
የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዎላይታ ዞን ቦሎሰ ሶሬ ወረዳ ወይቦ ወጋ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሳይንስ ለላቦራቶሪ አገልግሎት የሚውል የሕንጻ ግንባታ ጀመረ።
በማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል።
የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በትምህርትና ስልጠና መስክ የትምህርትን ጥራትን በለማሻሻልና ለማረጋገጥ በሳይንሳዊ መንገድ ችግሮችን በጥናት ለይቶ እየሰራ ይገኛል።
በዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከሚሰሩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች መካከል አንዱ የሆነውን የሳይንስ ላበራቶሪ ግንባታ በዎላይታ ዞን ቦሎሰ ሶሬ ወረዳ ወይቦ ወጋ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ስራ ጀምሯል።
ይህ ደረጃውን የጠበቀ የላቦራቶሪ ህንጻ ግንባታ ባለ 4 ክፍል እንደሆነና ለትምህርት ጥራት መሻሻልና መረጋገጥ አዎንታዊ ሚና እንዳለውም ተገልጿል።
የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 1.4 ሚሊዬን ብር የሚፈጅ ሲሆን፤ ለተግባራዊ የትምህርት ስራ አጋዥ እንደሆነና ከዚህ በፊት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን እንደሚቀርፍ ተጠቁሟል፡፡
የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ አሸናፍ አበበ እንደገለጹት፤ ኮሌጁ የማህበረሰቡን ችግሮችን በጥናት ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየተገበረ መሆኑን አውተዋል።
ከነዚህ ስራዎች አንዱ የሆነው ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚደረገው የላይበራቶሪ ግንባታ አንዱ መሆኑን ዲኑ ገልጸው፤ ግንባታው ተጠናቆ አስፈላጊው ቁሳቁስ ሲሟላ ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት አስታውጾው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የህንጻው ግንባታ ሲጠናቀቅ የውስጥ አደረጃጀት ማጠናከር በሚያስችል መልኩ እንደሚሰራ የኮሌጁ ዲን አቶ አሸናፊ አበበ ጠቁመዋል ሲል የዩኒቨርስቲው ኮጉዳ ዘግቧል፡፡