1000026444

የርዕሰ መስተዳድሩ በባህላዊና በሃይማኖታዊ ልብሶች ያሸበረቁ የማደናገርያ መድረኮች ማብቅያቸዉ መቼ ይሆን?

የሰሞኑ የሚዲያ ዘመቻ የፈጠረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት (ትንሹ አፀ ሚኒሊክ) ጉብኝትና የመሩት የዎላይታ ሶዶ መድረክ በተመለከተ ትዝብቱን ከስፍራው አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መረጃውን አድርሰውናል።

“ለእግዝአብሄርም ሆነ ለሾመዉ ለብልፅግና ፓርቲ ዴንታ የለሌዉ በአርቴፊሻል ማንነት በመገንባት ክልሉን ማተራመስ ዘዉትር ተግባር ያደረገዉ በተላይም የባለፉት ስድስት ወራት በብዙ ሀብት ተዉቦ በተደራጀዉ በዎላይታ ሶዶ ባለዉ ቤተመንግስት ከማደር የአርባምንጭ ፓራዳይዝ ሎጅ የሚቀናዉና ትንሽ ጊዜ ካገኘ ከEBC ስቱዲዮ ጋር ፎቶ ለመነሳት ብቻ ሶዶ የሚመጣዉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ትናንትና ለሆዳቸዉ ያደሩትን የከተማ፣ የዞን አመራሮችንና ስብሰባን ቋሚ የጡረታ ጊዜ መዋያ ያደረጉ ለአበላቸዉ ብቻ የሚኖሩ አስመሳይ ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ “ፈጣሪ ያያል፤ ፈጣሪ ይፈርዳል፤ የሚወራዉ ሁሉ የፈጠራ ወሬ ነዉ፤ እኛ ክልሉን የሰላም የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት እያደረግን እንገኛለን፤ እኔ ባልኖር ይሄ ክልል ይፈርስ ነበር”፤ ወዘተ በተለመዱ ቀልዶች የ3 ሰዓት የብቻዉን ኑዛዜ ይሁን ስብከት ወይ ስልጠና ወይ ቀልድ ብቻ ግልጽ ያልሆነ ድስኩር በማካሄድ መድረኩን አጠቃልሏል፡፡

የርዕሰ መስተዳድሩ የጥላቻ ማዕከል የሆነዉን ዎላይታን የማዳከም የመጀመርያ ስትራቴጅ ያደረገዉ ዎላይታን የሚወክሉ ሁለት የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከአንድ ቀበሌ የመመልመል፤ የጃላ ትርክት ማንዛት እና “እኔ አንተን በዚህ ቦታ የሾምኩትን ኤከለ የሚባል ግለሰብ ከልክሏል” በሚባሉ ትሪክቶች የዎላይታ አመራሮች እርስ በርስ በማፋጀት ለዘላለም እንዳይቀራረቡና እንዳይደማመጡ የማድረግ ሴራዉን በድል ተወጥቷል፡፡

በመቀጠልም በራሱ ብሄር ባደራጃቸዉ የፍትህ፣ የፖሊስ እና የፀረ-ሙስና ተቋማትን ሙስና በብቸኝነት ተወልዶ ያደገዉ በዎላይታ በሚመስል መልክ ለራሱ ተላላኪ አይሆኑም ብለዉ የገመታቸዉን የክልልና የዞን አመራሮችን የማሳደድ እንድሁም በነጋዴዎች ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ የመጣል እንቅስቃሴ አድርጓል፣ እያደረገም ይገኛል፡፡

በዚህም ለዘመናት በዎላይታ ላይ የተመኙትን ሁሉ አቀፍ ጉስቅልና በአንድ ዓመት የሥልጣን ጊዜያቸዉ ለማሳካት የቻሉ ከአፀ ሚኒልክ ቀጥሎ ሁለተኛ አምባገነን ገዥ ሆኖ በዎላይታ ታርክ ላይ ተመዝግቧል፡፡

በስተመጨረሻም ዞኑ ክልሉ ዉስጥ በመሆኑ ከዉጪ ሆኖ ለሚታዘብዉ አካልም ጭምር እስክታይ ድረስ የእሳቸዉ የሴራ ፖለቲካ ዞኑን ከልማት፣ መልካም አስተዳደርና ህግ በላይነት ዉጪ የሆነ ዞን እንዲሆን በማድረጉ ምክንያት የህዝቦች እሩሮና ጩሄት እስከ ፌዴራል መንግስትም በየቀኑ በመዝለቁ የከተሞች የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የፍትህ ንቅናቄ የሚል የማደናገርያ መድረክ እንድዘጋጅ አድርጎ ምንም ስብዕና የለሌዉ ሰዉ በመሆኑ ዓይኑን በጨዉ አጥቦ ከድምቱ ጀምሮ በእርጥብ ሳር በተቀበለዉ ህዝብ ላይ ለማፈዝ መድረኩን በራሱ መርቷል፡፡

የመድረኩ ዋና ዓላማ እዉነት የህዝቡ የፍትህ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ጉዳይን ምላሽ ለመስጠት ነዉ? ወይስ አቶ ጥላሁን ዎላይታ ህዝብ ላይ የጀመረዉ የጥፋት አጀንዳ ሁለተኛ ምዕራፉን ለመጀመር ለቀጣይ ሴራ ህዝቡን ለማሳሳት ያቀደዉ እቅድ ማስፈፀሚያ መንገድ ለመጀመር ማህበረሰቡንና የአመራሩ ስሜትን ለማየት ነዉ?…ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች በደንብ መታሰብ ያለበት ጉዳይ ብሆንም አብዘኛዉ የአቶ ጥላሁን ባህርን በቅርበት የሚያወቁ ሰዎች ለሚቀጥለዉ ሴራ የህዝቡ ሥነ-ልቦና ለመገምገም ነዉ ብሎ ይደመድማሉ፡፡

የመልካም አስተዳደር እና የህግ በላይነት ጉዳይ ቢቆረቁረዉና ሀላፊነት ቢሰማዉ አቶ ጥላሁን ማድረግ የነበረበት፡-

✅ በነባሩ ክልልም ጭምር አገልግሎት እየሰጠ የነበረ በአድሱ ክልል ራሱ እንድዘጋ ያደረገዉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሶዶ ምድብ ችሎት ማስከፈት ነበር፤

✅ በአንተ እጅ አዙር ትዕዛዝ በየቀኑ የሚፈፀሙ የጅምላ እስሮችን ታስቆም ነበር

✅ በፍርድ ቤትም ጭምር እንድፈቱ ተወስኖ በየፖሊስ ጣቢያ እየተሰቃዩ የሚገኙ ዜጎችን እንድፈቱ ማድረግ ነበር፤

✅ ርዕሰ መስተዳድሩ ባለበት ልኖሩ የሚገቡ ተቋማት በአርባምንጭ እንድቋቋሙ አታደርግም ነበር፤

✅ በዞኑ በየቀኑ የሚካሄደዉን ሹም ሽረት ማስቆም ነበር፤

✅ የሀምሌ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸዉን የመምህራንና ሌሎች የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ማስከፈል ነበር፤

✅ ለመ/ራን ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት የተዘጉ ት/ቤቶችን ማስከፈት ነበር

✅ ለጤና ባለሙያዎች ደመወዝና ዲዩቲ ባለመከፈሉ ምክንያት በአግባቡ አገልግሎት የማይሰጠዉን ጤና ኬላዎችን፣ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎችን ችግር መፍታት ነበር፤

✅ በወባ ወረርሽኝ እያለቁ ያሉትን ዜጎች ጉዳይ ያስጨንቅ ነበር

✅ ያንተን አካሄድ የተቃወሙ አመራሮችን ከሀላፍነት የማንሳት፤ የማሳደድ እና ለብሄሩ ሳይሆን ለአንተ ሴራ የሚሆኑ አመራሮችን የማደራጀት ስራ ማቆም ነበር፤

✅ በነሐሴ ወር በይፋ ግንባታ ይጀመራል የተባለዉን የአረካ አየር ማረፍያ ግንባታ ታስጀምር ነበር፤

✅ የሶዶ ከተማ 10 ኪሜ የዉስጥ ለዉስጥ አስፋልት መንገድ ሥራ ለመስራት የተስማማዉን የአስፋልት ሥራ ድርጅት አስቁሜህ ወደ አርባምንጭ አትወስድም ነበር
ሌዊ ግብርና ኮሌጅ ያለዉ አስፋልት መንገድ ተዘግቶ አራት ወራት እንድቆይ አታደርግም ነበር፤

✅ ያንተን ኮርደር ልማት በበጀት ታስደግፋለህ የእኛን 500 ካሜ በፎቶ ሾፒ አታደነጋግርም ነበር

103,410.3 ካሬ ሜትር የአርባምንጭ ከተማ ኢንቨስትመንት መሬት ህጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ ለግል ባለሀብት በማስተላለፍ በምትኩ ሁለት መንታ የግል መኖሪያ ያሰራ የጋሞ ዞን የቀድሞ አስተዳድርን ከማስጠየቅ ፋንታ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ገጽታ ልቀይሩ የሚችሉ፤ ለበርካታ ዜጎች ሥራ ዕድል ልፈጥሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን አሰራርን ባልተከተለ መልኩ አታሳግድም ነበር

✅ በክልሉ ዉሃ ማዕድንና ኢነርጅ ቢሮ ክልላችን አንገት እንዲደፋና በህግና በአሰራር የማይመራ ክልል እስኪመስል የተሰራዉን ዝርፍያ እንድያጣራ ከማድረግ ይልቅ የዎላይታ አመራርን ልያሳስር የሚችል ወንጀል ፍለጋ ላይ ጊዜ አታጠፋም ነበር።

እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ ከድርግቱ አስከፍነት የተነሳ በዞኑ እየተስተዋለ ያለዉን የህዝብ ቅሬታና ተቋዉሞ ለማደነጋገር ማሞ ሌላ መታወቂያዉ ሌላ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ራሱን ለማታለል ካልሆነ በስተቀር፤ ህዝብ እንደ ሆነ እዉነት እና ፍትህ የማይሠራበት ክልል መሆኑን አረጋግጦ ፊትህን ለፈጣሪ ሰጥቶ ጊዜዉን እየጠበቀ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጅ ትልቁና አሳፋርዉ ነገር ሰዉ ተፈጥሮን ሲክድ ለራሱም ለአገሩም ከፍተኛ መከራና እርግማን እንደሚሆን የርዕሰ መስተዳድሩ አሁናዊ ተጨባጭ ሁኔታ ማሳያ ነዉ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በተፈጥሮ ወደ ስልጣን መሄጃ መንገድ ሲመርጥ በነፍሱም፤ በማንነቱም ላይ ዴንታ የለዉም፤ ለአብነት አቶ ጥላሁን በብሔር ማንነቱ ጋሞ አይደለም፤ አለመሆኑ ደግሞ ኃጥያት አይደለም፤ መሆኑም በተለየ ፅድቅ አይደለም፤ ግን እሱ ጋሞ ላለመሆኑ ተጨባጭ እዉነታ ለማያዉቁና ይህን ሚዲያ ለሚከታተሉ ወገኖች 2005 እና 2006 “የአከባብዉ ጋሞ ማህረሰብ ህዝብ ጋሞ ሳይሆን ጋሞ ነኝ በማለት በልጆቻችን ላይ ከፍተኛ በደልና ስቃይ እየደረሰ ያለ አስመሳይ የዞናችን ዋና አስተዳዳር ይነሳልን ከልጆቻችን” ላይ በማለት እስከ ክልል ባሰሙት ቅሬታና ጩሄት ክልሉ በወቅቱ ከነበረበት ከህዝብ መራራ ጩሄትና ጥያቄ መነሻ ከዞን አስተዳዳሪነት አንስቶ ክልል እንዲገባ ማድረጉ የቅርብ ጊዜ ትዉስታ ነዉ።

እሱም የዚያን ጊዜም አቶ ጥላሁን የተፈጥሮ ማንነቱን ክዶ ጋሞ ሆኖ የጋሞ ህዝብም ሆነ የአከባብዉ ሌሎች ብሔሮችን ለማሰቃየት እንደ ማደነጋገሪያ መስፈርት ተጠቅሞ ለማሳካት ያቀደዉ የጋሞ ህዝብን ከዎላይታ ህዝብ ጋር ማጣላት እና እሱ የጋሞ ህዝብ ብቸኛ ጠበቃና ተከራካሪ ራሱን አድርጎ ለማሳየት የሌለ አጀንዳ እየቀረፀ ሲንቀሳቀስ ዉሸትንና ቅጥፈትን የማይፈልገዉ የጋሞ ህዝብ ሴራዉን በመረዳት ከአከባብዉ ማበረሩ ይታወቃል።

በዛን ወቅት ደግሞ ሌላ ማንነት በፍጥነት በመፍጠር “እኔ የጋሞ ብሔረሰብ ስላይደለሁና የጋንታ ብሔረሰብ ባላባት የልጅ ልጅ ስለሆንኩ ነዉ ጋሞዎች ያባረሩኝ በማለት አ/ምንጭ ከተማ የጋንታ ብሔረሰብ ሀብት ናት እኔን ታድጉኝ” በማለቱ ከዚህ የዋህ ህዝብ እዉነትም የኛ ልጅ እንዴት ይገፋል የምል የዋህ እሳቢያቸዉ ከሌላ በማግኘት የጋሞንንና የጋንታ ህዝብ እንዲቃቃሩ ጭምር ምክንያት ሆኖ ማለፉ ይታወቃል።

በአጭሩ ጥላሁን የሚፈልገዉን ጉዳይ ለማሳካት የማይሄድበት ርቀት የለም፤ ምክንያቱም እሱ ሂሳብ ሰርቶ ነዉ፤ ያዉቅበታል ምክንያቱም ጥርስ የነቀለበት ስለሆነ!” በሚል
የሰሞኑ የሚዲያ ዘመቻ የፈጠረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት (ትንሹ አፀ ሚኒሊክ) ጉብኝትና የመሩት የዎላይታ ሶዶ መድረክ በተመለከተ ትዝብቱን ከስፍራው አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን መረጃውን አድርሰውናል።

southethiopia #Wolaita