ ማቅረባችን አጠናክረን እንቀጥላለን።