
“ህዝብን እንዲወክሉ ተመርጠው የተከበሩ የሚል ስም አግኝተው ራሳቸውን የወከሉ ተወካዮች” የመረጣቸው ህዝብ ጥያቄ አልቆ ነው እንዴ ዝም ያሉት ? በሚቀጥለዉ ምርጫ ምረጡኝ እያሉ ሊመጡ ነው? ! በተጨማሪም ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለምሁራኑ “በአሁኑ ወቅት ዎላይታ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13 ተወካዮች አሏት፥ ለምንድነዉ እነኝህ ተወካዮቻችን ምንም አይነት ጥያቄ የማያነሱት? የመረጣቸዉ ሕዝብ ጥያቄ የለዉም ይሁን? በሚል ለጠየቀው ቀጣዩን ማብራሪያ ሰጥቷል።
“ሕዝቡማ ብዙ ጥያቄ አለዉ፣ ተወካዮቹ አይጠይቁም እንጂ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዎላይታ ተወካዮች፣ በጣም አቅም ያላቸዉም ቢኖሩም ዝም ብለዉ ወንበር ያሞቃሉ። ሕዝቡ የፌደራል አመራር በመጣ ቁጥር የሚጠይቃቸዉ ጥያቄዎች ለምን በእንደራሴዎቹ እንደማይጠየቅ አይገባኝም፣ የሐገሪቷ አቅጣጫ ላይምኮ ድርሻችንን መወጣት አለብን” ይላሉ።
“የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የአስፈጻሚውን አካል ፈላጭ ቆራጭነት ማጋለጥ ከተቻለም መገደብ ስለሚቻል የሕዝብን ዉክልና በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል። 13ቱም ተወካዮቻችን 5ቱንም አመት አንዳች ሳይተነፍሱ፣ ቆይተዉ በሚቀጥለዉ ምርጫ ምረጡኝ ሊሉን አይገባም” ሲሉም አስረድተዋል።

ለመሆኑ ባለፉት ዓመታት በቅርቡ ይገነባሉ ተብሎ በመሠረተ ድንጋይ ደረጃ ብቻ የተገደቡ ፕሮጀክቶችን ያውቃሉ ?


1. በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከኮካቴ እስከ ካዎ ሞቶሎሚ አደባባይ፣ ከካዎ ጦና አደባባይ እስከ ጉኑኖ ማዞሪያ የሚዘልቀው አስፋልት መንገድ፣
2. የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት፣
3. የቆርቆሮና ምስማር ፋብርካ፣ የወተት ከብት እርባታና የወተት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ፣ ቺፕውድ ኢንዱስትሪ፣ ወዘተ
4. ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤
5. ተጀምሮ የቆመው የሦስት የጀግኖችና ባለውለታዎች ሐውልቶች፣
6. የአረካ ግብርና ምርምር ልህቀት ማዕከል፤
7. የቦዲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል፤
8. የአበላ ፋራቾ እንስሳት ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ፤
9. አበላ አባያ ሳመር ሲቲ (Abaya Summer City)፤
10. የድምቱ ከተማ አዳሪ ትምህርት ቤት፣
11. ኦሞቲክ የቋንቋና ባህል ማዕከል፤
12. ከቀይ መስቀል_ዴሪ_ቴክኖሎጂ ካምፓስ_ዳልጋ ከብት_ገጠር ቴክኖሎጂ የሚዘልቀው አስፋልት መንገድ፤
13. ብሔራዊ ባንክ ቅርንጫፍ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዲስትሪክት ሕንጻዎች
14. የብላቴ መስኖ (በሆሎታ ከተማ የሚገነባውና ወላይታን፣ ኦሮሚያን፣ ሀዲያንና ሲዳማን ተጠቃሚ የሚያደርግ)
15. ክልሉ መክፈል ያለበት የካሳ ባለመክፈሉ የቆመው በአረካ አቅራቢያ የሚገነባው አየር ማረፊያ ግንባታ
በተጨማሪም በዞኑ በየአካባቢው የህዝብ መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተመለከተ ለበርካታ ዓመታት አብዛኛው ይሰራል ተብሎ ቃል የተገባ ይሁን መሠረት ድንጋይ የተጣለበት ፕሮጀክት ከማስጀመሪያ ፎቶ አላለፈም። ህዝብ እየሆነና እየታዘበ ባለው ተስፋ ቆርጠው Nu Deriyaaba Xoossi erees (የእኛን ነገር ፈጣሪ ያውቃል) በሚል ዝምታን መርጧል።
እንደሚታወቀው የዎላይታ ዞን በሀገሪቱ ከየትኛውም አከባቢ በላይ ወደ 2 መቶ ሺህ የሚጠጋ ከታወቁ ከፍተኛ ዩንቨርስቲዎችና ኮሌጆች የተመረቁ የስራ አጥ ወጣቶች የሚገኙበት፤ ፓለቲካዊ ቁውስ በፈጠረው ችግር ህፃናት በጨቅላ ዕድሜያቸው በሀገሪቱ ጎዳናዎች ሁሉ የስቃይ ህይወት እየገፉ ይገኛሉ። የወጣቱ ተስፋና የስራ ዕድል አማራጭ በግዴታም በውዴታም ውትድርና ብቻ እየሆነ ነው። በአከባቢው በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት የወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ እንዱስትሪና ሌሎች ተቋማት ባለመሰራቱ ችግሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ አባብሶታል።
ከዚህም የተነሳ ሴቶችና ወንዶች አስቸጋሪውን ሞትና ስቃይ ፊትለፊት እየተጋፈጡ ወደተለያዩ ስደት ሀገር ያቀናሉ። ዕድል ቀንቷቸው ከሞት ተርፈው ወደ አረብ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት የገቡ የተቀረውን ቤተሰቦቻቸውን በቻሉት መጠን ያግዛሉ።
ሌላው ደግሞ በአከባቢው ከህዝብ ተጠቃሚነት አንፃር ምን ለውጥ ያመጣል የሚለው ተዘንግቶ በግልጽ እየታየ ባለው ሁኔታ በክልሉ በየትኛውም አከባቢ ተግባራዊ ያልሆነ በተለየ መንገድ በዎላይታ የአመራሮች ሹም ሽረት መብዛት፣ የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ባለሀብቶችን የማሳደድና ተረጋግተው እንዳይሰሩ የሚወሰዱ እርምጃዎች ለአከባቢው ልማት በጎ ሚና ከመጫወት ይልቅ በኢኮኖሚ ሆነ ፓለቲካ ተሳትፎ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ለማድረስ ያመዘኑ እንደሆነ ይነገራል።
በተለይም የብሄሩ ተወላጆች ከፌደራል፣ ከክልል እንደሁም ከዞን ጀምሮ በተመደቡበት ኃላፊነት ቦታ ተረጋግተው እንዳይሰራ በመደረጉ ይባስ ብሎ “ደቡብ ኢትዮጵያ” በሚል የተዋቀረ ትንሹ ክልል ከመደራጀቱ በፊት በትልቁ ከ56 ብሄር ብሄረሰቦች በላይ አብሮ በአንድ ክልል በነበረው አደረጃጀት ውስጥ ከህዝብ ቁጥርና ተያያዥ እውነታ አንፃር በመንግሥትና በገዢ ፓርቲ መርነትም ተገቢ ውክልናና ተጠቃሚነት የነበረ ቢሆኑም አሁን በትንሹ ክልል የነበረውን ጭምር በማጣት ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ቀውስ የተጋለጠው ከዚህ የሚመነጭ እውነታ እንደሆነ አይካድም።
ይህ ሁሉ አድሏዊና ኢፍትሐዊ አሰራር በህዝብ ላይ በተደቀነበት በዚሁ ወቅት የህዝብ ተወካዮች ሆነ የህዝብ ድምፅ እንዲደመጥ የማድረግ ዕድል በእጃቸው የያዙ አካላት የራሳቸውን ጥቅምና ክብር ከማስጠበቅ ውጪ የህዝብ ውግንና እያሳዩ አይደለም በሚል በርካቶች ትዝብታቸውን በምሬት እያካፈሉ ይገኛሉ።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #wolaita