1000027605

“ስሜ ቶፊቅ አብድልቃድር እባላለሁ። የመጀመሪያ ዲግሪ በእጽዋት ሳይንስ 2001 ማስተርስ በአግሮኖሚ ከሀረማያ ዩኒቨርስቲ አግኝቻለሁ። ዲላ ግብርና ኮሌጅ ለሁለት አመታት በመምህርነት፣ ዎላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ወደ 14 አመት አገልግያለሁ። ለፕረዝዳንት ሳህለወርቅ ሳይቀር ዎላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ይህን የመሠለ ስራ የሰራው ብዬ በአካል ቆሜ አስረድቻለሁ። በዚህም ክልሉን አስጠርቻለሁ በሆድኩበት ቦታ ሁሉ ዎላይታ ዎላይታ ብዬ አስጠርቻለሁ። ሚኒስተር ዴኤታዎች በስልኬ ደውለውልኛል።

እኔ መ/ር ቶፊቅ የዎላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅን በመወከል እስከ ፌደራል ሳይንስ ሙዚየም ሚሊንየም አዳራሽ ከውጭ ዜጎች ጋር በተለያዩ ኤግዚቨሽኖች ላይ፣ የኢትዮጵያ የከተሞች ቀን፣ ዮዮ ጊፋታ፣ ሀገርአቀፍ በዓላት ላይ፣ ቀዳማዊ እመቤት ዳቦ ቤት የከተማ ግብርና (vertical farming) ለአመታት ሰርቼ ስራዎቼን አሳይቻለሁ።

ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተደጋጋሚ Post አድርጋችሁታል። የሰላም ሚኒስተር: የሰላም ማኒስቴር ዴኤታ፣ የአከባቢ ጥበቃ ባለስጣን፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስተር ስራዎቼን በአካል መተው ጎብኝተዋል። እንዲሁም ርዕስ መሥተዳደር፣ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ታዋቂ ሰዎች፦ ለቁጥር የሚከብድ ግለሰቦች…. በምሰራበት ኮሌጅ ወስጥ በአካል በመገኘት ስራዎቼ ጎብኝተዋል። የደቡብ ብልጽግና የግብርና መዝሙሩ ሳይቀር በኔ የከተማ ግብርና ሰራ ፎቶዎች ነው የሰራው።

በዚህም ተቋሙ ከፍተኛ እውቅናን አግኝቷል። እኔም እውቅናን አግኝቼበታለሁ። የከተማ ግብርና ስራን በማስተዋወቅ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ እንኳን ቀዳሚ ነበርኩ። ዛሬ ግን አዲስ ሀላፊ ሲቀየር ለስድስት ወራት ስራውን መደገፍ አቆመ….. ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገው ነውና በቁሜ እያለሁ ደብዳቤዬ ለቦርድ ግልባጭ ሆኖ ሳለ አቁም የሚል ደብዳቤ እንኳ ሳይሰጠኝ ሌላ ሰው አስገባ ነገር ግን ስራው ዛሬ ብታዩት ልብ ይነካል። ስራዎቼን ያልዘገበ ሚዲያ የለም።

የኔን ስራ ለማየት የት ነው ዎላይታ ሶዶ ብሎ ያልመጣ ክልሉን ያልጎበኘ ሰው የለም። የትኛውም ቦታ በኢትዮጵያ ቨርቲካል ፋርሚንግ ሲነሳ ዎላይታ ሶዶ ነው የሚባለው ዛሬ ያ ሁሉ ነገር እንዲጠፋ ተደርጓል። እስኪ የዎላይታ ታይምስ በአከባቢው ጉዳይ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ሚዲያ ይሄንን ሀቅ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲፈርዱ ወደ አደባባይ እንዲያወጣ እፈልጋለሁ።”

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita #የመምህራንድምፅ