1000026253

“የአርባምንጭ አከባቢ ፖለቲከኞች የዎላይታን ፖለቲካ የሚፈሩት ነፃ እየወጡ የቀሩ ብሄረሰቦች ነፃ የሚወጡበት ዕድል ያስገኛሉ በሚል ስጋትና ጭንቀት ነው” – የዎጋጎዳ ትግል መሪ አባል

ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም የሰሜን ኦሞ መዋቅር መፍረሱን ተከትሎ እየተባባሰ የመጣውን የሁለቱ አከባቢ ፖለቲካ ፉክክር በተመለከተ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በመንግስት ደረጃ ካለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ባሻገር መሠረታዊ የፉክክሩ መነሻ ምክንያት ምንድነው የሚለውን ምላሽ ለማግኘት በወቅቱ የነበረውን የጭቆና መዋቅር ለማፍረስ ታግለው ውጤት ካመጡት መካከል አንዱን ጠይቀን ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እኚሁ አንቱ የተባሉ በአሁኑ ወቅት ወደ 65 ዕድሜ የተጠጉና ትግሉን የመሩና የተሳተፉ ሰዎች መካከል አንዱ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እንደገለፁት “ጋሞ ማለት አርባምንጭና ዙሪያዋ ነች፥ ድሮ ከዎላይታ እስከ ዳውሮ ከኮንታ እስከ ጎፋ ብሔሮችን በሙሉ በመጠፈር ሰሜን ኦሞ በሚባል የጥርነፋ እስር ቤት ተደርጎ ያቺ በወበቅ ከአንድ ቀን በላይ ሰው ሊያሳልፋባት የማይችላትን ከተማ ብቻ አሳድገው በጀርባው ደግሞ ጋሞ የሚባልን ብሔር ብቻ የሰፋ አድርጎ በመሳል ከሁሉም በቁጥር የሚበልጠውን ዎላይታን በማሳነስ ሌሎቹንም ጭራሽ ደብዛቸውን በማጥፋት ጋሞን ብቻ የአካባቢው ትልቅ ብሔር የማስመሰል ሴራ በከፍተኛ ሁኔታ ሲሰራ ስለነበር ትግሉ የማይቀር የህልውና ጥያቄ በመሆኑ ለማቀጣጠል ወስነናል” በሚል ያስረዳሉ።

በዚህ የተበረታቱት የጋሞ ብሔረሰብ ፈጣሪ አባላት በወቅቱ የሌሎቹም ቋንቋ ጠፍቶ የጋሞ ቋንቋ የአካባቢው ቋንቋ መሆን አለበት በሚል ዎጋጎዳ የሚባል የፈጠራ ወፍኛ ቋንቋን እንደፈጠሩም ታጋዩ ያብራራሉ።

አክለውም አሁን ጋሞዎች በዎላይታ ሕዝብ ጥላቻ ተቃጥለው የሚንገበገቡት ዋንኛው ምክንያት ምንድነው ቢባል መልሱ ይህ ነው ይላሉ፦ “ትናንት በክልልነት ትግሉ ጊዜም የአካባቢው ሌላው ሁሉም ብሔር በኩሽና በተደበቀበት ወቅት ለመብቱ አደባባይ ወጥቶ በመታገል የፌዴራል መንግስቱን ጥይት ያስተናገደውና ውድ ልጆችን እስከመሰዋት ትግሉን በቁርጠኝነት ያከናወነው ዎላይታ እንደመሆኑ መጠን ይህንን ቆራጥነቱን በ1992 ዓ.ም በተመሣሣይ ሁኔታ ዎላይታ ፈፅሞ ያንን የጋሞዎቹን የጥርነፋ እስር ቤት ሰባብሮ የወጣው ይሄው የጦና ሕዝብ አንበሳው ዎላይታ ብቻ ነበር” ብለዋል።

“ይሄውልህ ልጄ፦ በወቅቱ በዎላይታ ወደ አራት የሚሆኑ ምሁራን ተሰውተው መላ ዎላይታ ለትግል ተነስቶ ዎጋጎዳን ድባቅ መትተን በማስወገድ ብቻ አላበቃንም ነበር…. ጋሞ ይሁን ሌላ ብሔር ድጋሚ በሌላኛው የአካባቢው ብሔር እንዲህ ዓይነት የጭቆና ሃሳብ እንዳያስብ ለማድረግ አንድ መሠረታዊ ስራ መሠራት ነበረበት። እናም ያንን ስራ በወንድማችን በታላቁ ፍሬው አልታዬ የተመራው የዎላይታ ሕዝብ በመሠረታዊነት ለውጦ ሰርቶታል” በሚል ታሪክን በኩራት ያወሳሉ።

ይህም የመዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት ነበረ…..በመሆኑም ዎላይታ ቀድሞ የዎላይታ ዞን የሚባል መዋቅር አቋቋመ (አልተፈቀደም እንጂ እሱማ በፍሬው አቅጣጫ አመላካችነትና በሃገር ሽማግሌዎቻችን አማካኝነት በወቅቱ ለነበሩት ጠቅላይ ሚኒስቴሩም ሆነ ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ገብቶ የነበረው ደብዳቤ የክልልነት መዋቅር ነበር)…..

…. ሆኖም ዎላይታ ዞንነትን አረጋገጠ። ልብ በል ልጄ፦ የዚህ ድል ፋይዳው ለዎላይታ ሕዝብ ብቻ አልነበረም። በወቅቱ ዎላይታ ሕይወቱን ሰውቶ ይሄንን ድል ያመጣው ሆኖ ያልታገሉትና አንዲት ጥይት ያልተተኮሰባቸው ወንድም የዳውሮ ሕዝብ የዎላይታ ትግል በቀደደላቸው ዕድል ተጠቅመው ምንም ዋጋ የሚያስከፍል ትግል ሳያካሄዱ በአርምንጭ ስር ከታሰሩበት እስር ቤት ከዎላይታ ጋር የራሳቸውን ዞን መዋቅር ተፈቅዶላቸው ነፃ ወጡ።

ዎላይታ በታገለው ለአካባቢው ሌሎችም ወንድም ሕዝቦች መንገድ ከፈተ። እኔ ሁሌም የምናደደው ይህ የዎላይታ ሕዝብ ውለታ በአግባቡ ያልተነገረና ዎላይታ ለአካባቢው ምን ያህል ጠቃሚ ሕዝብና የዲሞክራሲ መንገድ አለማማጅ የነበረ ሕዝብ መሆኑ ሁሌም እንደቆጨኝና ፀሐፊ ሆኜ ይህንን ውለታ በመፅሐፍ አሳትመው አሳትመውና አሰራጭ ያሰኘኛል በዕውነቱ።

ለዚህ የዎላይታ ሕዝብ ውለታ የመጀመሪያዎቹ የዳውሮ ዞን አስተዳዳሪዎች ዛሬም በሕይወት ያሉት እነ አቶ #ዳመነዳሮታ ሕያው ምስክር ናቸው በዕውነቱ። እነ አቶ #ሳሙኤልሃላላ ህያው ምስክር ናቸው።

ቀጠለና ሌላኛው ብሔር የሆነው ኮንታም በልዩ ወረዳነት ቋንቋውን፥ አለባበሱን፥ ጭፈራውን…. ማንም ሳይጨፈልቅበት እንደያዘ ራሱን አስከብሮ ወጣ!! ለዚህ ድል የትግሉ ፈር ቀዳጅ ሆኖ ዎላይታ ባይጀምረው እስካሁን የሌሎቹ ቋንቋ ጠፍቶ ጉዳያቸውን ለማስፀም ወደ አርባምንጭ እየተመላለሱ ይኖሩ እንደነበረ ግልፅ ነው።

ልጄ ዎላይታ|ኮ ባለውለታ እንጂ የዛሬ ተወላጆች የትናንቱን የዎላይታን ውለታ የማያውቁት ሌላ ነገር ሲያወሩ ስትሰማ የምታዝነው በባለማወቃቸው እንጂ በሌላ አደለም። ቀጠለና ጎረቤት ወንድሞች ጎፋ|ም ከትንሽ መዘግዬት በትግል በኋላ ራሱን ችሎ በዞንነት ወጣ።

ነገር ግን አሁንም በዞኑ በፊት ነፃ እየወጡ በጫና የቀሩ የተለያዩ ነባር ብሄር ብሄረሰቦች ለዘመናት ማንነታቸው ባልወከሉት ( ቁጫ፣ ቦሮዳ፣ ጋንታ፣ ዶርዜ፣ ዘይሴ፣ ካምባ፣ ቦንኬ፣ ኦቾሎ ብሄረሰቦች ) ታፍነውና ማንነታቸው ተደፍጥጠው የሚኖሩበት በዚህ እስርቤት ማንነታቸው እንዳይታወቅ ከፍተኛ ስቃይና አፈና እየተካሄደ መሆኑ የአርባምንጭ አከባቢ ፖለቲከኞች የዎላይታን ፖለቲካ የሚፈሩት ነፃ እየወጡ የቀሩ ብሄረሰቦች ነፃ የሚወጡበት ዕድል ያስገኛሉ በሚል ስጋትና ጭንቅ የመነጨ ነው” ሲሉም የዎጋጎዳ ትግል መሪ አባል ጠቁመዋል።

ታጋዩ ጨምረውም፦ “የትኛውም ብሄር አባል ለወጣበት ማህበረሰብ ከመታገል ባሻገር፦ እንዲህ በራሳቸው ማንነት የሚኮሩ እንዲሁም ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚጠይቁትን ያፈነ ከድሮ ሴራኞች እጅ ያልወጣ ፀረ ፌደራሊዝም በሆኑ ሰዎች አስተሳሰብና ሴራ ተደራጅተው መብታቸውን የነፈጉትን ለማሸነፍ በሚደረገው ተፈጥሯዊ መብት ትግል ደጋፊ መሆን ወንጀል ወይም ጥላቻ ሳይሆን ለፍትህና ለሰብዓዊነት መቆም ስለሆነ በታሪክ አደባባይ ሁልጊዜ በኩራት እንናገራለን” ብለዋል።

“እንግዲህ በአጭር ቋንቋ ለምን የአርባምንጭ አከባቢ ፖለቲከኞች በዎላይታ ላይ ጥላቻን አተረፉ ካልከኝ መልሱ ይህ ነው ልጄ” በሚል ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም የሰሜን ኦሞ መዋቅር መፍረሱን ተከትሎ እየተባባሰ የመጣውን የሁለቱ አከባቢ ፖለቲካ ፉክክር በተመለከተ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መሠረታዊ የፉክክሩ መነሻ ምክንያት ምንድነው የሚለውን ምላሽ ለማግኘት በወቅቱ የነበረውን የጭቆና መዋቅር ለማፍረስ ታግለው ውጤት ካመጡት መካከል አንድ ተጋይ ጋር ባደረግነው ቆይታ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #dawuro #konta #Wolaita #Gofa #Gamo #Kucazone