“ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዎላይታን ወግነዋል በሚል በርዕሰ መስተዳድሩ ጫና እየደረሰበት ነው” ሲል ጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራር ገልጿል።

“አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የዞኑ አስተዳደር ባለወቀበት መንገድ የምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ ቤት እንዲታሸግ አድርጓል” በሚል አንድ የዞኑ ከፍተኛ ባለስልጣን መረጃውን አድርሷል።
በየጊዜው በዞኑ ህገወጥ ተግባር እየፈጸመ እንደሆነ ያስረዱት እኚሁ የመረጃ ምንጫችን፦ “በሌብነት የፈረጠመው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንቱ ከዚህ ቀደም የክልል ማዕከል ውሳኔን ለዎላይታ ሶዶ ከተማ ወግነሃል በሚል የጌዴኦ ዞን የቀድሞ አስተዳዳሪን የአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ር/መ ማዕረግ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰን ከቀበሌ ቤት እንዲወጣ ቤተሰቦቹ ቤት ውስጥ እያሉ የዞኑ አስተዳደር ባለወቀበት በዲላ ከተማ ማዘጋጃ ስራ አስኪያጅና በራሱ ተላላኪ በሆነው የክልል አንድ ቢሮ ኃላፊ በኩል ቤቱ በሰሞኑ ታሽጓል” ብለዋል።

በተጨማሪም “በአቶ ሀይለማሪያም ተስፋዬ የሚመራው የጌዴኦ ፖለቲካ በጥላሁን ከበደ ዘዋሪነት ለጋሞ ዞን ልማት የፈለገውን ገንዘብ ያለካቢኔ ውሳኔ በቅርቡ 60 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎ ተሰጥቷል” ሲል ቅሬታ ገልጸዋል።
“የዞኑን ፖለቲካ በሩቁ እንዲከታተል እንኳን እድል ያልተሰጠው ዶ/ር አበባየሁ ለዎላይታ ይወግናል በሚል ብዙ ጫና እየደረሰበት ነው። በአቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ አማካኝነት የዲላ ከተማ ማዘጋጃ ስራ አስኪያጅን እና የዲላ ከተማ ብልፅግና ኃላፊን አቶ አብነት አክሊሉን የራሱ ግሩፕ በማድረግ እና ከዞኑ አምስቱንም አስተባባሪዎችን በመያዝ የዞኑ ፖለቲካ በአቶ ጥላሁን ከበደ ፈላጭ ቆራጭነት በአቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ አማላጅነት የዞኑ ሀብት ህዝቡ እንዳይጠቀም በማድረግ ዞኑ የብልሽት ምንጭ ሆኗል” ሲሉም ከፍተኛ ባለስልጣኑ አስረድተዋል።
በተለይ በሁሉም መዋቅር በሚባል ደረጃ የአንድ ባች የሆኑትንና በጓደኝነት በጎሣ ትስስር በዘመድ አዝማድ በቀን ምድር ዝርፊያ እየተፈፀመ እንደሆነም ጠቁመዋል።
“የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጥላሁን ቅጥ ያጣ ወዳጅነት ከአቶ ሀይለማሪያም ተስፋዬ የደቡብ ግብርና ኃላፊ ጋር በመፍጠር የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑትን ዶ/ር አበባየሁ ታደሰን ለዎላይታ ወግኗል በሚል ሰበብ የእነ አብዮት ደምሴ የደቡብ ቴክኒክ ሙያ ቢሮ ኃላፊ ለምለም ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ትራንስፖረት መንገድ ልማት ም/ኃላፊ ዘርሁን ማሞ ደቡብ ኢትዮጲያ የፐብሊክ ሰርቪስ ምክትል ኃላፊ የሆኑት የቀበሌ ቤታቸው ሳይነካ በአጠቃላይ የጌዴኦ ተወላጆች በአዲሱ ክልል ሹመት ያገኙት ሁሉ በተለምዶ 70 ቁጠባ በመባል የሚታወቀው የቀበሌ ቤት አላቸው፤ በጥላቻ ብቻ የዶ/ር አበባየሁ ታደሰን የዞኑ አስተዳደር የዲላ ከተማ ከንቲባ ባለወቀበት በአቶ ሀይለማርያም ተስፋዬና በጥላሁን ከበደ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ቤቱ መታሸጉ አግባብነት የለውም” በማለት አድሏዊ አሰራርን አጋልጠዋል።
“አቶ ጥላሁን ከበደ ሀይለማርያም ተስፋዬ አማካኝነት የዞኑን ልማትና በማጓተት ከዞኑ ሀብት እንዲሸሽ የምልጃን ስራ እየሰራ የዞኑ አስተባባሪዎች የሰው ሀገር ልማት እንዲጎበኙ እየተደረገ በራሱ ውሳኔ እንዳይኖረው እየተደረገ ያለው የፖለቲካ ጫና እንዲሁም ጠልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል” ብለዋል። #Ethiopia #Gedio #southethiopia