1000026588

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

አስደንጋጭ ከፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት መርህ ያፈነገጠ አሰራር በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ !!

ከ 2.4 ቢሊየን የሚበልጥ ሀብት ሕዝብ እንዳያውቀው ተሸሽጓል ‼ ምክንያቱ ምን ይሆን ⁉

በዩኒቨርሲቲው የ2017 በጀት ለህዝብ ይፋ ያልተደረገበትን የተሸሸገ ሴራ እና ሚስጢር በዛሬው ዘገባችን በትንታኔ እንዳስሳለን።

በስመ ትጥቅ ትግል በኤርትራ በርሃ በነበሩ በነጋ ልጅ ፕ/ር ብርሃኑ አድሮ ወደ ኢትዮጵያ የተላከው የጥልቁ ሸንቁጤ መንፈስ ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አዘጋለሁ በማለት ሲጩህ መደመጡን በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው በተካሄደ የምክክር መድረክ የተሳተፉ የመረጃ ምንጮቻችን ነግረውናል።

ወደ ዛሬው ትንታኔ ዜናችን ስንሻገር የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እና የማፍያ ስብስብ ግብረ አበሮቹ ዩኒቨርሲቲውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማራቆት ከፋይናንስ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት መርህ ባፈነገጠ መልኩ እያካሄዱት ያለውን ብልሹ ተግባር እንዳስሳለን።

ከጥቅምት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ የተመደቡት እና አሁንም ተጠባባቂ የሆኑት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እና ግብረ አበሮቹ ዩኒቨርሲቲውን ለማራቆት ከትምህርት ሚ/ር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የተላኩ የማፍያ ስብስብ ስለመሆናቸው እየተነገረ ይገኛል።

ይህ የማፊያ ስብስብ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ገና ስራ በጀመሩበት ማግስት በተናጠል እያንዳንዳቸው ግማሽ ሚሊየን ብር የሚያወጣ ቅንጡ ላፕቶፕ፣ እስከ 250 ሺህ ብር የሚያወጣ ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲሁም እስከ 1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ቅንጡ የውጭ ሀገር ሶፋ ጨምሮ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶችን በማግበስበስ እንደነበር የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል።

በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በህግ እና ህጋዊ አሰራር ስም ተቋም የማራቆት ተልዕኮውን የጀመረው ከዚህ ቀደም በፌዴራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት እንዲሁም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተደጋጋሚ የተረጋገጠውን የኦዲት ግኝት በማድበድበስ ወንጀልን በመሸሸግ እና ወንጀለኞች ለህግ ተላልፈው እንዳይሰጡ ጥብቅና በመቆም መሆኑን መረጃውን ያጋሩ ግለሰቦች ጥቆማ ሰጥተውናል።

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 4 ዓመታት ተቀባይነት የሚያሳጣ የኦዲት አስተያየት ውስጥ ያለፈ ተቋም መሆኑንና ይህንንም በትኩረት መስራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡን አስተያየት የሰጡት የመረጃ ምንጮች፤ ዶ/ር ጉቼ እና አዲሱ የማፊያ ስብስብ አመራር ግን የባለፉትን ዓመታት ከፍተኛ የኦዲት ግኝት እንዲያርም የተሰጠውን ተልዕኮ በመተው ከፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት መርህ ያፈነገጠ ተግባር ውስጥ መግባቱን ጠቁመዋል።

እንደ አስተያየት ሰጪዎች ጥቆማ ዶ/ር ጉቼ እና ግብረአበሮቹ ወደለየለት የተቋም ዝርፍያ ውስጥ ለመግባት ትራክ ላይ መሆናቸውን ማሳያ ያሉትን ፍንጭ ያመላከቱ ሲሆን፤ በዋናነት በዩኒቨርሲቲው የ2017 በጀት ለህዝብ ይፋ ያልተደረገበት የተሸሸገ ሴራ እና ሚስጢር መኖሩን አመላካች ነው ብለዋል።

በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የልማት ዕቅድ ባለሙያ የሆኑት እና ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት ግለሰብ “ከዚህ ቀደም በነበሩ ዓመታት በጀት ሲደለደል በግልጽ በቢል ቦርድ ማስታወቂያ ሰሌዳ፣ በተቋሙ ዌብሳይት እና ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ ይደረግ እንደነበር ገልጸዋል።

ነገር ግን ይላሉ ባለሙያው፦ ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው የ2017 በጀት ለህዝብ ይፋ እንዳይደረግ በተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ አቅጣጫ መቀመጡን እና አዲሱ ዓመት ከመግባቱ ጥቂት ቀናት በፊት በተቋሙ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በዌብ ሳይት እና ሶሻል ሚዲያ በኩል ይፋ የተደረገው የበጀት ማስታወቂያ ከገጹ ላይ በአምስት ደቂቃ ልዩነት እንዲነሳ መደረጉን ጠቁመዋል።

ይህ ከፋይናንስ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት መርህ ያፈነገጠ አሰራር መሆኑን የገለጹት ከፍተኛ ባለሙያው፤ የበጀት ማስታወቂያው ይፋ እንዳይሆን የተፈለገው ከዚህ ቀደም ታቅደው የተጀመሩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች ሆን ተብሎ በጀት ስላልተያዘላቸው በተጠቃሚው ህዝብ ቅሬታ የሚፈጥር በመሆኑ እንዲሁም አዲስ ይጀመራሉ የተባሉት የልማት ፕሮጀክቶች እንዳይታወቁ በማድረግ የሀብት ምዝበራና ሌብነት ለመፈጸም በማቀድ መረጃውን ይፋ ለማድረግ እንዳልተፈለገ ጠቁመዋል።

እንደ ባለሙያው ገለጻ በተያዘው በጀት ዓመት ገንዘብ ሚኒስትር ለዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 1,815,259,470 (አንድ ቢሊየን፣ ስምንት መቶ አስራ አምስት ሚሊዮን፣ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ሰባ) ብር መደበኛ በጀት እንዲሁም 650,000,000 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ብር ለካፒታል በጀት ተፈቅዷል።

በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲው ታቅዶ የተጠየቀና በገንዘብ ሚኒስትር የተፈቀደ የ2017 መደበኛ እና ካፒታል በጀት 2,465,259,470 (ሁለት ቢሊየን፣ አራት መቶ ስድሳ አምስት ሚሊዮን፣ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ሰባ) ብር መሆኑን የገለጹት ከፍተኛ ባለሙያው፤ ይህም ከባለፉት አምስት አመታት በጀት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ይላሉ ባለሙያው፦ ምክንያቱ ባልታወቀ አግባብ በዩኒቨርሲቲው ተጠይቆ በገንዘብ ሚኒስትር የተፈቀደው የ2017 በጀት ለበርካታ ዓመታት ተቋርጦ የቆዩትን የዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ልዩ ልዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ጨምሮ በዎላይታ ቦዲት ከተማ የተጀመረውን የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል የመማሪያ ክፍል ግንባታ፣ የአበላ ፋራቾ የመማሪያና የእንስሳት ሕክምና ሆስፒታል ቀሪ የግንባታ ስራዎችን፣ የዲምቱ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ህንጻ ግንባታ ማጠናቀቂያ እንዲሁም ሎሎች ትኩረት የሚፈልጉ ተግባራትን አላካተተም ብለዋል።

ሌላው ጉዳይ ይላሉ ባለሙያው፦ “ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለማካሄድ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን ለመሥራት በተያዘው በጀት ዓመት 78,944,300 (ሰባ ስምንት ሚሊዮን፣ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ሺህ ሶስት መቶ) ብር በገንዘብ ሚኒስቴር የተመደበ ቢሆንም ማህበረሰብ ውስጥ የሚሰሩ ዝርዝር ተግባራት ምን እንደሆኑ አይታወቅም፤ የተመደበው በጀት ምንም ሳይሰራበት 1ኛ ሩብ ዓመት ተጠናቋል፤ ይህም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ብዙሃኑ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተቋሙ ምን እየተካሄደ ስለመሆኑ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ፣ አመራሩና ሠራተኛው ሆድ እና ጀርባ ሆነው እንደተራራቁ፣ መድረክ ተፈጥሮ ከአጠቃላይ ሠራተኞች ጋር የጋራ ምክክር እንደማይካሄድ፣ አመራሩ ለሠራተኞቻቸው የከለከሉትን ውሎ አበል እና ጥቅማጥቅም ይዘው በየሳምንቱ አዲስ አበባ እንደሚሄዱ እና ምን እንደሚሰሩ እንደማይታወቅ ይህም አንዳች የተሸሸገ ሴራና ሚስጢር ስለመኖሩ ማሳያ መሆኑን ይኸው ባለሙያ ጠቁመዋል።

ውድ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተከታዮቻችን ለዛሬው ከፋይናንስ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት መርህ ባፈነገጠ አግባብ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ያለውን ብልሹ አሰራር በተመለከተ ያዘጋጀነውን ትንታኔ ዜና በዚሁ ቋጨን።

በቀጣይ ትንታኔ ዘገባችን EBC እና FANA ያልነገሯችሁን እና በብዙ መቶ ሚልየኖች ሚቆጠር የህዝብ ሀብት የተመዘበረባቸውን ነገር ግን “የጨነገፉ የግንባታ ፕሮጀክቶችንና የተሸሸገውን ምትሃታዊ ሴራ እንዲሁም ከሴራው ጀርባ ያሉ ሥውር እጆችን” የሚዳስስ መረጃ ይኖረናል። ይጠብቁን‼

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #dawuro #Wolaita