
“ክልሉ የፓርቲዉን 5ኛ ዓመት ጀምሮ ባጠናቀቃቸዉ ፕሮጀክቶች ሳይሆን በፈጻማቸዉ የሚድያ ኩኔቶችን በባህላዊ ልብስ በማታለል ለማክበር እየተዘጋጀ ነው” በሚል የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናት በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።
“ብልፅግና ፓርቲ ሲመሰረት ከመከፋፈል እና ከአግላይ የፖለቲካ እሳቤ የወጣ አካታች፣ ሚዛናዊ እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያፀና ለኢትዮጵያ ብልጽግና ራዕይ የሰነቀ እንደሆነ ይታወቃል” ሲል ይጀመራል፡፡
አከለውም ፓርቲው ኢ-ፍትሀዊነት፣ አግላይነት፣ የነጠላ ትርክት የበላይነትና ሌሎች ችግሮችን በሀሳብ ልዕልና ለመፍታት በፅኑ መሰረት ላይ የጣለ እንደነበር ገልጿል።
ያልተገራ ስሜትና ፅንፈኝነት የሚገራው፤ ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው፣ የህዝብ ኑሮ የሚሻሻለው፣ ብሔራዊ ጥቅም የሚከበረው፣ የጥራትና የኢፍትሀዊነት ችግሮች የሚቀረፉት፣ ማህበራዊ ፍትህ የሚነግሰው በሀሳብ ልዕልና ብቻ እንደሆነም የሚያምን ነበር ይላል።
“በዚህም እንደ ሀገር በፈተና ዉስጥም የብልፅግና አመራሮች በሚያወሩት ልክ ባይሆንም ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ የፓርቲዉ ሊቀምበርና የሀገርቱ ጠቅላይ ሚኒስተር በቁጥር ጥቂት አመራሮች ጋር የሀገርቷን ዕምቅ አቅም ከችግሮቿ በላይ በመመልከት ለብልፅግና እየተጉ እንደሚገኙ ለማንም ያልተደበቀ ሀቅ ነዉ” በሚል ያብራራል፡፡
“ሆኖም ግን ለዉጡን ከልብ ያልተቀበሉና በዉስጣቸዉ ላይ ነግሶ የቆየዉን ክፋትና ሰሬኝነት ማሸነፍ ያቃታቸዉ የራሱ የፓርቲዉ አመራር ለዉጡ የሰነቀዉን ግብ እንዳያሳካ አድርጎታል፡፡ የለዉጡ ትሩፋት ዉጤት እና የእዉነተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት ማሳያ ከሚጠቀሱት ክንዉኖች አንዱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ነበር” በማለትም ያስታውሳል።
“ይህ አደረጃጀት የህዝቦች የዘመናት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ቀስ በቀስ ይፈታል ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ብሆንም በአንድ ዓመት ቆይታዉ ለህዝቦቿ ተጨማር ዕዳ እየሆነ ይገኛል” በሚል ሁኔታውን ይገልፃሉ፡፡
“የፓርቲዉን ምሶሶዎችን በተጻረረ መልኩ በተላይም መከፋፈልን እና አግላይ የፖለቲካ እሳቤ የወጣ አካታችነትን፣ ሚዛናዊነትን እና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነት ከማፅናት ይልቅ በተቃራኒዉ ቅመኝነት፣ በቀለኝነት፣ ቡድንተኝነት፣ ኢ-ፍትሀዊነት፣ አግላይነት፣ የየአካባብዉ ገዥነትና የነጠላ ትርክት የበላይነት ወዘተ የነገሰበት ክልል መሆኑንም በማስረጃ አረጋግጧል፡፡
ለማሳያነት፡- ዎላይታ ዞን ከ40 ዓመት በላይ በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ ራሳቸዉ አባት እርሻ ማሳ ከአንዱ ስልጣን ወደ ሌላ ስልጣን በሚሽከረከሩ በአቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ እና በአቶ ገብረመስቀል ጫላ ዘመዶችና ጎሳዎች በተፈጠረዉ አደረጃጀትና ይሄን በሚቃወም ቡድን እየታመሰች ይገኛል ይላል መግለጫው፡፡
በተላይም ለቀጣይ የፓርቲ ጉባኤ ላይ የፓርቲዉ የሥራ አስፈጻም ኮሚቴ አባል ለመሆን ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ አድስ የአመራር አደረጃጀት በማዋቀር በየፍናዉ ሩጫ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጋሞ ዞን በማንነት ቀዉስ ዉስጥ በሚገኝ በአቶ ጥላሁን ከበደ በሚመራ ቡድንና እዉነተኛ ጋሞዎች እኛ ነን በሚል ፍልምያ ዉስጥ ዉስጡን እየተናጠ ይገኛል፡፡
ጋሞነት እንደ አየር ሁኔታዉ የሚቀበሉ ርዕሰ መስተዳድሩ በአሁናዊ ሁኔታቸዉ የጋሞ ልማት አርበኛ ነኝ ነጠላ ዜማ በኔትዎርካቸዉ አማካይነት እንድዘመር እያደረጉ በመሆናቸዉ ድል የቀናላቸዉ ይመስላል፡፡
ጌድኦ ዞን በአቶ ጥላሁን ከበደ ተላላክ በሆነዉ በአቶ ሃይለማሪያም ተስፋዬ የሚመራዉ ቡድን ዶ/ር አበባየሁ ታደሰን የማጥፋት ሴራ ላይ ተጠምዷል፡፡
የቀድሞ ደቡብ ኦሞ ዞን በአሁኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ዓለማየሁ ባዉድ በሚመራዉ ሰሬኛ ቡድን እና በአቶ ንጋቱ ዳንሳ በሚመራዉ ሚዛናዊ እይታ ባላቸዉ ቡድኖች ትግል ላይ ናቸዉ፡፡
ጎፋ ዞን ደግሞ በአቶ ጥላሁን ከበዴ የሴራ ልጅ በሆኑት በአቶ አክልሉ አዳኝ በሚመራዉ እና በእሱ በተገፉት የህዝብ ቅቡልነት ባለባቸዉ ወጣት ቡድኖች እየተናጠ ይገኛል፡፡
ኮንሶ ዞን ደግሞ በአቶ ጥላሁን ከበዴ ቀኝ እጅ በሆነዉ በአቶ ዳዊት ገበየሁ ሰሬኛ ቡድን እና በአቶ ሃልጋዮ ጅሎ በሚመራዉ ቡድን በየቀኑ የሰዉ ህይወት እየበላ ይገኛል፡፡
ሌሎች ቀሪ ዞኖችም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በሚደገፉ ትናንሽ ገዥዎች እጅ ወድቀዋል፡፡ በአጠቃላይ ክልሉ በብልፅግና ፓርቲ ሳይሆን በሰፈር ገዥዎች እየተመራ በመሆኑ ከሴራ ፖለቲካ ዉጭ እዝም እዛም በግለሰብ ደረጃ ከተሰሩ የልማት ሥራዎች በስተቀር በለዉጡ መንግስት ተጀምሮ የተጠናቀቁና እየለሙ ያሉ የልማት ዉጤቶችን ማሳየት አዳጋች አድርጓል” በሚል ያብራራሉ፡፡
በተቃራኒዉ የዜጎች ህገ-ወጥ እስራት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለፅ ዕድል ሙሉ በሙሉ የተከለከለበት ክልል ከሆነ ሰነባብቷል፡፡
ስለሆነም ክልሉ በአንድ ዓመት ቆይታዉ በአሰራርና በተቋም ሳይሆን በግለሰቦች ፍላጎትና እነዚህን ፍላጎቶችን ህጋዊ ለማስመሰል በተደረጉ የመድረክ ድስኩሮችና በሚዲያ ፖለቲካዎች ተጠማምደዉ ሰንብቷል፡፡
በመሆኑም “ክልሉ የተግባር ሳይሆን የሚድያ ክልል ስለሆነ የፓርቲዉን 5ኛዉን ዓመት የምስረታ በዓል በተደራጀ መልኩ ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ከማድረግ ይልቅ በ6ቱ ማዕከላት በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ሳይሆን በባህላዊ አልባሳት ባሸበረቁ ኩኔቶች ኦዲት ዉጤቶች ዙርያ በ16/3/2017 ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል” በሚል ጠቁመዋል፡፡
ከምንም በላይ የሚያሳዝነዉ የለዉጡ ባለቤት በነበሩ ህዝቦች ይሁንታ የተመሰረተዉ ክልል በራሱ የፓርቲዉ አመራር ለዉጡ በመቀልበሱ ምክንያት የዳር ተመልካች መሆኑ ነዉ፡፡
የህዝቡ የፍትህ ጥያቄ በአግባቡ የሚመለሰዉ መቼ ይሆን? ይህ የድብብቆሽ የሚዲያ ፖለቲካ ማብቂያዉ መቼ ይሆን? ይህ “የሰላም፣ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት ክልል” በሚዲያ ብቻ የሚናዉቀዉን በተግባር የሚናየዉ መቼ ይሆን? ብሎ ይጠይቃሉ። #Ethiopia #southethiopia