1000026333

ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ከፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጋር- የፖለቲካ ወጌሻ ዝግጅት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “በዎላይታ ሕዝብ ላይ ተጭኗል” ለማለት የሚያስችሉ ምክንያት የሚሏቸዉን ነገሮች ቢጠቅሱልን ? መንግስት የመዋቅር ጥያቄዎች በሙሉ ፈትችያለሁ እያለ ባለበት በአሁኑ ወቅት እየተካሄ ባለው ሀገራዊ ምክክሩ ላይ የዎላይታ ክልል ጥያቄ እንደ አጀንዳ ከእንደገና እንዴት ሊቀርብ ቻለ? ህዝቡ በግድ ተፈጥሯዊና ህገመንግስታዊ መብት ተጥሶ የተጫነበትን መዋቅር አስወግዶ ነፃነትን የሚያስከብረው መቼ ይሁን ?እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ምላሽና ቁምነገሮችን ይዘናል ቀጥታ ወደ ጥንቅራችን እንግባ👇

ብዙ ተለፍቶበት የተዘጋጀ ጥንቅር ነውና በትዕግሥት እንድታነቡ እንጋብዝሃለን!

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ፕሮፌሰር እንግዲህ እንደወትሮው ጥሪያችንን ተቀብለዉ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ እንላለን። ያዉ የሚዲያችን ቤተሰብ ስለሆኑ ቀጥታ ወደ ጥያቄ ምላሽ እንግባ።

ለመሆኑ መንግስት በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉትን የመዋቅር ጥያቄዎች በሙሉ ፈትችያለሁ እያለ ባለበት በሐገራዊ ምክክሩ የዎላይታ ክልል ጥያቄ እንደ አጀንዳ እንዴት ሊቀርብ ቻለ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ መንግስት ሲያወራ የነበረዉ ዉሸት ስለነበረ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ እንኳን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዛይሴ እና የቁጫ ተወካዮች ያነሷቸዉ ጥያቄዎች ዉሸት በአደባባይ ያረጋገጡ ናቸዉ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በአጭሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ሕዝብ ላይ ተጭኗል ለማለት የሚያስችሉ ምክንያት የሚሏቸዉን ነገሮች ቢጠቅሱልን ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ክልሉን በተለይ በዎላይታ ሕዝብ ላይ ብልጽግና በጉልበት የመሰረተዉ የሚባለዉ በተጨባጭ ማስረጃዎች ላይ በመመስረት ነዉ። ደግነቱ ጀግናው የዎላይታ ሕዝብ በቂ ትግል ከማድረጉም ባሻገር ብልጽግናን በሁሉም ግምባሮች ማኖ አስነክቷል።

  1. ብልጽግና የክልል ጥያቄውን ለመቀልበስ አንድ አመት ሙሉ የደቡብ ክልል ምክር ቤት እንዳይሰበሰብ ከማድረጉም በላይ በዞኑ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዷል።
  2. ሕዝበ ዉሳኔዉ ጸረ-ሕገመንግስታዊ ነበረ ምክንያቱም ትርጉሙ አይታወቅም ነበረ ለምሳሌ ( ጎጆ)። በአቶ አገኘሁ ተሻገር የሚመራዉ የፈደሬሽን ምክር ቤት በዚህ ተጠያቂ ነው።
  3. በዎላይታ የሕዝበ ዉሳኔ አስፈጻሚነት የተመለመሉ ወጣቶች ባካሄዱት በሰላማዊ መንገድ የማደናቀፍ ትግል የተነሳ ሕዝበ ዉሳኔዉ ዉጤቱ እንዲሰረዝ ማድረግ ተችሏል። ብዙዎች ታስረዋል፤ ተሰደዋል።
  4. በሁለተኛው ሕዝበዉሳኔ የሕዝቡ በቋንቋው የመገልገል ሕገመንግሥታዊ መብቱ ተጥሶ አስፈፃሚዎች ከአዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርጓል።
  5. ጎጆ የዎላይታን ክልል ይወክላል በሚል ሕጋዊ ትንታኔ ላይ የተመሠረተ ቅስቀሳ በተወሰኑ የዎላይታ ሊህቃን ተቀስቅሶ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቶ እንደሚያሸንፍ ምልክት ባሳየበት ሁኔታ የሕዝበ ዉሳኔዉን ዉጤት የሚያዛባ ዘገባ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተሠርቷል።
  6. በወቅቱ የምርጫ ቦርድ ፕሬዚዳንት የነበረችዉ ብርቱካን ሚዴቅሳ በምርጫ ጣቢያ ተገኝታ አለስራዋ ከስድስት ወር በፊት ባልወጣ መታወቂያ መምረጥ አትችሉም ብላ ሕገመንግሥታዊ መብት እየጣሰች ዉላለች። ከዛም በተጨማሪ የጎጆን ትርጉም ተጠይቃ አላዉቅም የእኔ ሥራ ማስፈጸም ብቻ ነው ብላም ነበረ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ሌላዉ ከነችግሩም ቢሆን ክልሉ ሲመሠረት ዎላይታ ሶዶ የመጀመሪያዋ ከተማ ተደርጋ ነበረ። በቅርቡ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለከፍተኛ አመራሮች በሰጠዉ ስልጠና ላይ ይሄንን ሽሯል፣ በተደጋጋሚ ስለ ኮሪደር ልማት ሲያወራ በቀጣይ በሁለተኛ ደረጃ ከተማነት ገሸሽ መደረጓን አስቀምጧል። ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን መቀየር ይችላሉ ? የዎላይታ ሕዝብስ የከተማ ጥያቄ እንዲሁ በቀላሉ የሚገፋ ነው ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ መብቱ ባይኖረዉም ያሻዉን እያደረገ ነው። የዎላይታ ሕዝብ ለዘመናት በቀየዉ ትልቅ ከተማ እንዳይሰራ የተጣለበትን ማዕቀብ ለማስቀጠል ያሰበ ይመስላል። እንደለመደዉ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ሕገመንግሥት የጣሰ አካሄድ እየሔዱ ናቸው። የዎላይታ ሕዝብ በተለይ በቅርብ አመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከደረሰበት ጥቃቶች በሁዋላ ይሄንን ግፈኛ ዉሳኔ ማሳለፍ በሕዝቡ ቁስል ላይ እንጨት መሥደድ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ለመሆኑ ዶክተር ዐብይ አህመድ እንዲህ በፈላጭ ቆራጭነት የሚወስነዉ ንጉስ ነው ወይስ ጠቅላይ ሚኒስቴር ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ አንድ ተካልኝ ገዳሙ የሚባል ሰው ሰዉ ዘዉዳዊዉን አገዛዝ ገርስሰናል የሚሉ ቀጥለዉ የመጡ የኢትዮጵያን መሪዎች የሚተችበት መጽሐፍ ርዕስ ምን ይላል መሰለህ “The Republicans on the throne” እናም ፈላጭ ቆራጭነት በኢትዮጵያ የቀጠላ መራራ ሐቅ ነው።

ሕዝብን ከመጋረጃ ጀርባ የሚወሰኑ ተንኮለኛ ዉሳኔዎች መምራት ቀጥሏል፣ የሐገሪቷ ሕዝብ አንድነትም የማይመጣዉ ያለ መሥፈርት በሚወሰኑ ዉሳኔዎች ጭምር ነው፤ ዉስጣቸዉ የብሔር ጭቆና እርሾ ስላለ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ምናልባት መንግስት በታሪክ ዎላይታ ሶዶ በአካባቢው ዋና ከተማ አልነበረችም የሚል መከራከሪያ ካቀረበስ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ የቀኝ ግዛት ዉሎችን አልቀበልም የሚል ትክክለኛ አቋም እንዳላት ይታወቃል። የዎላይተም ሕዝብ የብሔር ጭቆና በነበረባቸዉ እና እንደጠላት በሚታይበት ዘመን የተወሰኑ ዉሳኔዎችን አይቀበልም!!! በግልጽ ሕዝቡን ለመጉዳት የተወሰኑ ናቸዉና።

ሲጀመርኮ በአቶ አገኘሁ ተሻገር የሚመራዉ የፈደሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉትን የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄዎችን የሚያፍነዉ በተዘዋዋሪ የዎላይታን ሕዝብ ይጠቅማል ብሎ እንደሆነኮ የአደባባይ ሚስጢር ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መፍትሔ የሚሉትን ጠቁመዉን ብንጨርስ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ በሁሉም ግምባር በሰላማዊ መንገድ መታገል ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጀምሮ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎቻችንም ሆነ ሕዝባችን መብትና ጥቅሙን ለማስጠበቅ መታገል አለበት። ከእንግዲህ የዎላይታ ሕዝብ የሚገባዉን መብቱን ተነጥቆ ሌላ ከተማ አልምቶ እንደተለመደዉ ይባረራል ብዬ አላምንም። መፍትሔዉ ሰላማዊ እና ሕገመንግሥታዊ ትግል ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏