
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው
በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ለድሃ የሴፍቲኔት ተጠቃሚ ወገኖች ከአለም ባንክ በድጋፍ የሚሰጠው ገንዘብ “ለድሆች ሳይሆን ለከተማ አመራሮች ገቢ ምንጭ ሆኗል” ተብሏል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዲላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራአስኪያጅ የሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ገንዘብ በስራ ለተሰማሩ ሰራተኞች ተገቢ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ከመስጠት ይልቅ የባለስልጣናቱ ጉድለት ማሟያ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከስፍራው ደርሷል።
መረጃ እንደሚያሳየው ለሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችና ለስራው አጋዥ ቁሳቁስ ገዢ ጨምሮ አስፈላጊ ጉዳዮች እንዲውል የሚላከው ሙሉ ፓኬጅ በማዘጋጃ ቤቱ ስራአስኪያጅ አማካኝነት በየሳምንቱ አንዳንዴ ደግሞ በሳምንት ሁለት ሶስት ግዜ ለከተማ ስራአስፈፃሚዎችና ለፋይናንስ ቁልፍ የስራ ባልደረቦቻቸው ከ10,000 እስከ 25,000 ሺ ብር አበልና የውሸት ስብሰባ እየተባለ እየተሰራ፣ በፕሮግራሙ ተጠቃሚ መሆን የማይችሉት እንዲገቡ እንዲሁም አድረሻ በማይታወቁ ተጠቃሚዎች ጭምር ደመወዝ መክፈልም እንደሚገኝበት ተገልጿል።
ለድሃ ከአለም ባንክ የሚሰጠው ገንዘብ ለባለስልጣናቱ ልዩ መቀለቢያ በመሆኑ በከተማ የፊት ስራአስፈፃሚ አመራሮች “የማዘጋጃ ቤት ስራአስኪያጅና ሂሳብ ሰራተኞች የሚደረገው እንክብካቤ ከእንቁላሉ አስኳል በላይ ነው” ስሉ የመረጃ ምንጫችን ገልፀዋል።
እንደ አስተያየት ሰጭያችን መረጃ “ይህ ገደብ የሌለው የሴፍቲኔት ገንዘብ ብዝበዛ ከማዘጋጃ ውጪ ባሉ መስሪያቤቶች ሃላፊዎች ላይ አደጋ እንድደቀን ምክንያት ሆኗል” ስል ገልፀዋል።
ምን አይነት አደጋ ነው የሚደቀነው ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ “በተለይ ለዲላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ እና ሌሎች አስተባባሪ አካላት ልዩ ልዩ አስራትና በኩራት የማይሰጡ ሌሎች መስሪያቤቶች በማዘጋጃ ልክ ጥቅማጥቅም ስለማይሰጡ መስሪያቤቶችን የሚመሩ ሃላፊዎች ያለምንም ምክንያትና ያለ ምንም ጥፋት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ እየተደረጉ ይገኛሉ” በማለት ገልፀዋል።
ለእነኚህ የጉልበት ስራ ሰርተው ከሰፍቲኔት ፕሮግራም ጥቅም የሚያገኙ ድሆች “በሶስት አመት ውስጥ አንድ ግዜ ልብሳቸው እንደማይቀየርላቸው፤ የግብዓት ማሟያ ገንዘብ ለምን ጥቅም እንደሚውል እንደማይታወቅ እና በብዙ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ የከተማ ብልጽግና ፓርቲ አመራር እየተበዘበዘ ይገኛል” ስሉም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልፀዋል።
ባሳለፍነው ሳምንታት የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አባት ከነበረው ቀበሌ ቤት ወደተሻለ ቁጠባ ቤት አዘዋውረው ቤቱን አፍርሰው ለማሳደስ ለወጣው ወጪ በተለያዩ ሰዎች ስም ከዚህ ከሴፍቲኔት ገንዘብ በአበል መልክ ተሰርቶ የብሎኬት መግዣ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
በመሆኑም “በእነዚህ አጥፊዎች ላይ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢ እርምጃ ተወስደው ለእነዚህ ለሴፍቲኔት ተጠቃሚ ድሃ ማህበረሰቦች ጥቅማቸው እንዲከበር በማድረግ ለከተማዋ ውበትና ዕድገት ወሳኝ የሆነው ሰፍቲኔት ፕሮግራም ከአላማው አንፃር በተገቢው መመራት አለበት” በሚልም የመረጃ ምንጫችን አሳስበዋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
Ethiopia #southethiopia #dila
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው