1000027494

የመራራ እውነት ዘገባ – ተቋምን ከዝርፊያ ለማዳን የተዘጋጀና ግለሰብን በጥልቀት በመረጃ በእውነት የሚዳስስ ለየት ያለ በመሆኑ እባክዎ በጥሞናና በትዕግሥት ያንብቡ🙌

«መክሸፍ እንደ ‘ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳሞታ ኢንተርፕራይዝና ውሃ ሽታ የሆነው 100 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች ቅሌት‼» – በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ

የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ “የሙስና ግንደ ቆርቁር!!” በ “EBC/ETV በዓይናችን ፕሮግራሙ”፣ FANA እና ሌሎች ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የሚዲያ ተቋማት በዜናዎቻቸው በግርድፉ ሸፋፍነውት ያለፉትን ገሀድ ያልወጣና በብዙ መቶ ሚልዮን ብሮች ሚቆጠር የህዝብ ሀብት የተመዘበረባቸውን «የጨነገፉ የግንባታው ዘርፍ ፕሮጀክቶችን እና የተሸሸገውን ድብቅ ሴራ እንዲሁም ከሴራው በስተጀርባ ያሉትን ሥውር እጆችንም ለሰፊው ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ ዘላቂ ጥቅምና መፍትሔ ሲባል ሀቅ ሀቁን በአደባባይ እንተነትናለን።

በሀገራችን ግንደ ቆርቁር/woodpecker (🐧) የምትባል የወፍ ዝርያ አለች። ይህች ወፍ ግንድ ቆርቁራ ጎጆዋን ትቀልስና፡ በዛ ቤተሰብ መስርታ ለአመታት ትኖራለች።

ልክ እንደዚህች ወፍ ለሰናይ ሳይሆን ለእኩይ ዓላማ ተምሳሌታዊ “ግንድ የመቆርቆር” ገጽታ (Character) የተላበሰ «የሙስና ግንደ ቆርቁር» የሆነ እና አቻ የሌለው ግለሰብ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በአመራርነት ላይ ይገኛል። ይህ ግለሰብ ዶ/ር ተክሌ ሌዛ ይባላል። አንዳንድ በቅርበት የሚያውቁት የሥራ ባልደረባዎቹ ደግሞ በቅጽል ስሙ «ጋሽ አባ ኮዳ» ይሉታል–አልጠግብ ባይ አግበስባሽ መገለጫ ባህሪውን ለመግለጽ።

ከላይ በምሳሌ እንዳነሳነው የወፊቱ ግንድ የመቆርቆር ዋና ዓላማ ጎጆ ቀልሳ፣ ቤተሰብ መስርታ ለዓመታት የመኖር/የህላዌ ጥያቄ (The issue of Existence/Survival) ሲሆን የዶ/ር ተክሌ እና የግብረ-አበሮቹ ግን ተቋሙን በተደራጀ ሌብነት እና ዝርፍያ ቀስ በቀስ እየሰረሰሩ የማፍረስ እና የማበስበስ ተልዕኮ (mission based on nepotism, greed & extravagance to destroy an institution) ያነገበ ነው ማለት ይቻላል።

ግለሰቡ ከዚህ ቀደም የቢዝነስ እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት፤ ከአንድ ዓመት በፊት በተካሄደው መዋቅራዊ አደረጃጀት ደግሞ የግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ ፋይናንስ፣ ግዢ፣ ኦዲት፣ ንብረት አስተዳደር፣ ሰው ሀብት እና ሰፊውን የተማሪዎች አገልግሎት ጨምሮ በርካታ የሥራ ክፍሎች የያዘውን “የአስተዳደር እና ልማት” ምክትል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት እየመራ ይገኛል።

አሁን ከበፊቱ በበለጠ “ሁሉ በእጁ፥ ሁሉ በደጁ” ሆኗል፤ የሌብነት እና የዝርፍያው ሜዳ እና ፈረሱም በእጁ ገብቷል፤ ህግን ሽፋን በማድረግ ይዘርፋል፣ ያዘርፋል። በቃ
የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር) ከእንቅልፉ እስኪነቃ እና ከሙዝ የእርሻ ማሳው እስኪመለስ ድረስ ለዝርፍያው ከልካይ ሆነ ተከላካይ የለውምና ዶ/ር ተክሌ ተቋሙን የማራቆት ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል የሚሉት ብዙዎች ናቸው።

ዛሬን ጨምሮ በተከታታይ ጊዜ በሚኖረን ዜና ሀተታ ጥንቅር በሙስናው ግንደ ቆርቁር ተክሌ ሌዛ (ዶ/ር) እና ግብረአበሮቹ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለይ በግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እና በተቋሙ “ኢንተርፕራይዝና ሀብት ማመንጫ ዘርፎች” ሲካሄድ የቆየውን እና አሁንም ድረስ እየተካሄደ ያለውን የተደራጀ የዝርፍያ ቅሌት» በስፋት እንዳስሳለን።

በነገራችን ላይ የተቋሙ ኢንተርፕራይዝ እና ሀብት ማመንጫ ዘርፍ ባለፈው ዓመት 100 ሚሊየን የሚበልጥ ተንከባላይ የኦዲት ግኝት ያስተናገደውን እና የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተማሪዎችን ጨምሮ ለስልጠናና ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ተቋሙ የሚመጡ ተገልጋዮች የሚስተናገዱበት «ዳሞታ ኢንተርፕራይዝ» የተባለውን ግዙፍ ካፍቴሪያ እንደሚያካትት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል።

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ገለጻ ይህ ካፍቴሪያ በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ እና አሁንም እስከ አንድ ወር የሚቆዩ እና በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የሚገለገሉበት ቢሆንም እንደ አንድ “ህጋዊ ህልውና ያለው ኢንተርፕራይዝ” ግን በራሱ ገቢ ራሱን ማስተዳደር ያልቻለ እና እስከ አሁን ድረስ ከዩኒቨርሲቲው መደበኛ እና ካፒታል በጀት በሙስናው ግንደ ቆርቁር ዶ/ር ተክሌ ተመቻችቶለት እየተደጎመ የሚገኝ እና ከጥገኝነት ያልተላቀቀ “የከሸፈ የዋልጌዎች መጫዎች” መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል።

የተቋሙ ኢንተርፕራይዝና ሀብት ማመንጫ ዘርፍ የዝርፍያ እና የክሽፈት ትርክት ሲቀጥል «ዳሞታ ኢንተርፕራይዝ» ላይ ብቻ የሚቆም አይደለም የሚሉት የመረጃ ምንጮቻችን፤ ከስምንት ሺሕ ለሚበልጡ የዩኒቨርሲቲው መደበኛ ተማሪዎች ቀለብ የሚውል ዳቦ እና እንጀራ የሚያቀርበው፣ በስመ “የደለበ የበሬ ሥጋ” ስም በሳምንት ሁለት ጊዜ ለተማሪዎች ወጥ መስሪያ የሚሆን ቅንጥብጣቢ ሥጋ የሚያቀርበው “የከብት ማደለቢያ” ማዕከል እንዲሁም በቅርቡ ማስፋፊያ የተደረገለትና ከ180 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ ተገነባ የተባለው «የወተት ላሞች እርባታ ማዕከል» የሚያካትት ከፍተኛ የዝርፍያ ዋሻ መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን አመላክተዋል።

የሚያሳፍረውና የሚያሳዝነው ዋናው ጉዳይ ግን የ«ዳሞታ ኢንተርፕራይዝ» ካፌ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለት ዙር በተካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለተሳተፉ ከ40 ሺህ ለሚበልጡ ተፈታኞች ሙሉ ቀለብ በማቅረብ ያስተናገደ፤ ለአራት ተከታታይ ዓመታት ለአንድ ወር የጊዜ ቆይታ በተካሄደውና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የሰላም ሚኒስቴር የበጎ ፈቃድ ብሔራዊ አገልግሎት ሰልጣኞች የተሳተፉበት የተሟላ የምገባ አገልግሎትን ያስተናገደ፤ በተለየዩ ጊዜያት በተከታታይ የተካሄዱ ሀገር እና ክልል ሀቀፍ መንግስታዊ ስልጠናዎች በርካታ ሺሕ ሚቆጠሩ ሰልጣኞችን ከ15-30 ቀናት የተሳተፉበትን ሻይ ቡና ጨምሮ ሙሉ የምገባ አገልግሎት ያስተናገደ እና አሁንም እያስተናገደ የሚገኝ፤ ከተቋማቱ ጋር በገባው ውል መሰረት የአገልግሎት ክፍያ የተከፈለው ነገር ግን በሚያገኘው የውስጥ ገቢ ራሱን ማስተዳደር ያቃተው እና የከሸፈ መሆኑን መረጃውን ያጋሩን አካላት ተናግረዋል።

የመረጃ ምንጮቻችን አክለውም ፦ ዳሞታ ኢንተርፕራይዝ የውስጥ ገቢውን ተጠቅሞ ራሱን ማስተዳደር ተስኖት ለኦዲት ግኝት የበቃውና የከሸፈው በየወቅቱ በሚቀያየሩና በሙስናው ግንደ ቆርቁር ዶ/ር ተክሌ ሌዛ በጎሰኝነት እና በአካባቢያዊነት ተመልምለው በሚመጡ፣ እንዳሻቸው ዘርፈውና አስዘርፈው በሚሄዱ ቅጥ ያጣ የሌብነት እና የዝርፍያ ቅብብሎሽ ተዋረዳዊ አደረጃጀት በሚሰገሰጉ እኩይ ግለሰቦች መሆኑ ሊዘነጋ እንደማይገባ እነዚሁ የመረጃ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ።

የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲው የሙስና ግንደ ቆርቁር ተክሌ ሌዛ (ዶ/ር) እጅግ በረቀቀና በተጠና መንገድ እየመለመለ በህገወጥ መንገድ የሚቀጥራቸው የራሱ ጀሌዎችና ሚስጢረኞቹ ከባለፉት ሦስትና እና አራት ዓመታት ወዲህ ተቋሙን ሲያራቁቱ እንደቆዩ እና የኦዲት ግኝት የተባለው የ100 ሚሊየን ብር ጉዳይ እንደተለመደው የውሃ ሽታ ሆኖ መቅለጡ እንዲሁም ኢንተርፕራይዙን ሲመሩ የቆዩ የተለያዩ ግለሰቦች ከሕግ ተጠያቂነት ለማስመለጥ እንዲሸሹ መደረጉን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን ዶ/ር ተክሌ “ዩኒቨርሲቲውን ለማገልግል ሳይሆን ሊገለገልበት በማሰብ” ከዚህ ቀደም ሲዘርፍ እና ሲያዘርፈው በቆየው እና በኦዲት ከ100 ሚሊየን ብር የሚበልጥ ግኝት የተከናነበውን “ዳሞታ ኢንተርፕራይዝ” እንዲመራ ከዎላይታ ዞን ፋይናንስ የቀድሞ ወዳጁን እና አሁን ላይ በጡረታ የተገለለውን ግለሰብ በመቅጠር እና ዋና ሥራ አስኪያጅ በማድረግ ለዝርፍያ መዘጋጀቱን የመረጃ ምንጮቻችን አሳውቀውናል።

ዶ/ር ተክሌ በዎላይታ ዞን ከወረዳ ፋይናንስ ጽ/ት ቤት ጀምሮ እስከ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ድረስ በኃላፊነት መስራቱን የገለጹልን የመረጃ ምንጮች፤ የቅርብ ወዳጅ፣ ቤተ-ዘመድ እና በወቅቱም በዩኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዝዳንት በነበረው ዶ/ር አብርሃም አላሮ በተባለው ግለሰብ ድጋፍ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፒ.ኤች.ዲ የትምህርት እድል ተሰጥቶት ከአምስት ዓመት በፊት PhD in Rural Development እንዲያጠናቅቅና በተቋሙ መምህር እንዲሆን የተደረገ የመጀመሪያው የዞኑ የካቢኔ አባል መሆኑ ተመላክቷል።

የ ዶ/ር ተክሌ ደቀመዛሙርት እና የቅርብ ወዳጆች በፋይናንስ አሰራር ብቁ እና ብቸኛ ሰው አድርገው ቢያቀነቅኑለትም ግለሰቡ ግን «አላዳንኩሽም» የተሰኘውን ዜማ በውስጡ ከማዜም ባሻገር ባለፉት አምስት አመታት ተቋሙ ተከታታይ የኦዲት ግኝት ሰለባ ሲሆን እና ሀገር አቀፍ ውርደት ሲከናነብ አንድም የፈየደው ነገር እንደሌለ እንዲሁም ዘርፉን ለረዥም ዓመታት እንደመራና በዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባልነት ቆይታው በተቋሙ ላጋጠመው የፋይናንሻል ውድቀት ሚናውን ያልተወጣ፥ ይልቅ ለግል ጥቅሙ ሲል ግን ማኔጅመንቱን በስህተት መንገድ ሲመራ የቆየ እና ኢየሱስ ክርስቶስን በሰላሳ ዲናር የሸጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ተምሳሌት በመሆን የገዛ ወንድሞቹን አሳልፎ የሸጠ እና ያልተነቃበት «ከሀዲ» መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

ተክሌ ሌዛ (ዶ/ር) “የሙስና ግንደ ቆርቁር” ብቻ ሳይሆን የክፋት፣ የተንኮል፣ የመሰሪነት እና የእኩይ ድርጊቶች ሁሉ ባለቤት መሆኑን እና ባለፉት 5 ዓመታት በዩኒቨርሲቲው እንደ ሳሙና እየተሙለጨለጨ በአመራርነት የቆየ መሆኑን ከአንድ ዓመት በፊት በተቋሙ በርካታ ግለሰቦች በጽናት እየታገሉ በተካሄደ ውድድር መሰል የጨረባ ምርጫ–በተደራጀ ህገወጥ የቡድን ድምጽ አሰጣጥ–የአስተደደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሆን መደረጉ ትልቁ ማሳያ እንደሆነ መረጃውን ያጋሩን ምንጮች ጠቁመዋል። ((በተደራጀ ህገወጥ የቡድን ድምጽ አሰጣጥ የተካሄደውን «የጨረባ ውድድር መሰል ምርጫ» ድራማዊ ትወና የተመለከተ ሰፊ ዘገባ ለብቻው ይኖረናል))

ተክሌ ሌዛ (ዶ/ር) በአካዳሚክ የትምህርት ደረጃ ዶክትሬት ዲግሪና የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያለው ግለሰብ ቢሆንም ነገረ ስራው ሁሉ ግን የተማረ ሰው ምግባር እና የሞራል ልዕልና የተላበሰ አለመሆኑን ለማሳየት ያህል በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው የመደበኛ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ እንዲቀየር በማድረግ “ቁርስ ሻይ በዳቦ” ብቻ እንዲመገቡ ጭካኔ የተሞላ ውሳኔ ማስተላለፉን ነገር ግን የተለያዩ ሚዲያ ተቋማት ይህን የሜኑ ለውጥ መረጃ ሲያጋሩ መመልከታችንና በተማሪዎች የጸና ትግል ውሳኔው መቀልበሱ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

ወፊቱ ግንድ ቆርቁራ በሰራችው የወፍ ቤት ውስጥ እርሷ እና ቤተሰቦቿ ይኖራሉ፤ ተክሌ ሌዛ (ዶ/ር) ቆርቁሮ በሰራው የሌብነት ዋሻ ግን ተቋም እየፈረሰ እርሱ እና ግብረአበሮቹ ተንደላቀው ያለከልካይ የቅንጦት ኑሮ ይኖራሉ። አንደኛው ህይወት ለማቆየት ሌላው ደግሞ ሌሎችን ረግጦ በሚያገኘው የዝርፍያ ሀብት እጅግ ቅንጡ ሕይወት ለመኖር፤ ይህ ነው እንግዲህ የለየለት «የህይወት ተቃርኖሽ» ማለት። አዲዎስ!!!

የፕ/ር መስፍን ወልደማርያም «መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ» በሚል ሀረግ ለአንድ መጽሐፋቸው የሰጡትን ሀሳብ በመዋስ ይህ ግለሰብ አሁንም በማናለብኝነት ለሚያደርገው ብልሹ አሰራር እና የቅሌት ተግባር ይመጥናል በሚል ርዕስ «መክሸፍ እንደ ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳሞታ ኢንተርፕራይዝ!!» በሚል የጀመርኩትን ዜና ሀተታ “በኢንተርፕራይዙ የተጀመረውን የተደራጀ ዝርፍያ ለማስቆምና ወደለየለት ተቋም የማፍረስና የማክሸፍ ደረጃ ሳይሻገር በፊት ሁሉም ያገባኛል የሚል አካል ዓይኖቹን ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲያማትር በመጠየቅ ሀሳቤን ቋጨው።

ቀጣይ ይኸው ግለሰብ ሲመራው የቆየውን እና አሁንም እየመራው በሚገኘው የተደራጀ የሌብነት እና የዝርፍያ አዙሪት በሆነው፣ ነገር ግን “EBC/ETV በዓይናችን ፕሮግራሙ”፣ FANA እና ሌሎች ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የሚዲያ ተቋማት በዜናዎቻቸው በግርድፉ ሸፋፍነውት ያለፉትን ገሀድ ያልወጣና በብዙ መቶ ሚልዮን ብሮች ሚቆጠር የህዝብ ሀብት የተመዘበረባቸውን «የጨነገፉ የግንባታው ዘርፍ ፕሮጀክቶችን እና የተሸሸገውን ድብቅ ሴራ እንዲሁም ከሴራው በስተጀርባ ያሉትን ሥውር እጆች» የሚዳስስ ጥንቅር ይኖረናል። ይጠብቁን‼

ቸር እንሰንብት፤ መልካም ጊዜ ተመኘን!!
……………………………………..
የሙስና ግንደ ቆርቁር–የስርቆት/የሌብነት መሸሸጊያ ዋሻ!! ለማለት የተሰጠ ተዛማጅ ትርጉም የያዘ ሀረግ ነው።‼

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ