1000027782

“ታጋይ ሰለሞን ዋዳን የሚተካ ለግሉ ህይወት የማይሳሳና የዎላይታ ብሄር አንገት የማያስደፋ ግንባር ቀደም የለዉጥ ሀይል በማጣታችን የህዝባችን ሰቆቃ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ይገኛል” በሚል የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በክልሉ ወቅታዊ እና ቀጣይ ሁኔታ ላይ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።

አስተባባሪዎቹ አክለውም “ሰለሞን ዋዳ በወቅቱ የነበረዉን ዘዉዳዊ አገዛዝ በጽኑ የታገለ፤ የጭቁኖች ጉዳይ የሚያንገበግበዉ በተላይም የዎላይታ ጉዳይ የሚያቃጥለዉ ደፋር ሰዉ እንደነበር ታርክ በማስታወስ፥ ከታርክ እንደሚንረዳዉ ሰለሞን ትግሉን ዉጤታማ ልያደርጉ የሚችሉ ተግባራትን አከናዉኗል” ሲሉም ያብራራሉ።

ከነዚህ መካከል የመንግስት ሰራተኛዉ ለመብት እንድታገሉ፤ ሰፊዉ የዎላይታ ገበሬ የገዛ መሬቱ ባለቤት በመሆን ራሱን በራሱ እንድያስተዳድርና ለዘመናት የመዘበሩትን የመሬት ከበርቴዎች እንድታገል በማደራጀቱ የህዝቡ ንቃተ ህሊና በፍጥነት በማሳደግ የተለያዩ ፖለቲካዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ከህዝቡ አንደበት እንድወጣ በማድረግ ትግሉን ማቀጣጠሉን አብራርቷል፡፡

የተለያዩ መፈክሮችን በማመንጨት ለአብነት:- “ዴሞክራሲያዊ መብትን ከሰፊዉ ሕዝብ የሚነጥቅ ኃይል የለም!”፤ “የዎላይትኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ ሬዲዮ መደበኛ ፕሮግራም ይኑረዉ!”፤ “ሥልጣን የሰፊዉ ጭቁን ህዝብ ነዉ!” የሚሉት ከብዙዎች ጥቅቶች እንደነበርና የዎላይታን ህዝብ ሲረግጡና ሲበድሉ በነበሩት ላይ አጭር ግዜ ህዝብን በማሰተባበር ጠንከር ያለ ጫና በማሳደር ተጨባጭ ዉጤት ማስመዝገብ እንደቻለ ታርኩ ያስረዳል” ብሏል።

ዎላይታ በአፄ ሚኒሊክ በኃይል ንጉሳዊ አስተዳደር መዋቅሩ ከፈረሰበት ጊዜ ጀምሮ በየጊዜዉ በሚመጡና በሚቀየሩ መንግስታት የተሟላ የፖለቲካ ሥልጣን ባለበት እንዳይሆን ተደርጓል፡፡ ቂምም አሳድረዋል፤ በ1950ዎቹ የራሷ አዉሮፕላን ማረፍያ የነበራት ዎላይታ አሁን ወዳለችበት ደርሳለች፡፡ ለዚህ ያበቃን በዋናነት የዉስጥ አንድነት መላላት፤ የፖለቲካ ሴራና የሀብት ክፍፍል ችግሮች እንደሆኑ ጠቁሟል።

በተጨማሪም “እነዚህ የዎላይታ ፈተናዎች እንደ ታጋይ ሰለሞን ዓይነት የዎላይታ ጉዳይ ከልብ የሚያቃጥለዉ ታጋይ ካልተፈጠረ የዎላይታ ህዝብ ድህነት በባሰ ሁኔታ እንደሚቀጥል እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ የህዝቡ ያደሩ ጥያቄዎችና እና አዳጊ ፊላጎቶችን በሚዛኑ ለመፍታት የታሰበዉ የዎላይታ ክልልነት ጥያቄ ከመንግስት መኪና ከወረዱ የሚሞቱ በሚመስሏቸዉ በሆዳም አመራሮች ተጠልፎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንድገባ መደረጉን በመግለጫው አስታውሷል።

እንደ አስተባባሪዎቹ ገለፃ፦ ይህ አደረጃጀት ገና በማለዳዉ ዎላይታ ጠል በሆኑ ሌላ ብሄር ግለሰቦች እና ለሆድ ባደሩ በገዛ ልጆቹ ተጨማሪ ዕዳ ዉስጥ ይገኛል፡፡ በ33 ፔርሰንት ድርሻዉ መሰረት የፖለቲካ ዉክልናና የመንግስት በጀት ድጎማ እንዳያገኝ ተደርጓል፡፡

data by WT media

ለማሳያነት አሁን በተዋቀረው በክልሉ የዉሳኔ ሰጭነት ድርሻ መካከል በመንግስታዊዉ በካቢኔ አባልነት ቁጥር፤ እየመሩ ያሉባቸዉን ተቋማት በሚመሩት የመንግስት ሀብትና በሥሩ ባሉ ሠራተኞች እና እንድመሩ የተሾሙ አመራሮች ብቃትና ለወከሉት ህዝብ ጥቅም የማስከበር አቋም ማጤን አስፈላጊ ነዉ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ከመንግሰት ሀብት አንጻር 29 ፔርሰንት ድጎማ በጀት የተመደበ ስሆን ሌሎች በድጋፍ መልክ በረጂ ድርጅቶች በኩል የሚቀርቡት ዞኑ በልጽጓል በማለት እንድቆሙ ተደርጓል፡፡ ክልሉ ብዝሀ ማዕከላት እንድኖሩት በተደረገዉ ለሶዶ ማዕከል የተመደቡ ቢሮዎች የሚያስተዳድሩት የሰዉ ሃይል እና የሚመደብላቸዉ በጀት አንጻር ብታይ እንኳን ከተማዉን የማይመጥኑና ህዝቡን ለመጉዳት ታስቦና ታቅዶ የተመደቡ ቢሮዎች ናቸዉ በሚል አስረድቷል፡፡

data by WT media

“እንደዛም ሆኖ የተመደቡት ቢሮዎች ታፔላ ዎላይታ ሶዶ የዕለት ዕለት ኩኔቶች ደግሞ የሚፈፀሙት በሌሎች አካባብዎች ነዉ፡፡ በጥቅሉ ዓላማዉ ዎላይታ አካባቢ እንዳይረጋጋና የፀጥታ ስጋት እንድሆን ታስቦ የተሰራ የፖለቲካ ሴራ ነዉ፡፡ ሆኖም ህዝቡ ጨዋ በመሆኑ እና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተሩን ላለማሳዘን በትግዕስት ቆይቷል፡፡ ምክንያቱም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ከአደረረጃጀቱ ጋር በተያያዘ የዎለይታ ህዝብን በማክበር በርካታ መድረኮችን በመፍጠር መልፋታቸዉን ስለሚያዉቂና ለልፋታቸዉ ዕዉቅና ስለሚሰጥ ነው” በሚል ምክንያት አስቀምጧል፡፡

አሁን በደረሰበት ደረጃ የዎላይታ ህዝብ እዉነተኛ ጥያቄዎችና እየደረሱ ያሉት በደሎች በተለያዩ አማራጮች ለጠቅላይ ሚኒስተሩ እያቀረበ ያለ ብሆንም የህዝቡ ስቃይ እየጨመረ እንድሄድ ትልቅ አበርክቶ ያላቸዉ የገዛ ልጆቹ እንደሆኑ በፅኑ ያምናል ብሏል፡፡

በዚህም ምንም እንኳን በሀገር ደረጃ በሙያቸዉ አንቱ ብሆንም ሳይማር ላስተማረዉ ለዎላይታ ህዝብ ዴንታ የለሌዉ፤ ከዎላይታ ጠንካራ ሰዉ እንዳይወጣ ቀን ማታ የሚሰራዉንና ዎላይታን በቤተሰቡና በዘመዶቹ እየገዛ የሚገኘዉን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ አክለውም “የግለሰቡ የፖለቲካዉ አልፋና ኦሜጋ ቤተሰቡ ነዉ፡፡ ዎላይታ ዞን በጠንካራ አስተዳደር እንዳትመራ ያደረገ፤ የፖለቲካ ዕዉቀት የለሌዉ ነገር ግን በጓዳ ፖለቲካ የተካነ ግለሰብ ነዉ፡፡በእሱና በተላላኪዉ በአቶ ገብረመስቀል ጫላ በብቃት ሳይሆን በኔትዎርክ የተደራጀዉ የዎላይታ ዞን አመራሮች ከዞን አልፈዉ ለክልሉ ዕዳ ሆነዋል” ብሏል፡፡

ለማሳያነት ሲያብራሩ “ዎላይታ ሶዶ ያሉት ቀበሌዎችን በቅርጫ ተከፋፍለዉ 42 አመራሮችን እርስበርስ ሸንሽኖ በመመደባቸዉ ባለፉት ወራት አፈጻጸም በዞኑ ካሉት መዋቅሮች 19ኛ የወጣ ስሆን በራሷ ገቢ ወራዊ ደመወዝ መክፈል ወደማትችልበት ደረጃ ደርሳለች፡፡ በህዝቡ ስም በፌደራል መንግስት ሥልጣን ኮርቻ ቁጭ ብለዉ ዞኑን ከማተራመስ መቆጠብና የዞኑን ፖለቲካ ለፓርቲዉ፣ ለዞኑና ለህዝቡ መተዉ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ዞኑ ህጋዊ መዋቅር ስለሆነ በህግ እንጅ በግለሰቦች ፍላጎት ልመራ አይችልም” በማለት የችግሩን ጥልቀት አብራርቷል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ በትንሹ ለማንሳት እንደተሞከረዉ ዞኑ ለትላልቅ አደጋዎች ተዳርጓል፡፡ ከዚህ ችግር ለመላቀቅ ሁሉ አቀፍ በዕቅድ የሚመራና በጊዜ የተገደበ የተናበበ ሠላማዊ ትግል ይጠይቃል፡፡ የዎላይታ ጉዳይ የሚያቃጥለዉ ደፋርና የህዝቡን አንገት የማያስደፋ እዉነተኛ ታጋይ የሚያስፈልግበት ወቅት ደርሰናል፡፡ የህዝባችንን ህገመንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ መብትን ከሰፊዉ ሕዝብ የሚነጥቅ ምድራዊ ኃይል ልኖር አይችልም ብሏል፡፡

“በልመና የሚገኝ ዉጤት ስለሌን ዎላይታ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉ መገፋትና ጭቆና እስክቆም ድረስ፤ ሥራ አጥ ዜጎች በፍትሀዊነት ሥራ እስክያገኙ፤ የህዝባችን የፖለቲካ ዉክልና ምንም ሳይሸራረፍ ተግባራዊ እንክደረግና በህዝባችን ድርሻ መነሻ የሚገባንን በጀቶችና ልማቶች ሁሉ ያለምንም ግለሰብ ጣልቃ-ገብነት በአሰራሩ መሰረት ተፈጻሚ እስኪደረግ ድረስ ከማንኛዉም የፖለቲካ ፍላጎት ዉጭ የሆነ የተለያዩ ሰላማዊ የትግል አማራጮችን የሚንከተል ይሆናል” በሚል ጠቁሟል፡፡

“ይሄንን ሁሉ አቀፍ ሰለማዊ ትግል የሚያስተባብሩ አካላት በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሀገር ባሉት የዎላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ቅድመ-ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። ይህ ፍፁም ሠላማዊ የመጀመሪያ ዙር ትግል ከታህሳስ መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የሚካሄድ ስለሆነ ዝርዝሩ ጊዜዉ ስደረስ የሚናሳዉቅ ይሆናል” ብሏል፡፡

በመጨረሻም የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በክልሉ ወቅታዊ እንዲሁም በቀጣይ ሁኔታ በተመለከተ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በላኩት አቋም መግለጫ፦ “እስከዛ ድረስ ጥንቃቄ በተሞላበት መልክ ለትግሉ እየተዘጋጃችሁ እንድትቆዩ እያልን የሃይማኖት አባቶች በየሃይማኖት ተቋማት እግዝአብሄር ሃይልና ጉልበት እንድሆንልን በፀሎታችሁ እንድታግዙን ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን!!! “በታሪክ የምንመዘነዉ ለዎላይታ ሕዝብ ባሳየነዉ ዉግንና መጠን ነዉ!” ሲሉ የትግል ጥሪ አቅርቧል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita